Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow ፕ/ር መስፍን ከቀረበባቸው ክስ በነፃ ተሰናበቱ
ፕ/ር መስፍን ከቀረበባቸው ክስ በነፃ ተሰናበቱ Print E-mail
Wednesday, 07 May 2008
ክሱ ሰባት ዓመታትን ፈጅቷል

በታምሩ ጽጌ

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ ከሰባት ዓመታት በፊት ከመሠረተባቸው ክስ  በነፃ እንዲሰናበቱ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት በትናንትናው ዕለት ወሰነ፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን ከቀረበባቸው ክስ በነፃ ሊሰናበቱ የቻሉት የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ በሚያዚያ ወር 1993 ዓ.ም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን የሐሰት "የማወናበጃ" ወሬ በመንዛት ለአመፅ አነሳስተዋል በሚል የመሠረተባቸውን ክስ ሙሉ በሙሉ መከላከል በመቻላቸው መሆኑን ፍርድ ቤቱ ገል"ል፡፡

ዐቃቤ ሕግ በክሱ ላይ እንዳመለከተው፣ በሕገ መንግሥቱ ክልክል መሆኑን እያወቁ ሆን ብለው እሳቸው ሰብሳቢ በሆኑበት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በጠራው ስብሰባ ላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በመጋበዝ ስለአካዳሚክ ነፃነት እናስተምራለን በማለት ለአመፅ እንዲነሳሱ የሚገፋፋ ንግግር አድርገዋል በሚል ክስ መመስረቱን ፍርድ ቤቱ ለችሎቱ ባሰማው ንባብ አስታውሷል፡፡

ለተማሪዎቹ ንግግር በማድረግ ለአመፅ እንዲነሳሱ አድርገዋል በማለት ዐቃቤ ሕግ ክስ የመሠረተባቸው በፕ/ር መስፍን እና ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ላይ ቢሆንም፣ በዶ/ር ብርሃኑ ጉዳይ ፍ/ቤቱ ከአንድ ዓመት በፊት በሰጠው ብይን በሁለቱም ክስ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ ይሰናበቱ ብሏል፡፡ በዚሁ ዕለት ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም በአንዱ ነፃ ተሰናብተው በአንደኛው ክስ እንዲከላከሉ መወሰኑን ፍርድ ቤቱ ለችሎቱ በንባብ አሰምቷል፡፡

ፕ/ር መስፍን ያቀረቡአቸው መከላከያ ምስክሮች፣ ተከሳሹ በወቅቱ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በተናጋሪነት ጋብዘዋቸው እንጂ በኢሠመጉ ስብሰባ ላይ ሰብሳቢ ሆነው አለመሆኑንና ሌላም የሚያውቁትን መመስከራቸውን ፍርድ ቤቱ ተናግሯል፡፡

ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ በፖሊስ ጣቢያና በፍርድ ቤት የሰጡትን ቃል በመመርመርና በማገናዘብ፣ "ተከሳሹ ክሱን በበቂ ሁኔታ መከላከል በመቻላቸው በነፃ ተሰናብተዋል" በማለት ለዋስትና ያስያዙት ገንዘብ እንዲመለስላቸው ሲል ትዕዛዝ በመስጠት መዝገቡን ዘግቷል፡፡
 
< Prev   Next >