Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow ቲማቲም የቆዳን ጤንነት ለመጠበቅ
ቲማቲም የቆዳን ጤንነት ለመጠበቅ Print E-mail
Wednesday, 30 April 2008
ከቲማቲም የተዘጋጁ ምግቦችን በየቀኑ መመገብ ለቆዳ ጤንነት ጥሩ እንደሆነ አዲስ በተካሄደ ጥናት ተረጋገጠ፡፡ ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት ፒዛ እና ስፓጌቲም ቆዳ በፀሃይ እንዳይቃጠልና በእርጅና ምክንያት የሚከሰትን የቆዳ መሸብሸብ ለመከላከል ያስችላሉ፡፡

በየቀኑ አምስት የሾርባ ማንኪያ ቲማቲም ምግባቸው ጋር እየቀላቀሉ በሚጠቀሙ 1ዐ ያህል በጎፈቃደኛ ሰዎች ላይ የተደረገው አዲሱ ጥናት ቲማቲም ለጤና አደገኛ የሆነውን የአልትራ ቫዮሌት የፀሃይ ጨረር የመከላከል ብቃቱ እንዲጨምር አድርጓል፡፡

በተጠቀሰው የፀሃይ ጨረር መቃጠል ያለ እድሜ የቆዳ መሸብሸብንና የቆዳ ካንሰርንም ሊያስከትል ይችላል፡፡

ከዚህ በፊት የተደረገ አንድ ጥናት ቲማቲም በወንዶች ላይ የሚከሰተውን የኘሮስቴት ካንሰር መቀነስ እንደሚችል የሚያረጋግጥ ነበር፡፡ አሁን በማንችስተርና ኒውካስትል ዩኒቨርሲቲዎች የተካሄደው አዲሱ ጥናት ደግሞ አደገኛውን የአልራ ቫዮሌት ጨረር እንዲቋቋም ቆዳን በመርዳት የቆዳን ጤንነት መጠበቅ እንደሚችል የሚያሳይ ነው፡፡

ተመራማሪዎቹ ለቆዳ ጤንነት የሚጠቅሙ ምግቦች ብለው ከገመቷቸው መካከል በወይራ ዘይት ላይም ጥናት አድርገዋል፡፡ 2ዐ ያህል በጎ ፈቃደኞችን እንደ ናሙና በመውሰድ 1ዐ የሚሆኑት 55 ግራም የበሰለ ቲማቲም እንዲወስዱ ተደረገ፤ ቀሪዎቹ ደግሞ 1ዐ ግራም የወይራ ዘይት በየቀኑ ወስደዋል፡፡ ከሦስት ወር በኋላ ከሁለቱም ቡድን የቆዳ ናሙና ተወስዶ በተረገላቸው ምርመራ ቲማቲም ተመጋቢዎች 33 በመቶ በፀሃይ የመቃጠል አደጋን የቀነስላቸው ሲሆን የወይራ ዘይቱም ለቆዳ ጤንነት አስተዋፅኦ እንዳለው ታውቋል፡፡ ተመራማሪዎቹ "ቲማቲም መመገብ ከፀሃይ መከላከያ ክሬም ትንሽ ባነሰ መልኩ ቆዳን ከፀሃይ ጉዳት የሚከላከል ቢሆንም ጨርሶ የፀሃይ መከላከያ ክሬምን መጠቀም ማቆም አያስፈልግም፡፡ ቲማቲምን እንደ አጋዥ መጠቀም ተገቢ ነው" ሲሉ አሳስበዋል፡፡

ማይክሮሶፍት አዲስ ድረ ገፅ ከፈተ

ማይክሮ ሶፍት የተሰኘው ተቋም ላይቭ ሜሽ (Live mesh) የተሰኘ አዲስ ድረ ገፅ መክፈቱን አስታወቀ፡፡ ድረ ገፁ ዲዛይን የተደረገው ኦንላይን ላይ ያሉ የካምፓኒው ኘሮግራሞችን ለማገናኘት መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

እንደ ዘገባው ከሆነ አዲሱ ድረ ገፅ መከፈቱ ማይክሮሶፍትን እንደ አማዞን፣ ጉግልና ሲልስ ፎርስ ዶት ኮም የተሰኙ የተለያዩ የሶፍትዌር አገልግሎቶችን ከሚሰጡ ካምፓኒዎች ጋር ተወዳዳሪ እንዲሆን አድርጎታል፡፡

"ላይቭ ሜሽ"ን ዲዛይን ያደረገው ሚስተር ማታል የተባለ ግለሰብ እንዳለው "ድረ ገፁ በአዲሱ ድረ ገፅ የተለያዩ ፒሲዎችን ጨምሮ፣ ላኘቶኘ፣ ስልክ፣ ዲጅታል የስዕል ፍሬሞችንና፣ ሚዲያ፣ ጌም፣ ሙዚቃ ማጫዎቻና ሌሎችንም እንዴት መጠቀም እንደሚቻል የሚያሳይ ነው"

ማይክሮሶፍት ከሌሎች ካምፓኒዎች ጋር ተወዳዳሪነቱን ማጠናከሩ ያሁን (Yahoo) ለመግዛት እያደረገ ያለውን ጥረት ያግዘዋል የሚል ግምት አለ፡፡ የኤ ኤም አር ጥናት ማዕከል ኘሬዚዳንት ጆናታን ያርሚስ ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንደገለፁት "ማይክሮ ሶፍት አዲሱን ድረ ገፅ መክፈቱ ካምፓኒው እያደረገ ያለውን የእድገት እርምጃ የሚያሳይ ነው"

እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከሆነ ከዚህ ቀደም ማይክሮሶፍት በኦን ላይን ላይ ብቻ ያተኮረ ጥረት አያደርግም፤ እንዲሁም የዊንዶውን ጥቅም ከድረ ገፅ ጥቅም ጋር ለማስተሳሰር ይሞክራል የሚሉ ትችቶች ይደርሱበት ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት ግን ላይቭ ሜሽ የተሰኘውን አዲስ ድረ ገፅ በመጠቀም ደንበኞቹ እንደ ፒሲ፣ ላኘቶኘ፣ ሚዲያ ዲቫይስ፣ ቴሌፎን፣ ዲጅታል ፒክቸር ፍሬም ያሉትን የተለያዩ መሳሪያዎችን መጠቀም እንዲችሉ አድርጓል፡፡

የአየር ለውጡ በድሃ ህፃናት ላይ በትሩ ይበረታል

የአየር ሁኔታ ለውጡ (የዓለም ሙቀት መጨመር) በተለይ በታዳጊ ሃገራት በሚገኙ ድሃ ህፃናት ላይ በትሩ እንደሚበረታ የተባበሩት መንግሥታት የህፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) አስታወቀ፡፡

ድርጅቱ እንደሚለው ከሆነ በአየር ሁኔታ ለውጡ ምክንያት የሚከሰቱ የጎርፍ አደጋዎች፣ ርሃብና በተለያዩ ነፍሳት ምክንያት የሚተላለፉ በሽታዎች ጤናን፣ ትምህርትና አጠቃላይ ደህንነትን ይጎዳሉ፡፡ ሃብታሞቹ እነዚህ ጉዳቶች የልጆች ህይወት ላይ ተፅእኖ እንዳያደርሱ ሁኔታዎችን ማመቻቸት የሚችሉ ሲሆን ድሃዎቹ ግን ይሄንን ለማድረግ የሚያስችል ሃብት የላቸውም፡፡ በመሆኑም በትሩ በድሃ ህፃናት ላይ የበረታ እንደሆነ አስታውቋል፡፡

በህፃናት ላይ የሚከተለውን ችግር ግምት ውስጥ በማስገባት የምዕራባውያን መንግሥታት የካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀት መጠናቸውን በመቀነስና ድሃ ሃገራትን ለመርዳትም በገንዘብ መደጎም እንደሚጠበቅባቸው ድርጅቱ አሳስቧል፡፡

"ለዓለም ሙቀት መጨመር የመጨረሻውንና በጣም ትንሹን አስተዋኅኦ የሚያደርጉት የዓለም ድሃ ህፃናት በለውጡ ምክንያት ግን በግንባር ቀደምትነት ይጎዳሉ" ያሉት የዩኒሴፍ ዩኬ ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቡል ዓለም ከአሁኑ ስለዓለም የአየር ለውጥ ያለውን እውነት ተቀብሎ ሊደርሱ የሚችሉ ችግሮችን ለመቀነስ ካልተንቀሳቀሰ በ2015 የሚሊኒየሙን ግብ ለማሳካት እጅግ ፈታኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በምዕተ ዓመቱ ይሳካሉ ተብለው የተቀመጡትን ስምንት ግቦች በተለይ ከሰሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ ሃገራት ሊያጧቸው እንደሚችሉ ታውቋል፡፡ ቀደም ብሎ የአየር ሁኔታ ለውጡ ግቦቹን ለማሳካት አስቸጋሪ ሁኔታን መፍጠሩ ሲገለፅ ነበር፡፡

የካርቦን ዳይኦክሳይድ ይዘት እየተስተካከለ ነው

ከዓመታት በፊት የነበረ የተቃጠለ አየር ክምችት በመሬት ተፈጥሮአዊ ዑደት የተነሳ እየተስተካከለ ቢሆንም በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ ያለው የተቃጠለ አየር ዑደቱ ቀጣይነት እንዳይኖረው አድርጓል ሲሉ ሳይንቲስቶች አስታወቁ፡፡

በእሳተ ጐመራዎች የሚፈጠረው የተቃጠለ አየር ከአለቶች ወደ ውቅያኖስ ወለል በመግባት ይወገዳል፡፡

በአንታርቲክ የበረዶ ክምችት በተደረገ ጥናት የምርምር ቡድኑ ከ610"000 ዓመታት በላይ የታየው የረጅም ጊዜ የተቃጠለ አየር ለውጥ ከጠቅላላው ከባቢ አየር በሚሊዮን ሲሰላ ድርሻው 22 በመቶ ያህል ቢሆንም የበረዶው የመቅለጥ ሂደት ረጅም ጊዜ ይወስዳል ብለዋል፡፡

ዑደቱ አረንጓዴ ዕፅዋት ከሚያስገኙት ያነሰ ውጤት እንዳለው የሃዋይ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ ሪቻርድ ዜቢ ተናግረዋል፡፡

"በተፈጥሮአዊ ዑደቱ ይህ ምላሽ ባይገኝ ኖሮ ምድራችን አሁን ያላትን ገፅታ አታገኝም ነበር" ብለዋል ተመራማሪዎቹ፡፡
 
< Prev   Next >