Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow የአትሌት ጌጤ ዋሚ ተሽከርካሪ...
የአትሌት ጌጤ ዋሚ ተሽከርካሪ... Print E-mail
Sunday, 04 May 2008
የአትሌት ጌጤ ዋሚ ተሽከርካሪ በጉምሩክ ተያዘ

በአዜብ መሐሪ

የጉምሩክ ባለሥልጣን የታርጋ ቁጥር 3-50230 የሆነ ፕራዶ መኪና ከየካቲት 16/2000 ዓ.ም. ጀምሮ እንዲያዝባቸው አትሌት ጌጤ ዋሚና ባለቤቷ አቶ ጌታነህ ተሰማ ቅሬታቸውን ገለፁ፡፡
መኪናዋ ከቀረጥ ነፃ የገባች ብትሆንም ህጋዊ የባለቤትነት ማስረጃዎች በእጃችው መያዛቸውንም ነገር ግን ከሀገር ውጭ በነበሩባቸው ቀናት የቤተሰባቸው አካል የሆነ ሰው ህጋዊ ውክልና ሰጥተው ከሀገር ውጭ በነበሩበት ወቅት ልጆቻችውን ትምህርት ቤት በመውሰድ ላይ እያለ መኪናዋ እንድትታሰር መደረጉን ተናግረዋል፡፡

የጉምሩክ ባለሥልጣን የህዝብና ዓለም አቀፋዊ ግንኙነት አገልግሎት ኃላፊ አቶ ገብረመድህን ገብረዮሃንስን፣ የጉምሩክ ባለሥልጣን ከቀረጥ ነፃ የገቡ የግል ተሽከርካሪዎችን ከባለመብቱ ሌላ የባለ መብቱ ባል ወይም ሚስት እንጂ ወደ ሌላ እጅ ማስተላለፍ እንደማይቻልና ይህ ሆኖ ከተገኘ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ወደ ሚመለከተው የህግ ክፍል እንደሚያስተላልፍ ገልፀዋል፡፡

አያይዘውም የጉምሩክ ባለሥልጣን በውክልና ስም ህጋዊ ዝውውርን (ሽያጭን) ለመከላከል በሚል ከቀረጥ ነፃ ለገቡ የግል መኪናዎች ምንም ዓይነት ውክልና እንደማይቀበል አስታውቀዋል፡፡

የአትሌት ጌጤ ዋሚ ጉዳይ በጉምሩክ የህግ መምሪያ ክፍል እየታየ እንደሆነና ምርመራው ካለቀ በኋላ እንደሚወሰን ኃላፊው አረጋግጠዋል፡፡

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በተመሳሳይ ሁኔታ ተሽከርካሪውን ለሌላ ግለሰብ በውክልና አስተላልፎ በመገኘቱ መኪናዋ በጉምሩክ በቁጥጥር ሥር ከዋለች በኋላ መለቀቋንም ለማወቅ ተችሏል፡፡
 
< Prev   Next >