Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow የአቅም ግንባታ ፖለቲካ
የአቅም ግንባታ ፖለቲካ Print E-mail
Wednesday, 30 April 2008
በሰለሞን ከድር

ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በየጊዜው የሚቀርቡትን ሪፖርቶች አልፎ አልፎ እያገኘሁ እመለከታለሁ፡፡ በያዝነው የሚያዚያ 2000 ወር የመጀመሪያው አጋማሽ ውስጥ የአቅም ግንባታ ሚኒስቴር ለምክር ቤቱ ያቀረበው የአቅም ግንባታ ኘሮግራሞች (የዘጠኝ ወር አፈፃፀም) ሪፖርትም ከነዚህ ሪፖርቶች አንዱ ነው፡፡ ይህንን ሪፖርት አልፎ አልፎ እያገኘሁ ከምመለከታቸው ሪፖርቶች ለየት የሚያደርገው (ከእኔ አንፃር ማለቴ ነው) የአቅም ግንባታ ሚኒስቴርን የ1999 (ሚያዚያ 1999) የዘጠኝ ወር እቅድ አፈፃፀምና የ2ዐዐዐ ዓ.ም. እቅድ አቅጣጫ ሪፖርትም አግኝቶ የመመልከት እድል ያጋጠመኝ መሆኑ ነው፡፡

ሪፖርቶቹ የሲቪል ሰርቪስ የፍትህ ሥርዓት ማሻሻያ ኘሮግራሞችን፣ የገጠር ወረዳ የአስተዳደርና የአቅም ግንባታ የምህንድስና አቅም ግንባታ እና እንዲሁም የኢንፎርሜሽን ኮሙውኒኬሽን ቴክኖሎጂ ኘሮግራሞችን የሚመለከቱ ናቸው፡፡ በእያንዳንዱ ሪፖርት ላይ እያነፃፀሩ ዝርዝር ጉዳዮችን መመርመርና ልዩ ልዩ ጥያቄዎችን ማንሳት ይቻላል፡፡ በዚህ ፅሁፍና በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ አቅሜ ከፈቀደልኝ የምመለከተው በሁለቱም የ1999 ዓ.ም. እና በ2ዐዐዐ ሪፖርቶች የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ኘሮግራምን በሚመለከት ረገድ ብቻ የተነሱትን ጉዳዮች መሰረት በማድረግ ነው፡፡

ያለፈው ዓመት (የሚያዚያ 1999 ዓ.ም". ሪፖርት "የተሟላ ረየሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ኘሮግራሞት ትግበራሪ (ተቋማዊ ለውጥ) በፌዴራልና ክልል ተግባራዊ ማድረግን"ን በተመለከተ በፌዴራል በዋና ዋና ተቋማት መሰረታዊ ለውጥ (BPR) ተጠናቅቆ ውጤት ተኮር ሥርዓት ተመስርቷል የሚለው ግባትን በየተቋሙ በተለያየ ደረጃ የሚገኝ ቢሆንም ለውጥ አምጥቶ ውጤት ተኮር ሥርዓት ከመመስረት ግባችን አንፃር አልተሳካም ይላል፡፡ መንስዔ ያለውንም ሪፖርቱ በሦስት ከፍሎ ያሳያል፡፡ ከእነዚህ ሦስት ምክንያቶች መካከል አንደ ሪፖርቱ 1ኛ መሰረታዊ ለውጥ የማምጣት ሥራ ላይ የታየው ስህተትና ብዥታ ሳይፈታ የተወሰነ ጊዜ የቆየበት ሁኔታ ተፈጥሮ የሚያስፈልገውንና የሚጣለው አሮጌ ሥርዓት በዝርዝር ወደ ማጥናት በመግባቱ፤ 2ኛ የለውጥ ቀያሹ ኃይል በለውጡ ላይ የወገነ ኃይል መሆኑን አመራሩ ማረጋገጥ ሲገባው የኃላፊነት ቦታ ላይ ያሉ ሁሉ የለውጡን ሥራ መሥራት እንዳለባቸው ወስዶ የመሄድ መሳሳት በመኖሩ የሚሉት ሁለቱ ናቸው፡፡

ክልሎችን (አዲስ አበባን እና ድሬዳዋን ጨምሮ) በተመለከተ የ1999 ዓመቱ ሪፖርት የሚከተሉትን ዝርዝር ነጥቦችን ያወሳል፡፡ በአዲስ አበባ ተጀምሮ የነበረው የለውጥ ሥራ ከምርጫው በኋላ መቀልበሱን ይህን እንደ አዲስ ለማስጀመር ለዓመታት የሚቆይና ባለቤት የሚሆን አመራር በሌለበት መሰረታዊ የለውጥ ሥራ መጀመር ለይስሙላ ካልሆነ በስተቀር መጀመር ስለማይቻል አለመጀመሩን "በመሆኑም ዕቅዳችን ራሱ ለአዲስ አበባ የተሳሳተ እቅድ እንደሆነ መገንዘብ" መቻሉን ይገልፃል፡፡

ይህ የ1999 ዓ.ም. ሪፖርት "አቅሙ ላላቸው አራቱ ክልሎች" በሚላቸው ውስጥ (ኦሮሚያ አማራ፣ ትግራይና ደቡብ) በክልልና በዞን ዋና ዋና ተቋማት የመሰረታዊ ለውጥ ትግበራ ተጠናቅቆ ውጤት ተኮር ስርዓት ተመስርቷል የሚለው ግባችን አልተሳካም" ይላል፡፡

የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ኘሮግራሙ በእነዚህ ክልሎች በ1998 ዓ.ም. ጭራኀሽ ከቆመበት እንደገና ማንሳትና ማስጀመር ቢቻልም ግቡ" አለመሳካቱን ሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡ ምክንያቱንም ሲገልፅ "የግባችን አለመሳካትና ይህን ያህል ረጅም ጊዜ መጓተት ዋና መንስኤው የበላይ አመራሩ በመሰረታዊ ለውጥ ሥራ ላይ ያሳየው የአመለካከት ቁርጠኝነት መጓደል" መሆኑን ያስረዳል፡፡ በመሰረታዊ ለውጥ ሥራ ላይ የታየው ብዥታም ጉዳዩን እንዳባባሰው ይገልፃል፡፡

በተለይም ክልሎች (ሪፖርቱ በቀረበበት በሚያዚያ 1999 ዓ.ም". በጥቅሉ   የሚገኙበትን ደረጃ ሲያሳይ

•    ኦሮሚያ ከዓመቱ አጋማሽ ጀምሮ ወደ ለውጥ ጥናት ገብቶ ይገኛል
•    አማራ የበላይ አመራር ስልጠና በጥር ጨርሶ በተመረጡ ተቋማት ስልጠና መስጠት ለመጀመርና እንደ አዲስ ለማስጀመር በዝግጅት ላይ ነው
•    ትግራይ የበላይ አመራር ስልጠና በመጋቢት ጨርሷል፡፡ ሥራውን በተቋማት ለማስጀመር በዝግጅት ላይ እንደሆነ ነው
•    ደቡብ የበላይ አመራር ስልጠና ገና ስላልወሰደ መቼ እንደ አዲስ እንደሚጀምር ገና አልተመለሰም የሚለው ሪፖርት "ለበላይ አመራሩ እንደ አዲስ ስልጠና የሚሰጠው ይህን ሰበብ የሚሆን ብዥታ አስወግዶ የአመራር የቁርጠኘነት ጥያቄ ግልፅ ሆኖ እንዲወጣ ለማድረግ" እንደሆነ ያስረዳል፡፡

የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ኘሮግራም የ1999 ዓ.ም. አፈፃፀምን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረበው ሪፖርት ያጠቃለለው "ግቦችን እንዳቀድነው አላሳካንም" ብሎ ነው፡፡ መንስዔውም ይላል፣ የማጠቃለያው ሪፖርት፣ "መንስዔውም ኘሮግራሞችን ተግባራዊ ከማድረግ ውጭ የኪራይ ሰብሳቢነት ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ ወጥመዶችን መስበር እንደማይቻል የበላይ አመራር እርከኖች አለመገንዘባቸውና ከዚህም ተነስቶ ለለውጡ ቁርጠኛ አቋም ይዞ ለውጡን ለመስራት የሚያስፈልገውን እውቀት የራሱ አድርጐ አለመገኘቱ ነው" ግቦቹ ባይሳኩም ሪፖርቱ የ1999 ዓ.ም. ስኬቶች ያላቸውንም ገልጿል፡፡
ከእነዚህም መካከል አንድ የተዛቡ አመለካከቶችና ብዥታዎች በግልጽ ወጥተው በመታየታቸው ከእንግዲህ እነሱን ለመታገልና ለማረም ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ ሁለት የለውጥ ሥራ የመሰረት እውቀት በተሻለ እየተያዘ በተግባርም እየተፈተነ መሆኑ ናቸው፡፡ እዚያው የ1999ቱ የአቅም ግንባታ ሚኒስቴር ሪፖርት ውስጥ ነገር ግን ከሲቪል ሰርቪሱ ማሻሻያ ኘሮግራሙ ርዕስ አንድ ሳናነሳው የማይታለፍ አብይ ጉዳይ አለ፡፡ "በመልካም አስተዳደር የ2ዐዐዐ ዓ.ም. እቅዶችን ግብ መሆን ያለበት በሁሉም ኘሮግራሞች የምንሰራው ድምር ውጤት በመልካም አስተዳደር እመርታ ለማምጣት የምንሸጋገርበት ዓመት መሆን አለበት" የሚለው ደጋግሞ ስለሁሉም ኘሮግራሞች የሚናገረው የሪፖርቱ አካል

•    "ለዚህ ግብ መሳካት የመንግሥት መዋቅሩ ብቻ ሳይሆን የገዢው ፓርቲ መዋቅር ጭምር የሚሰራበት የክልል የበላይ አመራር ከበታች አመራር ጋር የክልል ከፌዴራል ጋር ወር ባልበለጠ መደበኛ ጊዜ እድገቱን መከታተልና በአብዮታዊ ባህሪይ አብዮታዊ እንቅስቃሴ መለኮስ የሚጠይቅ ነው፡፡ በልዩ ልዩ የለውጥ ኘሮግራሞች ላይ እስካሁን በመጣው መልኩ እያዘገመና ሞቅ ቀዝቀዝ እያለ ይህ የመሸጋገሪያ ግብ ሊሳካ አይችልም ብቻ ሳይሆን ሊቀለበስ ይችላል፡፡ ሁሉም የለውጥ ኘሮግራሞች አፈፃፀም በዚህ ማዕቀፍ እየታየ የሚፈፅም እቅድ" ነው ይላል፡፡

የአቅም ግንባታ ሚኒስቴር የ2ዐዐዐ ዓ.ም. የአቅም ግንባታ ኘሮግራሞች የዘጠኝ ወር አፈፃፀም ሪፖርት ደግሞ በተለይም በሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ኘሮግራሙ የሪፖርቱ ዋና ክፍል ውስጥ በየቦታው ደጋግሞ የሚያነሳው አሳሳቢ ችግር "በፖለቲካ አመራሩ አካሄድ"ን የሚመለከተው ነው፡፡

የፌዴራል ደረጃ ያለውን ስኬት ባመዛኙ የሚገልፀው ደህ ሪፖርት ፈተናዎች ያለበት መሆኑን ሳይደብቅ እነዚህ ደግሞ

1.    ለውጥ ቴክኒካዊና ተራ የአሰራር ለውጥ ሳይሆን መሰረታዊና ፖለቲካዊ መሆኑን በሚገባ አለመገንዘብና ከዚህም በሚመነጭ ለውጡን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ከሚደረጉ ዝንባሌዎች ጋር መደራደር የሚታይባቸው ሁኔታዎች በአንዳንድ ተቋማት መታየቱ፤
2.    ለውጡን የማስቀጠል ሚና ከሚጫወቱ የትምህርት የምርምር የስልጠናና የማማከር ስራ የሚሰሩ ተቋማት ወደ ለውጡ ኘሮግራም ሳይገቡ ወደ ኋላ መቅረት ዋነኞቹ ፈተናዎች መሆናቸው ቀጣዩ ጉዞም እነዚህን ፈተናዎች መሻገርን ግድ የሚል መሆኑን ናቸው፡፡

ክልሎችን በተመለከተ "የተሻለ አቅም ባላቸው ክልሎች በተለያየ ደረጃ አፈፃፀም ላይ የሚገኙ መሆናቸውን የሚገልፀው ሪፖርት "የጊዜ ልዩነት ካልሆነና እስከ አሁን የሚታየው የፖለቲካው አመራር ጠንካራ ግፊት ካልተለወጠ በስተቀር ለወጥ ማምጣት የሚችሉበት አፈፃፀም ላይ እንደሆኑ"" ይናገራል፡፡ የእያንዳንዱን የእነዚህን "የተሻለ አቅም" ያላቸው ክልሎች በሚመለከትም

•    ስለ ኦሮሚያ "አሁን ያለው የፖለቲካዊ አመራር ጠንካራ ግፊት ከላላ ረካልላላሪ ወይም ካልተዛባ በስተቀር የኦሮሚያ ክልል በዚህ ዓመት ሰፋ ባሉ ተቋማቱ ለውጥ ማምጣት በሚችልበት አካሄድ ላይ ነው ማለት" እንደሚቻል ይናገራል፡፡
•    ስለ አማራ "በዚህም የፖለቲካ አመራሩ አካሄድ ላይ ለውጥ ካልመጣ ረአፈፃፀሙንሪ እንደሚያሳካው አያጠራጥርም" ይላል፡፡
•    ስለደቡብ "እዚህም የስኬቱ ቅድመ ሁኔታ የፖለቲካ አመራሩ ጠብቆ መቀጠል መቻሉና ከቀደሙት ክልሎች የሚገኘውን ልምድ በማካተት ማፋጠን መቻሉ ነው" በማለት የደቡብ ተቋማት ጥናቱን በማጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን በሰኔ ወር የሙከራ ትግበራውን እንደሚጀምር ነገር ግን የተባለው ቅድመ ሁኔታ ማስፈለጉን ይገልፃል፡፡
•    ስለ ትግራይ ደግሞ "እነዚህ በዋነኛነት በጥናት ላይ የሚገኙ ሲሆን ትግራይ ከቀደሙት ልምድ ወስዶ በስራውና በጠንካራ ግፊት በመስራት ላይ ስለሆነ ካሁን እስከ ሰኔ ባለው ጊዜ ውስጥ ቢያንስ የሙከራ ትግበራ መጀመር እንደሚችል የሚጠበቅ አፈፃፀም ላይ የሚገኝ" መሆኑን
•    "የሐረሪና ድሬዳዋ የፖለቲካ አመራሩ ያዝለቀቀ ያለበት፣ አካሄድ ስለሚታይ ይህ አካሄድ ካልተለወጠ በስተቀር መሰረታዊ ለውጡን ማምጣት ይችላል ብለን ለመናገር አያስደፍርም" ይላል፡፡

ሪፖርቱ ባጠቃላይ ሲናገር "በአገር አቀፍ ደረጃ አጠቃለን ስንመለከተው በፌዴራልም ሆነ በክልል መሰረታዊ ለውጥ መስመር ውስጥ መግባት የምንችልበት አመት መሆኑን የእስካሁኑ እድገት" እንደሚያሳይ "ይህ እድገት ሊቀለበስ የሚችለው የፖለቲካ አመራሩ ቁርጠኝነት ከላላና ለፀረ ለውጥ ዝንባሌ የተንበረከከ ከሆነ ብቻ ነው" ሲል ይደመድማል፡፡

የሌሎችን የታዳጊ ክልሎች በሚመለከት በዚህ ረገድ የመንግሥት /የሚኒስቴሩ እቅድ የለውጥ ሥራውን የሚመራው ፖለቲካዊ አመራርን የሚደግፍ የለውጥ ሥራ ሊሰራ የሚችል ምርጥ ኃይል በአመቱ መጀመሪያ ሰጥተው/ አቅርበው በፌዴራል በማሰልጠንና በፌዴራል በሚሰራው ውስጥ በብቃት በማለማመድ ራሱን ችሎ መስራቱን በማረጋገጥ በዓመቱ መጨረሻ ወደ የክልሎች በመመለስና በየራሳቸው ተጨባጭ ሁኔታ እንዲጀምሩ ማድረግ የነበረ መሆኑን ሪፖርቱ ገልፆ፣ በዚህ እቅድ መሰረት የተንቀሳቀሰው የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ብቻ መሆኑን አፋርና ጋምቤላ ግን በቀረው ጊዜ ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ በመዘጋጀት ላይ መሆናቸውን ርዕሰ መስተዳድሮቹ ካሳወቁት የተሻገረ የአፈፃፀም ሪፖርት የሌለ መሆኑን ያስረዳል፡፡

የአቅም ግንባታ ባጠቃላይ በተለይም የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ኘሮግራሞች የ1999 ዓ.ም. እና የ2ዐዐዐ ዓ.ም. የሁለት ዓመት ተከታታይ ሪፖርቶች የሚሉትን ከዚህ በላይ የተመለከተው ነው፡፡ የመንግሥት ብቻ ሳይሆን በገዢው ፓርቲ መዋቅር ጭምር መሰራት ያለበት መሆኑን ሥራው "በአብዮታዊ ባህሪይ አብዮታዊ እንቅስቃሴ መለኮስ የሚቀይቅ" እንደሆነ እስከ አሁን የተመዘገበው እድገትም ቢሆን "የፖለቲካ አመራሩ ቁርጠኝነት ከላላና ለፀረ-ለውጥ ዝንባሌ ከተንበረከከ ሊቀለበስ እንደሚችልና ይህን የመስለ ብርቱ ስጋት እንዳለ ተመልክተናል፡፡ ጥያቄው በዚህ ሪፖርት ውስጥ የሚነበበው አንደምታ ምንድነው የሚለው ነው፡፡ ማሻሻያ የሚያስፈልገው የአገሪቷ ሲቪል ሰርቪስ እንደ መከላከያ ሠራዊቱ እንደ የዳኝነት አካሉ ከዚህ በኋላ የትኛውም ፓርቲ ፖሊሲውን የሚያስፈፅምበት እንጂ አፍርሶ እንደገና የሚሰራው ካልሆነ በስተቀር በገዥው ፓርቲ አምሳል የሚቀረፅ፣ ሌላ አዲስ መንግሥት ሥልጣን በያዘ ቁጥር ያንኑ የመንግሥት ሥልጣን አፈናጥሮ እንዲጥለው ካልተፈለገ በቀር የማሻሻያው ኘሮግራም ዞሮ ዞሮ ታጥቦ ጭቃ ይሆናል፡፡ በደርግ ቀጥሎም በኢህአዴግ እንዳየነው የነበረውን ማፍረስና መበተን ሁልጊዜም በ"ምርጫ" ማግስት የግድ የማሻሻያ ኘሮግራሙ አካል ይሆናል፡፡

 
< Prev   Next >