Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow የአንድ በርሜል የነዳጅ ዋጋ 122 ዶላር ደረሰ
የአንድ በርሜል የነዳጅ ዋጋ 122 ዶላር ደረሰ Print E-mail
Wednesday, 30 April 2008
በዚህ ሣምንት መጀመሪያ ላይ የአንድ በርሜል የነዳጅ ዋጋ 122 ዶላር መግባቱ ተገለፀ፡፡ ከነዳጅ ምርት ጋር የተያያዙ የሌሎች ምርቶችም ዋጋ እያሻቀበ መጥቷል፡፡

አሶሼትድ ፕሬስ እንደዘገበው የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ማደጉንና በአንድ ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ የዋጋ ለውጡ በእጥፍ አድጐ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተመልክቷል፡፡

ባለፈው ሣምንት እንኳን የአንድ በርሜል የነዳጅ ዋጋ 115 ዶላር ነበር ያለው ዘገባው በአንድ ሣምንት ውስጥ ከሰባት ዶላር በላይ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

በሰሞኑ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ዋነኛ መንስኤው በናይጀሪያ የነዳጅ ማምረቻ ቦታ የተቀሰቀሰ ብጥብጥና እንግሊዝ አንድ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ መዝጋት ጋር ተያይዞ ነው፡፡

እንደዘገባው ከሆነ የነዳጅ ዋጋ በፍጥነት እያደገ መምጣት ከነዳጅ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ምርቶች ላይም ከፍተኛ የዋጋ ለውጥ እያመጣ ነው፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት የዋጋ ለውጡ ፍጥነት እስከ ዛሬ በነዳጅ ዋጋ ላይ ያልታየ ሲሆን አሁን እየተመዘገበ ያለውን ዋጋ በሪኮርድነት እየተመዘገበ ነው፡፡ በየወቅቱ የሚነሱ ምክንያቶችና የነዳጅ አምራች አገሮች ዋጋውን ለመቀነስ ያላቸው ፍላጐት አነስተኛ በመሆኑ ከዚህ በኋላ ዋጋው ይቀንሳል የሚል ተስፋ የሌለ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

በዚሁ የነዳጅ ጭማሪ ሳቢያ ለምርት ግብዓት የሚሆነው የአንድ ቶን ዳፕ ማዳበሪያ ዋጋ አንድ ሚሊዮን ዶላር እንዲደርስ አድርጐታል፡፡ ለመንገድ ሥራ የሚውለውም አስፖልት ዋጋም ተመሳሳይ በሆነ መልኩ እየጨመረ በመምጣቱ የመንገድ ግንባታ ዋጋ ከፍ እንዲል እያስገደደ መምጣቱም ታውቋል፡፡

 
< Prev   Next >