Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow የኤርትራ ተቃዋሚዎች በጀመሩት ጉባኤ...
የኤርትራ ተቃዋሚዎች በጀመሩት ጉባኤ... Print E-mail
Wednesday, 07 May 2008
Image
Image
ከትናንት በስቲያ የተጀመረው ጉባዔ
የኤርትራ ተቃዋሚዎች በጀመሩት ጉባኤ የስደት መንግሥት ለማቋቋም አስበዋል


በየማነ ናግሽ

በኤርትራው ኘሬዚዳንት አሳያስ አፈወርቂ ስርዓት ተማረው ትግል የጀመሩ 13 ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ አንድነታቸውን አጠናክረውና በአንድ ጥላ ስር ሆነው ለመታገል በአዲስ አበባ የአንድነት ጉባኤ ጀመሩ፡፡ የስደት መንግሥት ለማቋቋም ፍላጎት አላቸው፡፡

ከትናንት በስቲያ የተጀመረው ጉባዔ በኤርትራ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ምስረታ የመጀመሪያው ምዕራፍ እንደሆነ በመክፈቻው ላይ ተገል"ል፡፡ በጉባኤው ላይ የተገኙት አንዳንድ ተሰብሳቢዎች የአሁኑ የተቃዋሚዎች ጉባኤ አጀንዳ ከሆነው አንድነቱን ከማጠናከር አልፎ የኤርትራ መንግሥት የሚያስወግድ የስደት መንግሥት የማቋቋም ሃሳብ ያለ መሆኑን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

በጉባዔው መክፈቻ ላይ "የኢትዮጵያና የኤርትራ ሕዝቦች በኢሳያስ አፈወርቂ የተሳሳተ ፖሊሲና ፀብ ጫሪነት የተነሳ ደም አፍሳሽ ጦርነት አካሂደዋል፡፡ ለስደትና ለችግር ተጋልጠዋል፡፡ ይህ ጥቁር ጠባሳ ተረስቶ ሰላም ይፈጠራል" የሚል ንግግር ቀርቧል፡፡

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አዳራሽ ለአንድ ሳምንት በሚካሄደው ጉባዔ ላይ ተቀማጭነታቸው አሜሪካና አውሮፓ ያደረጉ የኤርትራ የሲቪክ ማህበራት ተወካዮች፣ ታዋቂ የአገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች በታዛቢነት ተገኝተዋል፡፡

ታዛቢዎቹ ጉባዔው ግልፅና በኤርትራ ላለው ቀውስ መፍትሄ የሚያፈላልግ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

የኤርትራ ዴሞክራሲያዊ ኪዳን በሚል መጠሪያ የሚታወቁት የኤርትራ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በሀያላን አገሮች ድጋፍ እንደሚያደርጉላቸውም ለማወቅ ተችሏል፡፡
 
< Prev   Next >