| 'ከኤርትራ ጋር ጦርነት ሊፈነዳ ይችላል' ጅቡቲ |
|
|
| Wednesday, 07 May 2008 | |
![]() ፕሬዚዳንት ኦማር ጊሌ የኤርትራና የጅቡቲ ወታደሮች መፋጠጣቸውንና ጦርነት ሊፈነዳ የሚችል መሆኑን የጅቡቲው ፕሬዚዳንት ማስታወቃቸውን ሮይተር የዜና ወኪል ዘገበ፡፡ ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌ ባለፈው ሰኞ ምሽት ላይ በጅቡቲ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ኤርትራ ወታደሮቿን ልካ የሃገራቸውን የወሰን ክልል የጣሰች መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ኤርትራ ከአንድ ወር በፊት ጀምራ ወታደሮቿን ወደ ጅቡቲ መላኳንና ምሽግ እየቆፈረችና ሌሎችንም የመከላከያ ቦታዎችን እያጠናከረች መሆኑን ፕሬዚዳንት ኦማር ጊሌ በመግለጫቸው ላይ ጠቅሰዋል፡፡ የሁለቱ ሃገሮች ወታደሮች መፋጠጣቸውንና ጦርነቱ በማንኛውም ጊዜ ሊፈነዳ የሚችል መሆኑን የገለፁት ኦማር ጊሌ፣ የአፍሪካ ሕብረትና የአረብ ሊግ ጣልቃ ገብተው እንዲሸመግሉ መጠየቃቸውን አስታውቀዋል፡፡ ጊሌ በዚሁ መግለጫቸው ሁለቱ ሃገሮች ወደመጠፋፋት የሚያደርስ የኃይል እርምጃ እንዳይቀሰቅሱ፣ የአፍሪካ ሕብረትና የአረብ ሊግ ለረጅም ጊዜ የቆየውን የወሰን ክርክር እንዲሸመግሉ መልዕክት መላካቸውን አስታውቀዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ መግለጫ የሰጡት የአፍሪካ ሕብረትና የአረብ ሊግ ጉዳዩን የሚያጣራ ቡድን ወደዚያው በላከበት ወቅት ነው፡፡ ኤርትራ ለፕሬዚዳንት ጊሌ ንግግር እስከ ትላንት ማታ መልስ አልሰጠችም፡፡ በጅቡቲ አሜሪካና ፈረንሳይ በጅቡቲ የጦር ሰፈር እንዳላቸውና በተለይ ከፈረንሳይ ጋር የጋራ የመከላከያ ስምምነት እንዳላቸው ይታወቃል፡፡ ኤርትራ እ.ኤ.አ በ1990ዎቹ ከየመን ጋርና ከሱዳን ጋር፣ ከ1998 - 2000 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ጋር ጦርነት ማድረጓ ይታወሳል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |