Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Aug 08th
Home arrow Sections arrow የብሔራዊ ባንክ ሰራተኞች ማህበር ማኔጅመንቱን...
የብሔራዊ ባንክ ሰራተኞች ማህበር ማኔጅመንቱን... Print E-mail
Thursday, 10 January 2008

የብሔራዊ ባንክ ሰራተኞች ማህበር ማኔጅመንቱን በመቃወም ለሥራ አመራር ቦርዱ ሰብሳቢ ደብዳቤ ጃፈ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ሰራተኞች ማህበር መንግሥት የኑሮ ውድነትን ምክንያት በማድረግ ለሚያስተዳድራቸው ተቋማት ያደረገውን የደመወዝ ማስተካከያ በማስመልከትና ማኔጅመንቱን በመቃወም የባንኩን ገዢዎች በማለፍ ለስራ አመራር ቦርዱ ሰብሳቢ ደብዳቤ ፃፈ፡፡

ማህበሩ በቀጥታ ለሰብሳቢው ደብዳቤ የፃፈው ለባንኩ የበላይ አስተዳደር ህዳር 30 ቀን 2000 ዓ.ም በቁጥር ኢብሰማ/006/2000 ለፃፈው ደብዳቤ ምላሽ ባለማግኘቱ መሆኑን አንዳንድ ሰራተኞች ለሪፖርተር ጋዜጣ ገልጸዋል፡፡

ማህበሩ በደብዳቤው ..ህጋዊ ለሆነው የሰራተኞች ማህበር የሚሰጠው መልስ ምንም ይሁን ምን በተገቢው ጊዜ ውስጥ መልስ ሳይሰጥ ከአንድ ወር በላይ መውሰዱ ህብረት ስምምነቱ የሚጥስ ብቻ ሳይሆን መንግስት በአገር አቀፍ ደረጃ እየተገበረ ካለው የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ፕሮግራሞችና ባንኩም ከጀመረው መሰረታዊ የሥራ ሂደት ማሻሻያ ጥናት ጽንሰ ሀሳብ /ቢ.ፒ.አር ኮንሴፕት/ መመሪያ ጋር የማይጣጣም አካሄድ ነው.. በማለት ሠራተኛው በበላይ ሀላፊዎቹ ቅር መሰኘቱን ማብራራቱን ሰራተኞች አብራርተዋል፡፡

በሲቪል ሰርቪስ ውስጥ እንዲተገበር የተፈለገው የአሰራር ስርዓት ደንበኛ ተኮር፣ ቀልጣፋ፣ ፈጣንና ግልፅ የሆነ ምላሽን መስጠት የሚችል መሆን እንዳለበት በአቅም ግንባታ ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ የተሰራጨውን መመሪያ ጠቅሶ ለሰብሳቢው በፃፈው ደብዳቤ ያሳወቀው ማህበሩ፣ በግልም ሆነ በሚወክላቸው ማህበር በኩል ለሚቀርቡት ጥያቄ ትክክለኛና ወቅታዊ ምላሽ ሊሰጣቸው ይገባል በማለት እምነት እናዳለው አስምሮበታል፡፡

ባንኩ የገበያውን ሁኔታ እያጠና ያለውን የደመወዝ እስኬል በየሦስት ዓመቱ ማስተካከል እንዳለበት በባንኩ ፖሊሲ በግልፅ ቢቀመጥም፣ የባንኩ አስተዳደር ፖሊሲውን መተባበር ባለመቻሉና የተለያዩ በሰራተኛው ላይ የተለያዩ ችግሮች በማድረሱ፣ ብዙ ..ባንኩ ብዙ ወጪ በማውጣት ያስተማራቸውና ያሰለጠናቸው ሰራተኞች ያለማቋረጥ በመልቀቅ ላይ መሆናቸውን ሰራተኞቹ ለሰብሳቢው የተፃፈውን ደብዳቤ በመጥቀስ አብራርተዋል፡፡

..ከሁሉም በላይ የሰራተኞች ቅሬታ እንዲባባስ፣ መብታቸውንና ጥቅማቸውን እንዲያጡ ማድረግ የመንግሥት አላማና ፍላጎት እንዳልሆነ በእርግጠኝነት እናውቃለን.. ያሉት ሰራተኞች በዋጋ ንረቱ ምክንያት መንግሥት ያደረገውን የደመወዝ ማስተካከያ መከልከል አላአግባብና አዲስ ፈላጊ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ማህበሩ ለሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢው ለአቶ ንዋይ ክርስቶስ ገብረአብ በላከው ደብዳቤ ያቀረብነው ጥያቄ አግባብነት ያለውና በመንግሥት የተፈቀደ መብት መሆኑ እንደሌሎች የመንግሥት ተቋማት ሁሉ የኛንም መብት እንዲያስከብሩልን.. በማለት ማስተላለፉን ሰራተኞቹ ተናግረዋል፡፡

የብሄራዊ ባንክ ሰራተኞች ማህበር ሊቀመንበር አቶ አቤንኤዘር  ወንጌልን ያለውን ሁኔታ እንዲያብራሩልን ብንጠይቃቸውም ..በዚህ ሰዓትና ጊዜ ምንም መናገር አልፈለግም.. በማለት ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

የባንኩን ገዢዎች፣ ዳይሬክተሮችና መምሪያዎችን አግኝተን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ ..ስብሰባ ላይ ናቸው.. በሚል ሳይሳካልን ቀርቷል፡፡

በታምሩ ጽጌ

 
< Prev   Next >