| 114 ዓመት ያስቆጠረው የቴሌ ህንፃ... |
|
|
| Thursday, 10 January 2008 | |
|
114 ዓመት ያስቆጠረው የቴሌ ህንፃ በቅርስነት እንዲመዘገብ ተጠየቀ - ቴሌ በንብረትነት አያውቀውም ነበር
የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አማረ አምሳሉ እንዳስታወቁት ህንፃው በቅርስነት እንዲመዘገብ የጠየቁት እንደሚፈርስ በደረሳቸው ጥቆማ መሠረት ነው፡፡ እንግሊዝ ኤምባሲ ፊት ለፊት በ1886 ዓ.ም የተሰራው የስልክ ማስተላለፊያ ህንፃ ላይቭ ካፍቴሪያ የሚል ስያሜ ተፈጥሮለታል፡፡ በውስጡ የጐዳና ተዳዳሪዎች ይኖሩበታል፡፡ አቶ አማረ እንዳስታወቁት ህንፃው ከመቶ ዓመት በላይ ያስቆጠረ ታሪካዊ ህንፃ በመሆኑ በመንገድ ማስፋፊያ ምትክ ቢፈርስም ተመልሶ በነበረበት ሁኔታ ተገንብቶ ቅርስ መሆን አለበት፡፡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ወይም ኮርፖሬሽኑ በሚያመቸው ቦታ ታሪካዊውን የመጀመሪያ የረዥም የሽቦ ስልክ የተጀመረበትን ህንፃ ለማሰራት ኮርፖሬሽኑ ሙሉ በሙሉ ፈቃደኛ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈፃሚው ገልፀዋል፡፡ ህንፃውን አንኮበር ሎጅ ያላቸው ባለሀብት እንደሚፈልጉትና ከተፈቀደላቸው አፍርሰው ወስደውት በነበረበት ሁኔታ ሊገነቡት እንደሚፈልጉ መግለፃቸው ታውቋል፡፡ ህንፃው እንደሚፈርስ ለኮርፖሬሽኑ ከመጠቆሙ በፊት ኮርፖሬሽኑ ህንፃውን በንብረትነት አያውቀውም ነበር፡፡ ኮርፖሬሽኑ ህንፃውን በባለቤትነት ሲያውቅ በቅርስነት እንዲመዘገብ ጥያቄ አቅርቦ መልስ በመጠባበቅ ላይ ነው፡፡ ህንፃውን በአካል ተገኝተን ስንመለከት አስተያየት የሰጡ ህንፃው ሙዚየም ነው፡፡ ለታሪክ ዋጋ የማይሰጡ ካላጣጣሉት በስተቀር በጥንቃቄ ፈርሶ በጥንቃቄ መልሶ ቢገነባ መልካም ነው ብለዋል፡፡ በአሰግድ ተፈራ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |