Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow ቴሌ በ4.3 ቢሊዮን ብር ወጪ...
ቴሌ በ4.3 ቢሊዮን ብር ወጪ... Print E-mail
Sunday, 04 May 2008
ቴሌ በ4.3 ቢሊዮን ብር ወጪ የሞባይል አገልግሎት ማስፋፊያ ጀመረ

በተሾመ ንቁ

የኢትዮጵያ ቴሌ ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን በአገሪቱ ውስጥ ያለውን የሞባይል አገልግሎት መስመር ወደ 5.6 ሚሊዮን ለማሳደግ እንቅስቃሴ መጀመሩን የኮርፖሬሽኑ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዋና ክፍል ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱራሂም አህመድ ለሪፖርተር ገለፁ፡፡
በአቶ አብዱራሂም ገለፃ መሠረት በአገሪቱ የነበረውን የ1.2 ሚሊዮን የሞባይል መስመር ወደ 5.6 ሚሊዮን የማሳደግ ሥራ ተጀምሯል፡፡ ለማስፋፊያ ፕሮጀክቱ ኮርፖሬሽኑ 4.3 ቢሊዮን ብር ወጪ እንደሚያደርግ ታወቋል፡፡

ሥራ አስኪያጁ ከቻይና ዜድቲኢ ጋር የተጀመረው የማስፋፊያ ፕሮጀክት የሁለተኛ ዙር መሆኑን ገልፀው፤ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ 766 ከተሞችና 22 ዋና ዋና የሀይዌ የሞባይል ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡ በዚህም ከ5 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የሞባይል ተጠቃሚ እንደሚሆን አስረድተዋል፡፡

የፕሮጀክቱ የዲዛይንና የሰርቬይ ሥራ መከናወኑን የገለፁት አቶ አብዱራሂም፤ ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ ሁለት ዓመት እንደሚፈጅ አስታውቀዋል፡፡

ከዚሁ ፕሮጀክት ጎን ለጎን በአዲስ አበባ፣ በጅማ፣ በአዋሳ፣ በመቀሌ፣ በባህርዳርና በሌሎች 13 ከተሞች ያለውን የኔትወርክ መጨናነቅ የማስተካከል ሥራ ቅድሚያ በመስጠት የማስተካከያ ሥራ መጀመሩንና በአራት ወር ውስጥ እንደሚጠናቀቅ አቶ አብዱራሂም ገልፀዋል፡፡
 
< Prev   Next >