Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow የዲያስፖራ ፖሊሲ ለማውጣት ጥናት ተጀመረ
የዲያስፖራ ፖሊሲ ለማውጣት ጥናት ተጀመረ Print E-mail
Sunday, 04 May 2008
በጋዜጣው ሪፖርተር


በውጪ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና በትውልድ ኢትዮጵያዊያንን የኢንቨስትመንት እና የልማት ተሳትፎ ይበልጥ ለማሳደግ በቀጣዩ ዓመት አገራዊ የዲያስፖራ ፖሊሲ ለማውጣት ዝግጅት በመደረግ ላይ መሆኑ ተጠቆመ፡፡
በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያኖች ገዳዮች ዳይሬክቶሬት ተ/ዳይሬክተር አቶ ደመቀ አጥናፉ እንደተናገሩት አገራዊ የዲያስፖራ ፖሊሲ ለማውጣት ያስፈለገው እስካሁን የወጡና በሥራ ላይ ያሉ ፖሊሲዎችን ይበልጥ ምቹ ለማድረግ፣ የውጪ አገር ጠቃሚ ተሞክሮዎችን ለማካተት ታስቦ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት የጥናት ሥራው በመከናወን ላይ እንደሚገኝ ጥናቱም በቀጣዩ በጀት ዓመት ተጠናቆ ረቂቅ ሕጉ ለፓርላማ ይቀርባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡

በ2000 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት በሰባት ቢሊዮን ብር ካፒታል 671 ያህል ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በኢንቨስትመንትና በልማት መሳተፋቸውን፣ ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ሲገቡም ከ62ሺ በላይ ሰዎች የሥራ እድል እንደሚፈጥሩም አቶ ደመቀ ገልፀዋል፡፡

በያዝነው የበጀት ዓመት በአራት ወራት ጊዜ ውስጥ ብቻ ከውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሐዋላ ወደ ኢትዮጵያ የላኩት ገንዘብ 200 ሚሊዮን ዶላር እንደነበር፣ ከዚህ በፊት ብሔራዊ ባንክ የተሻሻለ መመሪያ ከማውጣቱ በፊት በዓመት 400 ሚሊዮን ዶላር ገደማ መላኩን በመግለጽ የአሁኑ የተሻለ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በተያያዘም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ለመጣው የፀጥታ ሁኔታ ጋር በተያያዘ በቤይሩት እና በሶሪያ በሕጋዊ መንገድ ሠራተኞች የመላክ ሥራ መቆሙን አስታውቀዋል፡፡ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር በመተባበር ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ጉዞውን ሊያቋርጥ የተገደደው ኢትዮጵያውያኑ የሚገጥማቸውን ችግሮች በፀጥታ መናጋት ምክንያት ለመፍታት ባለመቻሉ ነው፡፡ እንደ አቶ ደመቀ አባባል ከሆነ ኢትዮጵያውያን ይህን ሁኔታ በመገንዘብ ከሕገወጥ ጉዞዎች ራሳቸውን እንዲያቅቡ፣ ስለሚሄዱበት አገራት ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ወይም ከሠራተኛ ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ተገቢውን መረጃ እንዲጠይቁ መክረዋል፡፡

አቶ ኢሳያስ ጎታ በሚኒስቴሩ የኢኮኖሚ ትብብርና ቢዝነስ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ተ/ዳይሬክተር በኢኮኖሚና በቢዝነስ ጉዳዮች ስለተደረጉ እንቅስቃሴዎች ተጨማሪ መረጃ ለጋዜጠኞች ሰጥተዋል፡፡
 
< Prev   Next >