| የአበሻ ባንክና ደንበኞቹ |
|
|
| Wednesday, 30 April 2008 | |
|
አፄ ምኒልክ ባንክ እንዲከፈት ከመፍቀዳቸው በፊት ለምዕት ዓመታት መገበያያም ከመሆን አልፎ የጣዖትነት ባሕሪ የተጎናፀፈውን የ"ማርትሬዛ" ብር በሀገራዊ ገንዘብ ለመተካት ልዩ ጥረት አድርገው ነበር፡፡ ይህንንም የዜና መዋዕል ጸሐፊያቸው ጸሐፌ ትእዛዝ ገብረ ሥላሴ እንደሚከተለው ይገልፀዋል፡- "ነገር ግን እስከዚህ ቀን ድረስ የሚነገድበት ከወዲያ አገር የመጣ ብር ነበር እንጂ ከዚህ አስቀድሞ በኢትዮጵያ ሁሉ ነገሥታት በስማቸውና በመልካቸው አላሳተሙም ነበር፡፡
አጼ ምኒሊክ ገንዘብ ቅንስናሽ ሣንቲሞች (ሩብ፣ ተሙን፣ ቢሳ፣ ወዘተ ስላሉት ከማርትሬዛ ብር የተሻለ ቢመስልም፣ በኦስትሪያውን ገንዘብ ከዙፋኑ ለማውረድ ቀላል አልሆነለትም፡፡ ይልቁንም ሳንቲሞቹ ተወዳጅ ከመሆናቸው የተነሳ ከገበያ እየጠፉ ስላስቸገሩ፣ የጥቅማቸውን ያህል ሌላ ችግር ይዘው ብቅ አሉ ማለት ይቻላል" በዘመኑ የከተማ ዋና የገበያ ማዕከል ከነበረው ከአራዳ ብዙም ሳይርቅ ዋና መሥሪያ ቤቱን ያደረገው የአበሻ ባንክም ቢሆን በአገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ የነበረው ሚና ያን ያህልም የጎላ አልነበረም፡፡ ለዚህም አንዱ ምክንያት ባንኩ ለብድር ያስከፍል የነበረው የ12-15 በመቶ ወለድ ሲሆን ተቋሙ ለሃገሪቱ ባሕልና የእድገት ደረጃ ባዕድ መሆኑ የበኩሉን አስተዋጽኦ አድርጎ ነበር፡፡ ገንዘብን ለማያውቁት ባዕድ አካል ሰጥቶ ከመጨነቅ እንደወትሮው ትራስ ስር ወይም ማሰሮ ውስጥ ማስቀመጡን የሚመርጡ ጥቂት አልነበሩም፡፡ ደፍረው ያስቀመጡት ቢሆኑም እንቅልፍ አጥተው በጠዋት እየመጡ ገንዘባቸው በሰላም መኖሩን ለማረጋገጥ የሚወተውቱ እንደነበሩ የዘመኑ ታዛቢዎች ይተርካሉ፡፡ ከዚህም አልፈው ያስቀመጡትን ብር ራሱን በአካል ካላየሁ ብለው የሚያንገራግሩም አልታጡም ነበር፡፡ (የባንክ አመሰራረትና እድገት በኢትዮጵያ፣ ባህሩ ዘውዴ"ፕሮፌሰር") ውኃና ምግብ አንድ ሰው ከረሀብ ለማምለጥ በአንድ ዓመት 200 ኪሎ ግራም እህል መመገብ ይኖርበታል፡፡ አንድ ኪሎ ግራም እህል ለማምረት በትንሹ አንድ ሜትር ኩብ ውሃ ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ ለአንድ ሰው ለአንድ ዓመት የሚያስፈልገውን 200 ኪሎ ግራም እህል ለማምረት 200 ሜትር ኩብ ውሃ ያስፈልጋል፡፡ ይህም አምስት ትላልቅ የነዳጅ ቦቴ ከነተሳቢው መሆኑ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ያሉትን 70 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን ለመመገብ በየዓመቱ 14 ቢሊዮን ኪሎግራም ወይም 140 ሚሊዮን ኩንታል እህል የሚያስፈልግ ሲሆን ይህን ያህል እህልም ለማምረት በእያንዳንዱ ዓመት 14 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ውሃ ያስፈልጋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ከ20 ዓመታት በኋላ ለሚኖረው 100 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊ አንድ ዓመት ለመመገብ 20 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ውሃ ያስፈልጋል፡፡ (ታደሰ ኃ/ሥላሴ፣ የጥናት ፅሁፍ፣ 1996) "የሰይጣን ሥራ" የግብጹ ጳጳስ አቡነ ሰላማ እ.ኤ.አ በ1843 አካባቢ ወደ ሃገር ያስገቡት በውሃ የሚሰራ የእህል ወፍጮ ሸዋ ውስጥ ተተክሎ የነበረ ቢሆንም እንኳን፣ የአካባቢው ቀሳውስት ወፍጮው "የሰይጣን ሥራ" ነው ብለው እንዲነቃቀል አድርገዋል፡፡ የዚህን ወፍጮ መነቀል የደገፉት አፄ ቴዎድሮስ (ምንም እንኳን የሰይጣን ሥራ ነው ብለው በማመን ባይሆንም) ጳጳሱን አቡነ ሰላማን ዳግመኛ የዚያ ዓይነት ወፍጮ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳያስመጡ ከለከሏቸው፡፡ ቴዎድሮስ ለዚህ ውሳኔያቸው የሰጡት ምክንያት ደግሞ "በሴቶቻችን ክንድ ምን ልናደርግበት ነው?" የሚል ነበር፡፡ ከአፄ ቴዎድሮስ በተለየ ሁኔታ አፄ ዮሐንስ የወፍጮው መምጣት ጥሩ ሃሳብ እንደነበር ያመኑ ሲሆን ምክንያታቸውም "የከበቡንን ሴቶች ብዛት ይቀንሳል" የሚል ነበር፡፡ ወፍጮ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲተከልና እንዲሰራበት ሃሳቡን የተቀበሉትና ሌሎችን እንዲቀበሉ ግፊት ያደረጉት አፄ ምኒልክ ሲሆኑ በዚያም መሠረት እ.ኤ.አ በ1888 በአቃቂ ወንዝ ላይ በሃይድሮሊክ የሚሰራ ወፍጮ ተተከለ፡፡ "ጣይቱ እና ምኒልክ" በሚል ርዕስ መፅሐፍ የፃፈችው ክሪስ ፕሩቲ እንደገለፀችው አንዲት ሴት ወፍጮውን ለተከለው ኢንጂነር ለካፑቺ "ይህንን ድንቅ መሣሪያ እንድታይ በሕይወት በመቆየቷ እግዜርን እንደምታመሰግን" ነግራዋለች፡፡ ከዚህ በኋላ "ምንም የማይሳነው" የሚባለው የምኒልክ አማካሪ ስቴቭኒን ንጉሡ በእጅ ኃይል የሚሰሩ ወፍጮዎችን ከፈረንሣይ ለማስመጫ የሚሆን ገንዘብ እንዲመድቡ አጥብቆ ጠየቃቸው፡፡ በወቅቱ ስቴቭኒንግ ያቀረበው ማሳመኛ "በአድዋ ጦርነት ወቅት የኢትዮጵያ ጦር አቅም የተዳከመው ለዳቦ የሚሆን ዱቄት በብቃት ለማግኘት ባለመቻሉ ነው" የሚል ነበር፡፡ አውሮፓ ውስጥ ስቴቭኒን እነዚያን በእጅ የሚሠሩ ወፍጮዎች በጥሩ ዋጋ አግኝቶ ነበር፡፡ ምክንያቱም በተለይ ፈረንሳይ ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል መገኘት የእጅ ወፍጮዎችን ከአገልግሎት ውጪ አድርጓቸው ስለነበር ነው፡፡ (ቴሌ ነጋሪት መፅሔት፣ 1995) ድብቁ አእምሮ አንዱ ደስተኛ ሌላው ሀዘንተኛ፣ አንዱ ባለፀጋ ሌላው ደሀ፣ አንዱ ፈሪና ተጠራጣሪ ሌላው በእምነት የተመላና በራሱ የሚተማመን፣ አንዱ ስኬታማ ሌላው የማይሳካለት የሚሆነው ለምንድን ነው? የሚለው የብዙዎቻችን ጥያቄ ነው፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ የድብቁን አእምሮ ምትሀታዊ ሀይል በሚገባ የመጠቀም ወይም ያለመጠቀም ጉዳይ ነው፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት የአንድ ሰው ስብእና በድብቁ አእምሮው ክፍል ከሚያስበው ነገር ጋር የተቆራኘ በመሆኑ ነው፡፡ ሁሉም ሰው ያለው አንድ አእምሮ ነው፡፡ ልዩነቱ ያለው የድብቁን አእምሮ ተአምራዊ ሀይል መጠቀም ያለመጠቀሙ ላይ ነው፡፡ በመሆኑም ጆሴፍ ሙርፔይ የተባሉ ምሁር በውስጣችን ተከማችቶ ያለውን መጠነ ሰፊ እምቅ ሀይል በመገንዘብ አውጥቶ ለመጠቀም ተከታዮቹ ነጥቦች ጠቃሚ ናቸው ይሉናል፡፡ 1. መልካም ነገር ለማግኘት መልካም አስቡ፡፡ ለአወንታዊ ሀሳቦች ቦታ ስጡ፡፡ 2. የሌሎችን ደስታ የምትሹ፣ በህብረት መሥራት የምትወዱ፣ የጓደኝነት መንፈስ ያላችሁ ሁኑ፡፡ 3. ባላችሁ ትልቅ የመምረጥ ሀይል ደስታንና ጤንነትን ምረጡ፡፡ 4. የራሳችሁ ሀሳብ እንጂ የሌሎች አስተያየት በእናንተ ላይ ጉዳት እንደማያደርስ ራሳችሁን አሳምኑ፡፡ 5. ለመናገር የምትፈልጉትን ነገር አስተውላችሁ ተናገሩ፡፡ 6. "አልችልም" የሚለውን ቃል በድብቅ አእምሮዬ ሀይል ተጠቅሜ ሁሉንም ለማከናወን እችላለሁ በሚል ሀረግ ተኩት፡፡ 7. ሌሎች በእናንተ እግር ሆነው እንዲያስቡላችሁ ፈፀሞ አትፍቀዱ፡፡ 8. ንቁው አእምሮአችሁ ያመነበትን ነገር ሁሉ ድብቁ አእምሮአችሁ ስለሚቀበል በጥሩ እድል፣ በመለኮታዊ እርዳታና በመልካም ተግባር እመኑ፡፡ (አዲስ ኢንቨስትመንት መፅሔት፣ ነሐሴ 1999) መሄዴ ነው ባር ባር አለ ሆዴ፣ ልቤ መሬት ለቆ ሊያከንፈኝ እንዳይሆን፣ አለግብሩ መጥቆ አለአስተዳደጉ፣ አለባህሉ ወድቆ፡፡ ሽው እልም ሽው እልም፣ ልቤ ወፌ-ይላላ በመስተፋቅር ቀስት፣ በሮሮ ምሀላ እንደደመና አክናፍ፣ እንደጮራው ጥላ ሽው እልም ሽው እልም፣ ሽው እልም ይላላ፡፡ ነሸጠው፣ ሸፈጠ፣ ሄደ ሸመጠጠ በመስተፋቅር ጦር፣ በሮሮ አመለጠ፡፡ (ፀጋዬ ገ/መድኅን፣ እሳት ወይ አበባ፣ 1999) ሚጥሚጣ ለምግብ መፈጨት የባህላዊውም ሆነ የዘመናዊው ሕክምና ጠበብት የሚጥሚጣን ፈውስ ሰጪነት ይቀበላሉ፡፡ ሚጥሚጣ ለብርድ፣ ለነርቭ ህመምና ለቁርጥማት ማስታገሻነት ከሚመረቱ የዘመናዊው ሕክምና ቅባቶችና ፕላስተሮች ጋርም ይዳበላል፡፡ ሚጥሚጣ በአግባቡ ጥቅም ላይ ከዋለ፣ ከዊስኪና ከብራንዲ በተሻለ ሁኔታ የአካል ሙቀትን በመለገስ መንፈስን ያነቃቃል፡፡ ሆድ ዕቃ ውስጥ የተከማቸን ጋዝ በማስወገድ ጨጓራ ሥራውን በወጉ እንዲያከናውን ያደርጋል፡፡ በ1942 የታተመው "ዘ ኮስመቲክ ዲክሽነሪ" እንደሚያትተው፣ ሚጥሚጣ ከዳቦ ዕንቡጥ ጋር በኪኒን መልክ ተጠቅልሎ ሲዋጥ፣ የምግብ አለመፈጨትን በፍጥነት ያስወግዳል፡፡ ለመድኃኒትም ሆነ ለምግብነት የሚውለውን የሚጥሚጣ መጠን የሚወስነው ባለቤቱ ነው፡፡ ሚጥሚጣ በአፍም ሆነ በጨጓራ ውስጥ አንዳችም ችግር እስካልፈጠረ ድረስ መጠኑን እንደአስፈላጊነቱ ከፍ ማድረግ ይቻላል፡፡ የሚጥሚጣ ውጤት ፈጣንና ቀጥተኛ ነው፡፡ አንድም ድባቅ ይመታል፤ አሊያም የህመምን ጥላ ወዲያውኑ ይገፋል፡፡ ሚጥሚጣን ጥቅም ላይ በማዋል በኩል ከቀዝቃዛዎቹ ይልቅ ቆላማዎቹ ሀገሮች የመጀመሪያውን ሥፍራ ይይዛሉ፡፡ (አባይነህ አበራ፣ ዶክተር ለራሴ (ትርጉም"፣ 1990) ገራገር ቼኮሌትን ለምርምር የሚመገቡ ሴቶች ሳይንቲስቶች ለአንድ ዓመት የቼኮሌት ቁራጭ የሚመገቡ ሴቶችን ይፈልጋሉ፡፡ ታይምስ እንደዘገበው የምሥራቅ አንጀሊያ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች 150 በጐ ፍቃኞችን ይፈልጋሉ፡፡ የጥናቱ ዓላማም ፣ሴቶች ካረጡ በኋላ የሚከሰተውን የልብ ህመም ቼኮሌት ይከላከላል፣ የሚለውን ለማረጋገጥ ነው፡፡ በውስጡ የያዛቸው ጣዕም ሰጪ ንጥረ ነገሮችና በካካዋ ውስጥ የሚገኙ የአትክልት ድብልቆች የልብ በሽታ አምጪ ተህዋስያንን ይቀንሳሉ ብለዋል ተመራማሪዎቹ፡፡ በጎፈቃደኛ ሴቶቹ ያረጡ፣ የልብ ህመም ተጠቂዎችና የኮሌስትሮል መጠናቸውን በመቀነስ ላይ ያሉ መሆን አለባቸው፡፡ ሰዎች ከፍተኛ የስኳር መጠንና ስብ ያላቸውን ቼኮሌቶች መብላት እንደሌለባቸው በእርግጠኝነት እንመክራለን ብለዋል የምርምሩ ዳይሬክተር ኢያን ፍሬም፡፡ ኢራን የአሻንጉሊቶች ገበያ አሳሰባት በኢራን የመንግሥት ሕግ አስፈፃሚ የኢራንን ገበያ ያጥለቀለቁትን የአሜሪካን የግርቢ አሻንጉሊቶች ከፍተኛ ማሕበራዊና ባህላዊ ቀውስ እያስከተሉ መሆኑን አስታወቀ፡፡ "ሕገወጥ ነው" በማለት የሕግ አስፈፃሚው ቃል አቀባይ ጐርባን አሉደሪ ናሽፋባስ ለኢራን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር በፃፉት ደብዳቤ ገልፀዋል፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢራን የተከሰተውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን ተከትሎ የኢራን ገበያዎች በሕገወጥ መንገድ በሚገቡ የምእራባዊያን አሻንጊሊቶች መጥለቅለቃቸውን ዴይሊ ቴሌግራፍ ዘግቧል፡፡ ሚስተር ናሽፋባስ ኢራን በዓለም የአሻንጉሊቶችን ከውጭ ከሚያስገቡ አገሮች ግንባር ቀደም ስትሆን እነዚህ ከውጭ የሚገቡ አሻንጉሊቶች የማንነት ቀውስ ማስከተላቸውን ገልፀዋል፡፡ ቻይናዊው በሽቦ ኬብል ላይ መኪና ነዳ አንድ ቻይናዊ ከወራጅ ወንዝ 45.72 ሜትር ወደ ላይ ርዝመት ባለው ከፍታ ላይ በተዘረጉ ሁለት የሽቦ ኬብሎች ላይ መኪና በመንዳት አስጨናቂውን ጉዞ አጠናቋል፡፡ በሁናን መንደር ነዋሪ የሆነው የ48 ዓመቱ ጎልማሳ ሊዊ ሱዝሁ 228 ሜትሩን የሽቦ ላይ ጉዞ በመኪና ሲያካሂድ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ተመልካቾች በአካል ተገኝተው ተመልክተውታል፡፡ ጉዞውን ለመጨረስ 30 ደቂቃ የወሰደበት ሉዊ በቻይና የመኪናው ንጉሥ የሚል ትልቅ ስም ተሰጥቶታል፡፡ ኬብሎቹ መኪና ሲሄድባቸው ይንቀጠቀጡ ስለነበር በተለይ የጉዞው የመጨረሻ ደቂቃዎች በጣም ፈታኝ እንደነበር የሚናገረው ሉዊ በየደቂቃው መኪናውን ያቆም እንደነበርና አየርም ያጥረው እንደነበር ገል"ል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |