Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow 400 የኢራን ባለሀብቶች አፍሪካን ይጎበኛሉ
400 የኢራን ባለሀብቶች አፍሪካን ይጎበኛሉ Print E-mail
Wednesday, 30 April 2008
በዳዊት ታዬ

በአምስት ምድብ የተከፈሉ 400 የኢራን ባለሀብቶች ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የአፍሪካ አገራት ውስጥ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ለመሰማራት ጉብኝት እንደሚያካሂዱ ተገለፀ፡፡

አይ.አር.ኤን.ኤ የተባለው የኢራን የዜና አገልግሎት ከትናንት በስቲያ ባሠራጨው ዘገባው ወደ ኢትዮጵያና ሌሎች የአፍሪካ አገራት የሚመጡት የኢራን ባለሃብቶች ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ለማፍሰስ የሚያስችላቸው ጉብኝት እንደሆነ አመልክቷል፡፡ በአፍሪካ የኢራን ኢንቨስተሮች ሽፋን እንዲጨምር የአገሪቱ ባለሀብቶች ትኩረት የሰጡት ጉብኝት እንደሚሆን ጠቁሟል፡፡

የኢራን ኢንቨስተሮች ኢትዮጵያን ጨምሮ ቱኒዚያ፣ ሱዳን፣ ሊቢያና ግብፅን የሚጎበኙ ሲሆን ይህንን ያህል አባላት ያለው የኢራን የንግድ ልኡካን ወደ አፍሪካ ሲመጣ የመጀመሪያው እንደሆነም ተጠቅሷል፡፡

ከጉብኝቱ ጋር በተያያዘ ባለሀብቶቹ አፍሪካ ውስጥ በሚካሄዱ የንግድ ኤግዚቢሽኖች ላይ የሚሳተፉበትን ሁኔታ የሚያመቻቹ ሁለት የኤግዚቢሽን ኩባንያዎችም ከባለሀብቶቹ ጋር ጉብኝት ወደሚያደርጉባቸው አገሮች ይመጣሉ፡፡
እነዚህ ኩባንያዎች የኢራን አምራቾች በአፍሪካ ውስጥ በሂደት ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ ድምፅ በመሆን የሚያገለግሉ ሲሆን አፍሪካ ውስጥ ኢንቨስት ለማድረግ የሚያስችላቸውን ቅድመ ስምምነቶች ለማድረግም የሚረዳቸውም ይሆናል፡፡

በአምስት ምድብ የተከፈሉት እኒሁ የኢራን ባለሀብቶች በአምራችነት ከምትታወቀው ሃሜዳን ግዛት የተውጣጡ ሲሆኑ የሚያመርቷቸውም ምንጣፎች፣ የሴራሚክስ ውጤቶችና ማሽነሪዎች መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡ ኩባንያዎቹ ጉብኝት ከሚያደርጉባቸው አገሮች ነጋዴዎች ጋራ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ያደርጋሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡ በተለይ ምርቶቻቸውን ወደ ኢጣሊያ፣ ኔዘርላንድ፣ ጀርመን፣ ዩክሬን፣ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ፣ ካናዳ እና ሩሲያ ኤክስፖርት በማድረግ የሚታወቁ መሆናቸውም ዘገባው ገል"ል፡፡

የኢራን የንግድ ልኡካን ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውን በተመለከተ ያነጋገርናቸው የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ምክትል ዋና ፀሐፊ አቶ ታምራት አድማሱ ከኢራን ጋር ያለው የንግድ ግንኙነት እያደገ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ምክር ቤቱ በየዓመቱ በሚያካሄደው የንግድ ትርዒት ላይ የሚሳተፉ የኢራን ኩባንያዎች ቁጥር አድጓል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት ለማድረግ የሚፈልጉ የኢራን ኩባንያዎች ተመሳሳይ በሆነ መንገድ እድገት ማሳየቱና ከኢትዮጵያውያን ኩባንያዎች ጋር በጋራ ለመሥራትና ምርቶቻቸውን እዚህ እንዲያከፋፍሉላቸው የሚፈልጉ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡

ምክር ቤቱም ከኢራን ኩባንያዎች ጋር በተለያየ ጊዜ ውይይት ሲያደርግ እንደነበርና በተለይ ምርቶቻቸውን በኢትዮጵያ ለማከፋፈል የሚሹ መሆናቸውን የገለፁት አቶ ታምራት በቅርቡ ይመጣል ተብሎ የሚጠበቀው የኢራን ልኡክም ከምክር ቤቱ አባል ኩባንያዎች ጋር በማገናኘት በጋራ የሚሠሩበት መንገድ እንዲመቻች ይደረጋል ብለዋል፡፡
 
< Prev   Next >