Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Aug 29th
Home arrow Sections arrow የአውሮፓ ህብረት ፖሊሲ...
የአውሮፓ ህብረት ፖሊሲ... Print E-mail
Sunday, 04 May 2008
የአውሮፓ ህብረት ፖሊሲ አውጪዎችና የአፍሪካ ዲያስፖራዎች ይወያያሉ

በጋዜጣው ሪፖርተር

ዲያስፖራው ስደትን ለማርገብም ሆነ በልማት ለመሳተፍ ቁልፍ ሚና ስላለው የአውሮፖ ፖሊሲ አውጪዎች በመጪው ሰኔ ወር ከአፍሪካዊያኑ ዲያስፖራ ጋር በብራስልስ ለውይይት ይቀመጣሉ፡፡

 

"ዘ አፍሪካን ዲያስፖራ ፖሊሲ ሴንተር" እንዳስታወቀው የብራስልሱ ሴሚናር የሚካሄደው የአፍሪካዊው ዲያስፖራ ድምፅ፣ ራዕይና አመለካከት በአውሮፓ ህብረት ደረጃ በሚወጡ ፖሊሲዎች ላይ መካተት የሚችሉበትን መንገድ ለማመቻቸት ነው፡፡ በሌላም በኩል በማኒላ በመስከረም 2001 ለሚደረገው የስደትና ልማት አለማቀፍ ፎረም የአፍሪካዊውን ዲያስፖራ አመለካከት ለፖሊሲ ግብዓትነት መጠቀምን ዓላማ ያደረገ ነው፡፡

ሁለት ተያያዥነት ያላቸውን ዋና ዓላማዎች መሠረት አድርጐ የሚካሄደው ሴሚናር ዲያስፖራው በተለያዩ መድረኮች ላይ ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ተሳትፎ እንዲያደርግ ያግዛል፡፡ በተለያዩ የፖሊሲ ደረጃዎችም የዲያስፖራው የተለያዩ ሃሳቦች ይካተታሉ፡፡ የፖሊሲ አቅጣጫዎችም ከዲያስፖራው መሰንዘሩ በስደትና ልማት ጉዳይ ላይ ድምፁ እንዲሰማ ያደርጋል፡፡

የዲያስፖራውን ድምፅ በመዋቅራዊና አግባብ ባለው መልኩ በዓለማቀፍ ደረጃ በሚደረግ ውይይት ላይ ማካተት አፍሪካዊው ዲያስፖራ ያለበትን ችግር ለመፍታትም ሆነ ለአገሩ ሊያበረክት የሚችለውን አስተዋፅኦ ለማጐልበት ጉልህ ሚና ይኖረዋል ተብሏል፡፡

በተለያዩ የስደትና የልማት ጉዳዮች ላይ ከአውሮፓ ህብረት ፖሊሲ አውጭዎች ጋር ለመወያየት፣ ግንኙነት ለመፍጠር፣ መረጃ ለመለዋወጥ፣ ጥሩ ተሞክሮዎችን ለማሳየትና ልምድ ለመለዋወጥ እንዲሁም አዲስ ሃሳቦችንና የአሰራር ዘዴዎችን ለመሰንዘር በ10 በአውሮፓ ህብረት አባል አገራት ነዋሪ የሆኑ 50 የአፍሪካ ዲያስፖራ ድርጅቶች ይሳተፋሉ፡፡

በሰኔ ላይ ለሚደረገው ሴሚናር ቅድመ ዝግጅትም ከአፍሪካዊው ዲያስፖራና ከአውሮፓ ህብረት ፖሊሲ አውጪዎች የተውጣጡ 20 ቁልፍ ሚና ያላቸው ኃላፊዎች ውይይት አካሂደዋል፡፡

ሚያዚያ 17 ቀን 2000 ዓ.ም በሄግ የተካሄደው ይኸው ቅድመ ውይይት በአውሮፓ ያሉ አፍሪካዊያን ዲያስፖራዎችን በአፍሪካ ቁልፍ የልማት አጋር ለማድረግና ሃሳባቸውን በሰኔ ለሚካሄደው ውይይት ለማካተት ነበር፡፡

ዲያስፖራው ያለንበትን የ21ኛውን ክፍለ ዘመን አቅጣጫና አሰራር ለመቅረፅ አንዱ ሃይል ነው፡፡ በመሆኑም ዲያስፖራው ለአገሩ ለሚያደርገው የልማት አስተዋፅኦ የህብረቱ አባል አገራት እንደ አጋር መጠቀም አለባቸው፡፡

አፍሪካዊውን ዲያስፖራ እንደ ቁልፍ የልማት አጋር ለመጠቀምና የአውሮፓ ህብረት ለአፍሪካ አገራት ለሚሰጠው እርዳታ አጋዥ ለማድረግ የዲያስፖራውን ድምፅ በፖሊሲ ማካተቱ ወሳኝ ነው፡፡

በተደረገው ቅድመ ውይይት ቅድሚያ ተሰጥቷቸው በሰኔው ሴሚናር የሚቀርቡ የዲያስፖራው ጉዳዮችም ተለይተዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ለዲያስፖራ ድርጅቶች የሚያስፈልጉ እገዛዎች፣ የግንኙነት መረብ መዘርጋት፣ ተቋማትና ማበራትን ማጠናከር ይገኙበታል፡፡

በአፍሪካ ያሉ ውስብስብ ችግሮችን ለመቅረፍ የሶሻል ካፒታል፣ የምሁራን አስተዋፅኦ፣ ማበረታቻዎችና እንቅስቃሴዎች እንዲሁም የተጠናከረ አቅም ያስፈልጋል፡፡ ለዚህ ደግሞ አፍሪካዊው ዲያስፖራ ያለው አስተዋፅኦ ቀላል አይደለም፡፡

በህብረቱ አባል አገራት የሚገኘውን የዲያስፖራ ሃይል ማንቀሳቀስና ቀጣይነት ባለው መንገድ ለአፍሪካ ልማት መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡ በመሆኑም ለህብረቱ አጋር የሆነውን አፍሪካዊ ዲያስፖራ በፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ማወያየቱ አመርታን ያመጣል ተብሎ ታምኖበታል፡፡

በአውሮፓ ህብረት አባል አገራት ብቻ የሚኖረው ዲያስፓራ 3.3 ሚሊዮን የሚደርስ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 1 ሚሊዮን የሚሆነው ከሰብ ሰሃራ አፍሪካ በታች ከሚገኙ አገራት የመጣ ነው፡፡ በመሆኑም አፍሪካዊው ዲያስፖራ ያለው የአቅምና የእውቀት ሃይል ብዙ ደሃ አገራት በሚገኙበት ለዚሁ የአህጉሪቱ ክፍል እንደ ተቀማጭ ሃብት ነው፡፡  

ከፍተኛ ቁጥር ያለው ዲያስፖራ የአስገዳጅነት ሃይል ባላቸው፣ የፖለቲካ ማዕከላትና ዓለማቀፍ ፖሊሲዎች ውሳኔ በሚያገኙበት እንደ ለንደን፣ ፓሪስ፣ ኒውዮርክ እንዲሁም ዋሽንግተን በመሳሰሉ አገራት መኖሩ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ ሆኖም አፍሪካዊው ዲያስፖራ የእሲያዎቹን ያህል በእነዚህ አገራት በመኖሩ አቅሙን ሙሉ ጥቅም ላይ አላዋለውም፡፡

ሆኖም በአሁኑ ወቅት ደግሞ በምዕራቡ ዓለም የሚገኘው ዲያስፖራ በአገሩ ኃላፊነት እንዳለበት ያለው ግንዛቤ እያደገ መጥቷል፡፡ በምዕራቡ ዓለምና በአፍሪካ መካከል ጠንካራ ግንኙነት ለመፍጠርና የህብረቱ አባል አገራት በአፍሪካ ለሚያደርጉት ልማት እንደድልድይ ለማገልገል ስሜትም እያሳየ ነው፡፡

አፍሪካዊው ዲያስፖራ ለልማት ያለው አስተዋፅኦ ከዚህ ቀደም ከነበረው በበለጠ እየታየ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በትውልድ አገራቸው ልማት ለማሳተፍና አዎንታዊ ለውጥ ለመምጣት ፍላገቱ አላቸው፡፡

ሰኔ 18 እና 19 ቀን 2000 ዓ.ም በብራስልስ የሚካሄደው ሴሚናር የአፍሪካዊውን ዲያስፖራ የልማት አጋርነት ለማረጋገጥ ወሳኝ የፖሊሲ አቅጣጫዎች የሚጣለበት ነው ተብሎ ይጠበቃል፡፡ 

 
< Prev   Next >