Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow የዚምባብዌው ምርጫና ቀውሱ
የዚምባብዌው ምርጫና ቀውሱ Print E-mail
Wednesday, 07 May 2008
በዚምባብዌ ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የቆየው ፕሬዚዳንታዊ የምርጫ ውጤት ይፋ ሆነ፡፡ የውጤቱን መገለጽ አስከትሎ የተሰባበሩ እግሮችና እጆች፣ የተቃጠሉ ጎጆዎችና አስከሬኖች የሚታዩባቸው ጨለማ ቀናት ነበሩ ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ህዝቡ ቆራጥ ነው፡፡ ውጤቱ ተሳሳተ ማለት ተቀባይነት የሌለው ነገር ነው ሲሉ አዲሱ የዛኑ ፒ ኤፍ ተመራጭ ቢትሪስ ኛሙፒንዳ ተናግረዋል፡፡

ለእኛ ለተማርን ሰዎች ይህ ወደ 1ኛ ደረጃ ተመልሶ እንደመግባት ይቆጠራል፡፡ እኔ አሸንፌያለሁ ስለዚህ ደግሞ መቁጠሩ ሰዓት ማባከን ነው ብለዋል ቢትሪስ ኛሙፒንዳ፡፡

ውጤቱ እንደተነገረ የሐራሬ መንገዶች ወደ ባንክ በሚሄዱ ነዋሪዎች ተጨናንቆ ታይቷል፡፡ ገንዘብ ማግኘት ከባድ ነው፤ ነዳጅ በጋሎን በጣም ብዙ በሆነ የዚምባብዌ ዶላር በጥቁር ገበያ እየተሸጠ ነው፡፡ በኃይል መቋረጥ ምክንያት ከተማዋን ጨለማ ውጧታል፡፡ እናም ሐራሬዎች የፖለቲካ ዕጣ ፈንታቸውን ለማስጠበቅ ደፋ ቀና ይላሉ፡፡

“የመራጮቹ አስተሳሰብ የታወቀ ነው፡፡ ሙጋቤ ከአህያ ጋር እንኳ ቢወዳደሩ አህያዋ ታሸንፋለች፡፡ ምክንያቱም የሚመርጣቸው የለም፡፡” ሲሉ የቀድሞው የማስታወቂያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ጆናታን ሞዮ ተናግረዋል፡፡

የቻይናው መሪ ጃፓንን እየጎበኙ ነው

የቻይናው መሪ ሁ ጂንታኦ ለአምስት ቀናት የሚቆየውን የጃፓን ጉብኝት ጀመሩ፡፡ ይህም በ10 ዓመታት ውስጥ የተደረገ የመጀመሪያው ጉብኝት ነው ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ስለ ንግድ ግንኙነቶች፣ ደህንነትን በተመለከተና ሌሎችንም ጉዳዮች ከጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ያሶ ፉክዳ ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ቻይና በጃንችሮ ኮዙሚ ከተካሄደው ሻምፒዮንስ ማለት ከ2001 - 2006 ባሉት ዓመታት ከጃፓን ጋር የነበራትን ግንኙነት አቋርጣ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ የሚስተር ሁ ጉብኝት የመጀመሪያ ረጅም ጉዞ እንደሆነና ከጃፓን ጋር ግንኙነት መኖሩ ጠቀሜታ እንዳለው የሚያሳይ ነው ብለዋል ተንታኞች፡፡

“በጉብኝቴ ወቅት የቀድሞ ጃፓናዊ ጓደኞቼን እንደማገኛቸውና አዳዲስ ሰዎችንም እንደምተዋወቅ ነው” ብለዋል ሲል ዥነዋ ቅዳሜ ዘግቧል፡፡ የቢቢሲው ዘጋቢ በበኩሉ ሁለቱም አገሮች መልካም ጉርብትናን ይፈልጋሉ ብሏል፡፡

የኦልመርትና አባስ ውይይት ቀጥሏል

የፍልስጥኤሙ መሪ ፕሬዚዳንት ማህሙድ አባስ እና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ኢሁድ ኦልመርት በኢየሩሳሌም ተገናኝተው ተወያዩ፡፡ ውይይታቸው በአንድ ወር ውስጥ ለሦስተኛ ጊዜ መሆኑን ቢቢሲ ዘገበ፡፡

የወደፊቱን የፍልስጥኤም ዳርድንበርንና የዌስት ባንክን የሰላም አጠባበቅ በተመለከተ በሚደረገው ውይይት ላይ ስምምነት ላይ እንደሚደርሱ ይጠበቃል ሲሉ ኃላፊዎቹ ተናግረዋል፡፡

የአሜሪካ መንግሥት ዋና ፀሐፊ ኮንዶሊዛ ራይስ ጉብኝታቸውን ያጠናቀቁ ሲሆን ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዋሽንግተን ቡሽ ስልጣናቸውን ከመልቀቃቸው በፊት የሰላም ስምምነት ላይ እንደሚደርሱ ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል፡፡


ፕሬዚዳንት ቡሽ 60ኛውን የእስራኤል መንግሥት ምስረታ በዓል በማስመልከት በሚቀጥለው ወር እስራኤልን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል፡፡

ሶማሊያ የምስራቅ አፍሪካ አዲሷ አፍጋኒስታን?

አሜሪካና ሌሎች የምዕራቡ አገራት ምስራቅ አፍሪካ በተለይም ሶማሊያ የአክራሪ ሙስሊም ሸማቂዎች ምሽግ ላለመሆናቸው ይጠረጠራሉ ሲሉ ቢቢሲ ዘገበ፡፡

በተለይም በ2006 በኢትዮጵያ ወታደራዊ ሃይሎች ከሞቃዲሾ የተባረረው አልሻባብ የተሰኘው ታጣቂ የእስላማዊ ፍርድ ቤት ክንፍ ዋና ተጠርጣሪ ነው፡፡

ማክሰኞ የተገደለው የአልሻባብ መሪ አደን ሀሺ አይሮን ጨምሮ የሶማሊያ ጂሀዲስቶችም በ1990ዎቹ ከአፍጋኒስታን ማሰልጠኛ ተቋም የወጡ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ 
 
< Prev   Next >