Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow 7ኛው የሙዚቃ ፌስቲቫል...
7ኛው የሙዚቃ ፌስቲቫል... Print E-mail
Sunday, 04 May 2008
Image7ኛው የሙዚቃ ፌስቲቫል ለግርማ በየነ መታሰቢያ ሆነ
በሔኖክ ያሬድ

አልያንስ ኢትዮ ፍራንሴዝ የዘንድሮውን የኢትዮጵያ ሙዚቃ ክብረ በዓል (ፌስቲቫል) ለአንጋፋው ድምፃዊና የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋች መታሰቢያ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

 

ተቋሙ 7ኛው (7ኛው) የኢትዮጵያ ሙዚቃ ክብረ በዓል ከሚያዝያ 29 እስከ ግንቦት 10 ቀን 2000 ዓ.ም በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር ባለፈው ኀሙስ ዳይሬክተሩ ዳኒ ሻርል ኩርዶን፣ ፍራንሲስ ፋልሴቶና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዋ ማርሴማ ታሪኩ ገልፀዋል፡፡ በመክፈቻው ዕለት የፎቶግራፍ ዐውደ ርዕይ፣ የፈረንሣዊው አሌክስ ሜያርና ወዳጆቹ የባህላዊ ሙዚቃ ዝግጅት ይቀርባል፡፡ የ27 ዓመቱ ፈረንሳዊ ወጣት የሙዚቃ ባለሙያ አሌክስ ሜያር ከሦስት ዓመታት በፊት ጀምሮ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ዙሪያ ከኢትዮጵያውያን ሙዚቀኞች ጋር ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ለዚህም ፌስቲቫል አሌክስና ወዳጆቹ የባህል ዜማዎቻቸውን ከሰምና ወርቅ ብሎም ከተለያዩ ድምፀቶች ጋር በማቀናበር ልዩ ጣዕመ ዜማ እንደሚያቀርቡ ታውቋል፡፡

በሁለተኛው ቀን ሚያዚያ 30 በኢትዮጵያ የሙዚቃ ሰዎች የሕይወት ታሪክና ሥራ ዙሪያ የሚያጠነጥን ዶክመንተሪ ፊልም የሚቀርብበት ይሆናል፡፡ በካናዳ የምትኖረው አሜሪካዊት ጋዜጠኛ ካየል ስቶን ለበርካታ ዓመታት በአሜሪካና በካናዳ ከሚኖሩት ኢትዮጵያውያን ድምፃውያንና ሙዚቀኞች ቃለ መጠይቆችን በማድረግ ያዘጋጀችው ጥናታዊ ፊልም ነው፡፡ አንድ ሰዓት የሚፈጀው ፊልም ሁለት አጫጭር የተውጣጡ ፊልሞችን ያካተተ ሲሆን አንዱ ክፍል ግርማ በየነ ላይ ሲያተኩር፣ ሌላኛው ክፍል ደግሞ በ1960ዎቹ እና በ1970ዎቹ መጀመሪያ ላይ መድረክ ያንቀጠቀጡትን በቡድንና በግል ይንቀሳቀሱ የነበሩትን ሙዚቀኞች፣ ድምፃውያን፣ ዜማ ደራሲያንና የሙዚቃ አሳታሚዎች የሚያሳዩ እንደሆነ መግለጫው አስረድቷል፡፡

ዓርብ ግንቦት 1 ቀን በአሊያንስ "የቀድሞ ሙዚቃ መሣሪያዎች ሕዳሴ" (ሬኔሳንስ) በሚል ርእስ የሚኖረውን መሰናዶ በኢትዮጵያ በ1950ዎቹ ይቀርቡ የነበሩትን ተወዳጅ ዜማዎች በአዲስ መልክ የተዘጋጁ ሲሆን በቀድሞ ጊዜ የኢትዮጵያን የሙዚቃ መድረክ ተቆጣጥረው የነበሩት እንደ ማንዶሊን፣ አኮርዲዮን፣ ክላርኔትና ዳብል ቤዝ የመሳሰሉትን መሳሪያዎች በማካተት የተዘጋጀው የፖፕና የጃዝ ሙዚቃ ለኢትዮጵያውያን ትዝታን የሚያጭር ለተቀረው ዓለም ደግሞ የአገሪቱ ሙዚቃ መገለጫ የሆኑ ድምፆችን የሚያስተዋውቅ ሥራ እንደሚቀርብ እምነቱ እንደሆነ ተቋሙ ገል"ል፡፡ በ7ኛው የኢትዮጵያ ሙዚቃ ፌስቲቫል ከኢትዮጵያውያን ሌላ የውጭ አገር የሙዚቃ ባለሙያዎች ሆላንዳውያን የሚሳተፉበት ግንቦት 2/2000 ይካሄዳል፡፡ ዚያ በሚባል መጠርያ የሚታወቁት ሁለቱ ወጣት ሙዚቀኞች ኦርናልድ ዳቦልድ በጊታርና ድምፅ፣ ሬንኮ ሙየር ማን በኪቦርድ ይጫወታሉ፡፡ ሆላንዳውያኑ ሮክ ኤንድ ሮል፣ ቴክኖና ፖፕ የሙዚቃ ስልቶችን በማቀንቀን ይታወቃሉ፡፡

በተከታታይ ቀናት ከሚካሄዱት ዝግጅቶች መካከል የቀድሞ ኦርኬስትራ ኢትዮጵያ ውስጥ ግንባር ቀደም ተሳታፊ ከነበሩት መካከል አሜሪካዊው ቻርልስ ሳተን፣ ጌታ መሳይ አበበ፣ መላኩ ገላውና ዮሐንስ አፈወርቅ የሚያቀርቡት ባህላዊ ሙዚቃ ትርዒት ይኖራል፡፡

በፌስቲቫሉ ኢትዮጵያዊቷ ሙኒት መስፍንና ኑሮውን በኢትዮጵያ ያደረገው ጊታር ተጫዋች የርግ ፕፈል አዲሱን አልበማቸው የሚያስመርቁ ሲሆን ለየት ባለ መልኩ የግርማ በየነን የሙዚቃ ዜማዎች በሚያስታውስ መልኩ ያዘጋጁትን ስለፍቅር፣ ስለሕይወትና ስለ ትዝታ እየዳሰሱ በሦስት ቋንቋዎች በአማርኛ፣ በእንግሊዝኛና በፈረንሣይኛየጃዝ የፖፕና የሮክ ቅልቅል ጣዕመ ዜማቸውን ያቀርባሉ፡፡ በታዋቂዎቹ ኢትዮጵያውያን የሳክስፎን ተጫዋቾች የሳክስና የአዝማሪ ምሽቶች፣  እንደሚዘጋጁ የወጣው መርሐ ግብር ያመለክታል፡፡  

"""""///"""""

ፒያኒስት፣ ድምፃዊና ዜማ ደራሲ ግርማ በየነ


በኢትዮጵያ ወርቃማ የሙዚቃ ወቅት በሸክላው ኅትመት ዘመን ቁልፍ አስተዋጽዖ ካደረጉት የጥበብ ሰዎች አንዱ የሆነው ግርማ በየነ ከ1973 ወዲህ ነዋሪነቱ በአሜሪካ ነው፡፡ ከስድሳ በላይ በሆኑ የሙዚቃ ሥራዎች ላይ በሙዚቃ አቀናባሪነት፣ ወደ 25 በሚጠጉ ሸክላዎች ላይ በፒያኒስትነት፣ ድምፃዊና ዜማ ደራሲ በመሆን የተሳተፈው ግርማ በየነ ሙዚቃ በሸክላ ይታተም በነበረበት ከ1961 እስከ 1970 ዓ.ም ባለው ወቅት ብዛትና ጥራት ያላቸውን አዳዲስ ጣዕመ ዜማዎችን በማቅረብ ይታወቃል፡፡

ፍራንሲስ ፋልሴቶና ኅሩይ አረፋይኔ እንዳብራሩት በአሜሪካ፣ በፈንሣይና በሆላንድ በሚገኙ ታላላቅ ኦርኬስትራዎችና ባንዶች በሚሠሩት የሙዚቃ ዝርዝራቸው ውስጥ የግርማ በየነን ሥራዎች በማካተት ለዓለም አቀፍ መድረክ ያቀረቡበት ሁኔታ መኖሩና ሥራዎቹም በዓለማቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያን ውበት፣ የፈጠራ ችሎታና ዘመናይነት ሲያስመሰክሩ ይኖራሉ፡፡

 
< Prev   Next >