Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow ፑንትላንድ ተጨማሪ ወንጀለኞችን...
ፑንትላንድ ተጨማሪ ወንጀለኞችን... Print E-mail
Wednesday, 07 May 2008
ፑንትላንድ ተጨማሪ ወንጀለኞችን ለኢትዮጵያ መንግሥት አስረከበች

በጋዜጣው ሪፖርተር

የሶማሊያ ፑንት ላንድ ባለሥልጣናት በኢትዮጵያ መንግሥት የሚፈለጉ ወንጀለኞችን ለኢትዮጵያ አሳልፋ መስጠቷን ገለልተኛ ወገኖችን በመጥቀስ ጋሮዋ ኦንላይን የተባለ ድረ ገፅ ዘገበ፡፡

በዘገባው መሠረት ከኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር ጋር ግንኙነት ያላቸው ከአሥራ ሦስት በላይ ሰዎች በጋልካዬ ከተማ አካባቢ በፑንት ላንድ የፀጥታ ኃይሎች ተይዘዋል፡፡ የፑንትላንድ የፀጥታ ኃይሎች ባደረጉት ምርመራ ከስድስት በላይ የቡድኑ አባላት ለኢትዮጵያ የደህንነት ሠራተኞች ተላልፈው እንዲሰጡ ተደርጓል፡፡

በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪዎች ዘመዶች፤ የፑንት ላንድና የኢትዮጵያ የደህንነት ሰራተኞች ተጠርጣሪዎችን በጋሮዋ ከተማ ውስጥ በድብቅ ቦታ ማሰራቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል፡፡

የተጠርጣሪዎች ዘመዶች ተጠርጣሪዎቹ ለሥራ ፍለጋና የህክምና ወደ ፑንት ላንድ መሄዳቸውን አሳውቀዋል፡፡ የአካባቢው ሽማግሌዎች በበኩላቸው የጋልካዬ ከተማ መስተዳድር አባላት ስለተጠርጣሪዎቹ መረጃ ከመስጠት መቆጠባቸውን ገልፀዋል፡፡

በጋልካዬ የሚገኙ የጐሣ መሪ በበኩላቸው ተጠርጣሪዎቹ ከጐሣ ግንኙነት ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል፡፡ ሽማግሌዎቹ ተጠርጣሪዎቹ በኦጋዴን አካባቢ የሚገኝ ጐሣ አባላት መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

ሽማግሌዎቹ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ የሞቃዲሾ ነዋሪዎች "ኢትዮጵያ ወራናለች" የሚል አመለካከት እንዳላቸው አስታውቀዋል፡፡

ከአንድ ወር በፊት የፑንትላንድ የመረጃ ሠራተኞች ሁለት የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን በቁጥጥር ሥር በማዋል ለኢትዮጵያ ማስረከባቸው ይታወሳል፡፡ የፑንትላንድ አስተዳደር ሁለቱ የግንባሩ አባላትን ለኢትዮጵያ ሲያስተላልፍ የመጀመሪያ ጊዜው መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት የፑንትላንድ አስተዳደር ለነፃ አውጪው ግንባር ድጋፍ ያደርጋል በሚል አጥብቆ ወንጅሏል፡፡ ይህንን ተከትሎ ያለፈው ወር የፑንትላንድ ኘሬዚዳንት አዴ ሙሴ ኢትዮጵያን መጐብኘታቸው ይታወሳል፡፡
 
< Prev   Next >