| የግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስቴር... |
|
|
| Sunday, 04 May 2008 | |
የግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስቴር የ100 ዓመት ጉዞበታምሩ ጽጌ የግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስቴር አንድ መቶኛ ዓመቱን ሚያዚያ 24 ቀን 2000 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በሴባስቶፓል ሲነማ አዳራሽ አክብሯል፡፡ በዓሉን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስትር አቶ አዲሱ ለገሠ በይፋ መርቀው ከፍተዋል፡፡ ሚኒስትሩ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ መቶኛ ዓመት በዓሉን በማስመልከት ያዘጋጀውን ኤግዚቢሽን መከፈት ይፋ ሲያደርጉ ባደረጉት ንግግር፣ “በዓሉን ልዩ የሚያደርገው የሚሌኒየም በዓል በሚከበርበትና በአገራችን ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢኮኖሚያችን ዘርፍ ከፍተኛ ዕድገት እያስመዘገበ ያለበት ወቅት መሆኑና ዕድገቱን ለማስመዝገብ ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈልንበት የግንቦት 20 በዓል ዋዜማ ላይ መከበሩ ነው” ብለዋል፡፡ ለድህነትና ለኋላ ቀርነት የዳረገንን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ መዋቅር ከሥር መሠረቱ የሚንድ በሕዝቦች ተሳትፎና ትግል የተረጋገጠ ሕገ መንግሥት ባለቤት መሆናችንና በዚሁ ሕገ መንግሥት ተረጋግጠው የወጡ ፖሊሲዎችና መብቶች በመኖራቸው ዛሬ ዕድገትን እያየን መሆኑን ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል፡፡ ሴክተሩ በገበያ የሚመራ ግብርና መር በመሆኑ ዓለምንም የሚያነጋግር የኢኮኖሚ መሠረት መሆኑን፣ በአገራችንም በርካታ አርሶ አደሮች ሕይወታቸውን እየለወጡበት መሆናቸውን አቶ አዲሱ ተናግረዋል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |