Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 06th
Home arrow Sections arrow 4000 መምህራን ለምርጫ ሥራ...
4000 መምህራን ለምርጫ ሥራ... Print E-mail
Thursday, 10 January 2008

4000 መምህራን ለምርጫ ሥራ መሰማራታቸው ትምህርቱን ይጐዳል

በአዲስ አበባ ከተማ በሚካሄደው የወረዳ፣ የቀበሌና የማሟያ ምርጫ 4ሺ መምህራኖች መመልመላቸው የትምህርት ሂደቱን ይጐዳል በሚል የክፍለ ከተማ የትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ተቃወሙት፡፡

የክፍል ከተማ የትምህርት ሥልጠና ፅህፈት ቤት (የክፍለ ከተማ የትምህርት ቢሮ) ኃላፊዎች ተቃውሟቸውን ያቀረቡት በጋራ ባደጉት ስብሰባ ነው፡፡

የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ መምህራኑ በብዛት ወደ ምርጫ ሥራ እንዲገቡ መደረጉ በትምህርቱ ሥራ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያደርስ እንደሚችል ኃላፊዎቹ አስጠንቅቀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ማስተባበሪያ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ካሳሁን ጣሰው የክፍለ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ባቀረቡት መሠረት ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር ንግግር እንደሚደረግ ለሪፖርተር ገልፀዋል፡፡

የክፍለ ከተማ የቢሮ ኃላፊዎች ለምርጫ ሥራ የሄዱባቸውን መምህራን ብዛት በየዘርፉና በየደረጃው ለይተው እንዲያቀርቡ መጠየቃቸውም ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

የምርጫ ሥራ ሁሉም ወገኖች መሰለፍ አለባቸው ያሉት ኃላፊው የትምህርት ሥራ ላይ ችግር የሚፈጠር መሆኑ ታይቶ ማስተካከያ እንዲደረግበት ይደረጋል ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ በቅድመ መደበኛ 4..534፣ በአንደኛ ደረጃ 14..549 በሁለተኛ ደረጃ 4..565፣ መምህራኖች ሲኖሩ የተጠቀሰው ቁጥር የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤቶችን አያካትትም፡፡

በአሰግድ ተፈራ

 
< Prev   Next >