| በዐዲግራት ከተማ የጎደና ተዳዳሪ ወጣቶችን... |
|
|
| Wednesday, 30 April 2008 | |
|
በዐዲግራት ከተማ የጎደና ተዳዳሪ ወጣቶችን መልሶ ማቋቋም ጥረት እየተደረገ ነው
በዓዲግራት ከተማ የሚገኙ ወላጅ አልባ የጎደና ተዳዳሪ ወጣቶችን መልሶ ለማቋቋም የተለያዩ ሙያዊ ስልጠና መስጠት መጀመሩን የከተማው ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ፅህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ የፅህፈት ቤት ኃላፊ መምህርት ንግሥቲ ገብረመስቀል እንደገለፁት በከተማው ከ1 ሺ 5ዐዐ በላይ ወላጅ አልባ ጎዳና ተዳዳሪ ወጣቶች መኖራቸው በጥናት ተረጋግጧል፡፡ ወጣቶቹን በተለያዩ የሥራ መስኮች ለማሰማራት ጥረት ተጀምሯል ያሉት ኃላፊዋ ፅህፈት ቤቱ ከግሎባል ፈንድ ባገኘው 50 ሺ ብር ድጋፍ ከአዲግራት ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በመተባበር 3ዐ ችግረኛ ወጣቶች ለስድስት ወር የሚቆይ የብረታ ብረት ሙያ ሥልጠና እየተሰጣቸው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ወጣቶቹ ሙያዊ ሥልጠናውን እንዳጠናቀቁ በማህበር ተደራጅተው በብረታ ብረት ሥራ ለማሰማራት የብድርና ሌሎች ድጋፎች እንደሚደረግላቸው ገልፀው መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ባለሃብቶች የጎዳና ተዳዳሪ ህፃናትና ወጣቶችን ለማቋቋም የተጀመረው ጥረት ማገዝ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡ የኮሌጁ ምክትል ዲን መምህር ዮናስ ዓለም በበኩላቸው ወጣቶቹ ለሥራ ፈጠራ መነሻ የሚኖቸውን በቂ ክህሎት እንዲያኙ የሚያስችል ሥልጠና እየተሰጣቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ከሰልጣኝ ወጣቶቹ መካከል ወጣት በሽር ከድርና ሄለን ገብረመስቀል በሰጡት አስተያየት የከተማው አስተዳደር ከወደቁበት አንስቶ እያደረገላቸው ያለውን ድጋፍ ማድነቃቸውን የዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘገባ ያመለክታል፡፡ በእንስሳት ላይ የዋጋ ጭማሪ ሲከሰት በምግብ እህሎች ላይ መረጋጋት እየታየ ነው በባህር ዳር ከተማ ከፋሲካ በዓል ጋር ተያይዞ በእንስሳትና እንስሳት ተዋፅኦ ላይ የዋጋ ጭማሪ መከሰቱንና በአንዳንድ አትክልትና ፍራፍሬዎችና የምግብ እህሎች ላይ ደግሞ የገበያ መረጋጋት መታየቱን ነጋዴዎችና ሸማቾች ገለፁ፡፡ ሸማቾች እንደገለፁት አምና በፋሲካ በዓል አካባቢ 35 ብር ይሸጥ የነበረ አንድ ኪሎ ንፁህ ቅቤ ዘንድሮ 6ዐ ብር፣ በሊትር 1 ብር ከ5ዐ ሳንቲም የነበረው የላም ወተት 3 ብር እየተሸጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ እንዲሁም የተቀለበ በሬ በአማካይ አምስት ሺ ብር፣ መካከለኛው ሦስት ሺ ብር፣ ወይፈን እስከ 2 ሺ 5ዐዐ ብር፣ መሲና ደግሞ እስከ ሁለት ሺ ብር እየተሸጡ ሲሆን ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከ5ዐዐ እስከ 1 ሺ 5ዐዐ ብር የዋጋ ጭማሪ መታየቱን፣ አምና 650 ብር ይሸጥ የነበረ የበግና የፍየል ሙክት ዘንድሮ እስከ 850 ብር፣ መካከለኛው እስከ 400 ብር፣ ወጠጤ እስከ 250 ብር ድረስ እየተሸጡ መዐናቸውን እንዲሁም 25 ብር ይሸጥ የነበረ አንድ ትልቅ ሴት ዶሮዎች እስከ 30 ብር መሸጣቸውን ተናግረዋል፡፡ (ኢዜአ) በአሜሪካ ሂውስተን ሙዩዚየም የሚገኘውን የሉሲ ቅሪተ አካል ከ17ዐ ሺህ በላይ ህዝብ ጎበኘው በአሜሪካ ሂውስተን የተፈጥሮ ሳይንስ ሙዩዚየም ውስጥ በተዘጋጀ ኤግዚቢሽን የቀረበውን የሉሲ ቅሪተ አካል እስከ አሁን ከ17ዐ ሺህ በላይ ህዝብ እንደጎበኘው የሙዚየም ባለሥልጣናት አስታወቁ፡፡ የሉሲ ቅሪተ አካል በሙዚየሙ የሚጎበኝበት ጊዜም እንዲራዘም መወሰኑን ሙዚየሙ አመልክቷል፡፡ በሂውስተን ሙዚየም ክፍት የሆነው ኤግዚቢሽኑ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በዚህ ወር መዘጋት የነበረበት ቢሆንም በህዝብ ጥያቄ መሰረት እንደ አውሮፓ አቆጣጠር እስከ መጪው መስከረም 1 ቀን ድረስ እንዲራዘም መወሰኑን ባለሥልጣናቱ አስታውቀዋል፡፡ በኢትዮጵያ አፋር ክልል ውስጥ የተገኘው እና 3 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዓመት እድሜ እንዳለው የሚነገርለት በዓለም እጅግ ቀደምቱ የሉሲ ቅሪተ አካል የሂውስተን ኤግዚቢሽን እንደተጠናቀቀ በአሜሪካ ሰያትል ወደ ሚገኘው የፓስፊክ ሳይንስ ማዕከል ይንቀሳቀሳል፡፡ (አዲስ ዘመን ሚያዚያ 19 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም.) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |