| መደበኛ ያልሆኑ የሥራ መስኮች... |
|
|
| Wednesday, 30 April 2008 | |
|
መደበኛ ያልሆኑ የሥራ መስኮች ኢኮኖሚያዊ እድገት ወሳኝ ናቸው
በጋዜጣው ሪፖርተር መደበኛ ያልሆነው (informal) የሥራ መስክ ከመንግሥት ቁጥጥርና ከታክስ መጣል ጋር ያላቸው ግንኙነት አነስተኛ በመሆኑ በአፍሪካ ውስጥ ከፍተኛ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ መሆናቸው ተገለፀ፡፡ ይህ ዘርፍ በዚሁ ከቀጠለ አፍሪካ ድህነትን ለመቀነስ እያደረገች ባለው ጥረት አጋዥ ሊሆን እንደሚችልም ተጠቁሟል፡፡ ባለፈው ሳምንት አዲስ አበባ ውስጥ በተካሄደው የአፍሪካ ህብረት የሥራና የማኅበራዊ ጉዳዮች ስብሰባ ላይ እንደተገለፀው መደበኛ ያልሆነው የሥራ ዘርፍ በቴክኒክ ሲመዘን ሕገ ወጥ የሥራ ዘርፍ ቢሆንም ለአገር እድገትና ማኅበራዊ ችግሮችን ለመፍታት ያላቸው ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ያመለክታል፡፡ በዚህ መደበኛ ባልሆኑ የሥራ መስኮች ዙሪያ በቅርቡ የተደረገ ጥናትና ጥናቶቹም ያመለከቱት አሃዛዊ መረጃዎች ከሰሃራ በታች ያሉ በርካታ አገራት ያሉ ወጣቶች ሥራ የሚጀምሩት ኢ-መደበኛ በሆነ የሥራ ዘርፍ ውስጥ በመግባት ነው፡፡ የአፍሪካ ኅብረት የሥራና ማኅበራዊ ጉዳይ ኮሚሽን ኮሚሽነር ቢሮንሴ ጋዋናስ በዚሁ ስብሰባ እንደገለፁት በአሁኑ ወቅት ኢመደባዊ የሆነው የኢኮኖሚ ዘርፍ (Informal economy) እንደ አንድ አጋዥ መሣሪያነት የምንቀበልበት ወቅት ላይ ደርሰናል ብለዋል፡፡ በተለይም አፍሪካ ካለችበት ኢኮኖሚያዊ ችግሮችና ድህነትን ለማጥፋት በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ትልቁ መሣሪያችን ይኸው ኢ-መደባዊ የሆነው ዘርፍ መሆኑንም የተለያዩ መረጃዎችን በማጣቀስ ገልጿል፡፡ እንደ ኮሚሽንሩ ገለፃ ከሆነ ኢ-መደባዊ የሆኑ ሥራዎች በተለይ ከመንግሥት ቁጥጥር ውጭ ሆነው የሚንቀሳቀሱና እንደ ታክስ ካሉ ጉዳዮች ጋር ያልተገናኙ በመሆናቸው ለድህነት መጥፋት ትልቅ ሚና ይጫወታሉ፡፡ በቅርቡ በሰባት የአፍሪካ አገሮች በተደረገ ጥናት ኢመደበኛ የሆነው የኢኮኖሚ ዘርፍ ለአህጉሪቷ እድገት ተጠቃሽ ሊሆን የሚችል መሆኑን የጠቆመው ይኸው ዘገባ በደቡብ አፍሪካ ይህ ዘርፍ በአገሪቱ ከጠቅላላው 36 በመቶ ይሆናል፡፡ ይህም አነስተኛ የተባለ አሃዝ ሲሆን እንደ ቤኒን፣ ካሜሮን፣ ሴኔጋል፣ ታንዛኒያ እና ዚምባብዌን በመሳሰሉ አገራት ደግሞ ከሚገኘው ጠቅላላ ገቢ ውስጥ ከ60 በመቶ በላይ ድርሻ እንዳለው ተጠቁሟል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |