| አገር ውስጥ ገቢ ከ5 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ< |
|
|
| Wednesday, 07 May 2008 | |
|
በጋዜጣው ሪፖርተር
የፌዴራል አገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን በ2000 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ከዕቅድ በላይ በማሳካት 5.903 ቢሊዮን ብር ገቢ ሰበሰበ፡፡ ባለሥልጣኑ ከሐምሌ 1 ቀን 1999 እስከ መጋቢት 30 ቀን 2000 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት 5.571 ቢሊየን ብር ገቢ ለማግኘት አቅዶ 5.903 (105.96 በመቶ) ማሳካቱን አቶ አበበ ከበደ በባለሥልጣኑ የሕዝብ ግንኙነት አገልግሎት ኃላፊ ለሪፖርተር ጋዜጣ ገልፀዋል፡፡ ባለሥልጣኑ በዘጠኝ ወራት አፈፃፀሙ ያገኘው ገቢ በታክስ መደቦች ሲቀመጥ ከቀጥተኛ ታክሰ 2.867 ቢሊየን ብር፣ ቀጥተኛ ያልሆኑ ታከሶች 3.033 ቢሊየን ብር፣ ታክስ ያልሆኑ ገቢዎች 3.040 ሚሊዮን ብር ነው፡፡ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ቀጥተኛ ካለሆኑ ታክሶች የሚመደብ መሆኑን፣ በዚህ ዘርፍ ከተገኘው ገቢ 2.338 ቢሊየን ብር ድርሻ መያዙ ተጠቁሟል፡፡ ባለሥልጣኑ ዘንድሮ ያገኘው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሣሣይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ36.56 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን አቶ አበበ ተናግረዋል፡፡ ለዕድገቱ መገኘት እንደምክንያት ከተጠቀሱት መካከል የኮምፒዩተር ቴክኖሎጂ ሥርዓት በአግባቡ መጠቀም መቻሉ፣ የግብር ከፋዩ ትምህርት መጠናከሩ፣ የአገሪቱ ኢኮኖሚ እያደገ መምጣቱ፣ ከ3ኛ ወገን የሚሰበሰበው መረጃ እና የአገልግሎት አሰጣጡ መሻሻሉ ይገኝበታል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |