| የዕንቁ መጽሔት አሣታሚና ሦስት የሥራ... |
|
|
| Wednesday, 07 May 2008 | |
|
የዕንቁ መጽሔት አሣታሚና ሦስት የሥራ ባልደረቦቻቸው የጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው
በታምሩ ጽጌ በአለማየሁ አሣታሚ ድርጅት ሥር በየወሩ እየታተመ የሚወጣው የዕንቁ መጽሔት አሣታሚ፣ ምክትል አዘጋጅና ሦስት ተባባሪ ሠራተኞቻቸው ላይ ትናንት ፖሊስ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆ ተፈቀደለት፡፡ ፖሊስ አሣታሚውን አቶ አለማየሁ ማህተመ ወርቅ፣ ሲሳይ ወርቁ፣ ሰሎሞን መኮንንና ኢሣያስ (የታክሲ ሾፌር) ሚያዚያ 24 ቀን 2000 ዓ.ም ከምሽቱ 4፡30 ሰዓት አካባቢ በብራና ማተሚያ ቤት ያሳተሙትን አሥር ሺ ዕንቁ መጽሔት ለመውሰድ ሲሄዱ ከነመጽሔቱ በቁጥጥር ሥር አውሎ እንዳሰራቸው የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ፈቃዱ ማኅተመ ወርቅ ለሪፖርተር ጋዜጣ ገለፀዋል፡፡ መጽሔቱን ለክልሎችና ለአዲስ አበባ ለማከፋፈል ወደ ማተሚያ ቤቱ (ብራና) ሲገቡ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሠራተኞችም ሆነ እሳቸው ባላወቁት ምክንያት ለሦስት ቀናት ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ፖሊስ በትናንትናው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ልደታ ክፍለ ከተማ ምድብ ችሎት አቅርቦ የ14 ቀናት ጊዜ ቀጠሮ ጠይቆ እንደተፈቀደለት ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡ ሚያዚያ 25 ቀን 2000 ዓ.ም ለገበያ ሊበቃ የነበረው ዕንቁ መጽሔት በአብዛኛው የያዘው መጣጥፍ ከፊት ሽፋኑ ጭምር፣ በቅርቡ ክስ ተመስርቶበት የዋስትና መብት ተከልክሎ ማረሚያ ቤት የሚገኘው አርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁንን (ቴዲ አፍሮ) መሆኑንና ሌሎችንም መጣጥፍ እንደያዘ ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት በቁጥጥር ሥር ውለው በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በእስር ላይ የሚገኙት የመጽሔቱ ሠራተኞች ለግንቦት 11 ቀን 2000 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን፣ በዕለቱ ችሎት ሲቀርቡ ቤተሰብና ጋዜጠኞች እንዳይገቡ ተከልክሎ በጽ/ቤቱ በኩል ጊዜ ቀጠሮ እንደተጠየቀባቸው ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |