Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ይቋቋማል
የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ይቋቋማል Print E-mail
Wednesday, 07 May 2008
በኃይሌ ሙሉ

የፌደራል ገቢ ሰብሳቢ መሥሪያ ቤቶች እንዲዋሀዱና በአንድ ተቋም እንዲደራጁ የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ፡፡ የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለሥልጣንና የፌደራል አገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን በመዋሀድ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የተባለ ተቋም ይቋቋማል፡፡

አዲሱን አደረጃጀት አስመልክቶ የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ እንደሚያሳየው ገቢ ሰብሳቢ መሥሪያ ቤቶቹ እንዲዋሀዱ የታሰበው መንግሥት የአገሪቱ ኢኮኖሚ ሊያመነጭ የሚችለውን ገቢ በብቃትና በወቅቱ ለመሰብሰብ የሚያስችል አደረጃጀትና ዘመናዊ የአሰራር ስርዓት ያለው ጠንካራ ገቢ ሰብሳቢ ተቋም ሊኖረው ስለሚገባ ነው፡፡

በረቂቅ አዋጁ ምሰረታ ባለሥልጣን ሆኖ እንዲደራጅ የሚደረገው አዲሱ ተቋም ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅህፈት ቤት ሲሆን የተቋሙ መሪ /ዋና/ ዳይሬክተርም የፖለቲካ ተሿሚ ይሆናል፡፡ ተቋሙን በባለሥልጣን ደረጃ ማቋቋም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲጠራ ያስፈለገው የመንግሥትን የቅርብ ክትትልና ድጋፍ እንዲያገኝ ስለሚያስችለው መሆኑ ተመልክቷል፡፡

የተቋሙ ሠራተኛ ሌላው የመንግሥት ሠራተኛ ከሚተዳደርበት በተለየ የሠራተኛ አስተዳደር ህግ እንዲተዳዳር፣ ተቋሙ በራሱ የሆነ የኢንተሌጀንስ፣ መርማሪና ዐቃቤ ሕግ እንዲኖረው እንዲሁም የተለየ ችሎት እንዲደራጅለት የሚደረግ መሆኑንና የፖሊስ ተግባርን በተመለከተም በተለይም የጥበቃ፣ የቁጥጥር፣ ቅኝትና አጥፊን የመያዝ ሥራ ከተቋሙ ወጥቶ በፌደራል ፖሊስ እንዲከናወን መታሰቡን ረቂቅ አዋጁ ይገልፃል፡፡

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዓላማ ለማሳካትና በከፍተኛ ፖሊሲና ስትራቴጂክ ነክ ጉዳዮች ላይ የመንግሥትና የህብረተሰቡን ጥቅምና ፍላጐት ማዕከል በማድረግ ዋና ዳይሬክተሩን የሚያማክር ቦርድ እንዲቋቋም በአዋጁ ላይ ተመልክቷል፡፡

የቦርዱ አባላት በዋና ዳይሬክተሩ የሚሰየሙ ሲሆን የአባላቱ ስብጥርም ከተለያዩ የመንግሥት አካላት፣ ከግሉ ሴክተር እና ከሙያ ማህበራት የተውጣጡ እንደሚሆኑ የቦርድ ሰብሳቢም ዋና ዳይሬክተሩ እንደሚሆኑ ተጠቅሷል፡፡

የፌደራል ፍርድ ቤቶችን ኃላፊነት በተመለከተም ከዚህ ቀደም ሲካሄዱ የነበሩ ክሶች በመደበኛው ችሎት ላይ ተደርበው ስለሚታዩ በተፈለገው ፍጥነት ውሳኔ እንደማያገኙ ተጠቁሞ በታክስና ጉምሩክ ጉዳዮች ለፍርድ ቤት የሚቀርቡ ክርክሮች በተለየ ችሎታ እና ለዘርፉ በቂ እውቀት ባላቸው ዳኞች እንዲታዩ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

በረቂቅ አዋጁ ላይ እንደተገለፀው አዲስ በሚቋቋመው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤት ውስጥ የፖሊስ ተግባር በሁለት ተከፍሏል፡፡ የምርመራ ሥራው ባለሥልጣኑ በሚያደራጀው የኢንተለጀንስና ምርመራ ክፍል ባለሙያዎች እንዲከናወን ሲደረግ የጥበቃ፣ የቅኝት እንዲሁም የወንጀል ተጠርጣሪን አድኖ መያዝና ለህዝብ የማቅረብ ተግባር ግን በፌደራል ፖሊስ እንዲከናወን ይደረጋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በገቢዎች ሚኒስቴር ሥር የሚገኘው የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር በአዲሱ አደረጃጀት መሠረት ከገቢ ሰብሳቢ መሥሪያ ቤቶቹ ተገንጥሎ ራሱን ችሎ እንደሚቀጥል ታውቋል፡፡

የገቢ ሰብሳቢ መሥሪያ ቤቶቹ መዋሀድ ተመሳሳይ ሥራዎችን፣ አቅምን፣ ሀብትን፣ የሰው ኃይልን በማዋሀድ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል ተብሏል፡፡
 
< Prev   Next >