Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow በክልሎች የዋጋ ግሽበት ተባብሷል
በክልሎች የዋጋ ግሽበት ተባብሷል Print E-mail
Sunday, 04 May 2008
Image
ዶ/ር ኃይሌ ክብረት
በቤዛዊት ሥዩም

በምግብ ምርቶች ላይ ያለው አጠቃላይ ብሄራዊ የዋጋ ግሽበት 29 በመቶ ሲሆን በክልሎች የዋጋ ግሽበት ተባብሶ መቀጠሉ ተገለፀ፡፡

የዋጋ ግሽበትን አስመልክቶ በተካሄደ መድረክ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር የማክሮ ኢኮኖሚ ክፍል ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ኃይሌ ክብረት እንደተናገሩት የዋጋ ግሽበት የተባባሰ ሲሆን የዋጋ ንረቱ በቤንሻንጉል ጉምዝ 54.3 በመቶ፣ በኦሮሚያ 43 በመቶ፣ በደቡብ ክልል 42.9 በመቶና በትግራይ 47 በመቶ መድረሱን ገልፀዋል፡፡

የነዳጅና የምግብ እህሎች ዋጋ መጨመር፣ የሚሰጠው የምግብ እርዳታ መቀነስና ማቆም፣ በምግብ እህል ራሳችንን ባለመቻላችን፣ ወደ አገር ውስጥ በግዢ የሚገባ ምርት በአንዳንድ አገሮች በመቆሙና ለባዮፊውል አገልግሎት በመዋሉ የዋጋ ንረቱ እየተባባሰ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

መንግሥት ለዋጋ ግሽበት እየወሰደ ካለው እርምጃ የታክስ አነሳሱ በትክክል ተግባራዊ እየሆነ አለመሄዱን ገልፀው ለነዳጅ የሚሰጠው ድጎማ አንድ ወጥ መሆን እንደሌለበት ጠቁመዋል፡፡ የተሻለ የመግዛት አቅም ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ከሕዝብ ገንዘብ በእኩል ድጎማ መስጠት ተገቢ እንዳልሆነም ተናግረዋል፡፡

አሁን ያለው የዋጋ ግሽበት አስጊና አሳሳቢ ሲሆን ለረዥም ጊዜ ሊቆይ እንደሚችል ያላቸውን ሥጋት ገልፀው የዋጋ ለውጦች ከምግብ አቅርቦት ጋር የተያያዙ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ያለው የዝናብ እጥረት ከቀጠለ የዋጋ ንረቱ ይብሳል፡፡

..ኢኮኖሚው እድገት እያሳየ ቢሆንም በአጭር ጊዜ ፍላጎትን በመጨመር በዋጋ ንረቱ ላይ ጫና የሚፈጥር በመሆኑ የእድገት አይነቱን መቀየርና ከሌሎች ዘርፎች እድገት ጋር ተጣጥሞ እንዲሄድ ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ የዋጋ ንረቱን ለማስተካከል በእድገቱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊፈጥሩ የሚችሉ እርምጃዎችን በድፍረት መውሰድ ተገቢ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የገበያው ይዘት ለውድድር የሚመችና የተዘጋጀ አለመሆኑን የገለፁት ዶ/ር ኃይሌ ነጋዴዎች በመካከላቸው ያለው ውድድር ጤናማ በሚሆንበት ዙሪያ ትኩረት ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል፡፡

የዋጋ ንረትን ለማውረድ እርምጃና መስዋዕትነት እንደሚያስፈልግና ሸማቾች የዋጋ ንረቱን ተቋቁመው መግዛት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መስራት እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል፡፡ 
 
< Prev   Next >