Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow በድሬዳዋ አንድ ተሽከርካሪ...
በድሬዳዋ አንድ ተሽከርካሪ... Print E-mail
Wednesday, 07 May 2008
በድሬዳዋ አንድ ተሽከርካሪ በውሃ ተወስዶ ሁለት ሰዎች ሞቱ

ጀልዴሳ ከተባለ የገጠር ቀበሌ አምስት ስዎች አሳፍሮ ወደ ድሬዳዋ ይጓዝ የነበረ ቶዮታ ላንድ ክሩዘር መኪና ከትናንት በስቲያ በደራሽ ውሃ ሙላት በመውሰዱ በውስጡ ከነበሩት መካከል ሁለቱ ሲሞቱ አንድ ሰው በጽኑ መቁሰሉን የድሬዳዋ ጊዜያዊ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ተሽከርካሪው በደራሽ ውሃ ሙላት የተወሰደው ለገደኒ የተባለውን ወንዝ በማቋረጥ ላይ እንዳለ መሆኑን፣ በውስጡ በገጠር ቀበሌዎች የክትባት አገልግሎት ሰጥተው ወደ ድሬዳዋ በመመላለስ ላይ የነበሩ የጤና ባለሙያዎች እንደነበሩ ተገልጿል፡፡

(አዲስ ዘመን ሚያዚያ 28 ቀን 2ዐዐዐ)

ፖሊስና የህብረተሰቡ ተሳትፎ

ፖሊስ በተለያዩ ወቅቶች የሚፈፀሙ ዓይነትና መጠናቸው የበዛ፣ ወንጀሎችን ለመከላከል የሚያደርገው ጥረት ያለ ሕብረተሰቡ የላቀ ተሳትፎ ውጤታማ ሊሆን እንደማይችል ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በአሁኑ ወቅት የሚፈፀሙ ወንጀሎች ዓይነታቸውና መጠናቸው መብዛቱን፣ በተጠናከረ መልኩ የሚፈፀሙትን ወንጀሎች ለመከላከልና ለመቆጣጠር የህብረተሰቡ ድጋፍ ይበልጥ አስፈላጊ መሆኑን ፖሊስ አስገንዝቧል፡፡

(ኢዜአ)

በልዩ ፍላጐት መምህርነት የሰለጠኑ ተመረቁ

ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሰና ትምህርት ቤት የገቡ ሕፃናት ችግራቸውን በትክክል ለመረዳት የልዩ ፍላጐት መምህራን እንደሚያስፈልጉ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የተለያዩ የአካል ጉዳት ያለባቸው ሕፃናት የሚረዷቸውንና በቅርበት የሚንከባከቧቸውን መምህራን እንደሚፈልጉ፣ የቋንቋና የመግባባት አቅም ማነስ እንደዚሁም የአካባቢ እና የባህል ተፅእኖ ያሉባቸውን ተማሪዎች በመምህራንና በቤተሰብ ልዩ ልዩ ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባና፣ ለዚህም የሚሆኑ የልዩ ፍላጐት ትምህርት መምህራን ማሰልጠኛ ተቋም በዘርፉ ያሰለጠናቸውን 15 መምህራን በምስክር ወረቀት አስመርቋል፡፡

(ኢዜአ)

ወጣቱ ትውልድ ለአገሩ ቀናኢ እንዲሆን ፈጣሪን መለመን ነው

በአዲሱ ሚሊኒየም ወጣቱ ትውልድ ለአገሩ ቀናኢና ኢትዮጵያን የሚገነባ እንዲሆን ጥረት ከማድረግ በላይ ፈጣሪን እንለምናለን ሲሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አስታወቁ፡፡

“አገር ገንቢው ወጣት ትውልድ በማሊኒየሙ መንፈሳዊ ተግባሩ የበረታና በአካል የነቃ እንዲሆን እግዚአብሔር አምላክን እንለምናለን”፣ የኢትዮጵያ ራዕይና የወደፊት ተስፋ የሆነው ወጣቱ ትውልድ በአእምሮው የበቃ እንዲሆን ለማድረግ ፆም ፀሎት እንደሚያስፈልገውም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ገልፀዋል፡፡

(አዲስ ዘመን ሚያዚያ 27 ቀን 2ዐዐዐ)

የቱርክ ጤና ባለሙያዎች ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ ለበርካታ ሰዎች ህክምና ሰጠ

የቱርክ ጤና ባለሙያዎች ቡድን የጤና ዘርፉን ለማገዝ በአድዋ ከተማና አካባቢው ለሚገኙ ሦስት ሺ ነዋሪዎች የውስጥ ደዌ የህክምና አገልግሎት መስጠታቸውን የከተማው ማስታወቂያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ከከተማዋ አስተዳደር ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ጋር በመተግበር ህክምናውን የሰጠ ሲሆን፣ አብዛኛዎቹ ተጠቃሚዎች ሕፃናት፣ ሴቶችና አዛውንቶች መሆናቸውን፣ የተሰጠው ህክምና ከ6ዐዐ ሺ በላይ እንደሚገመት፣ እንዲሁም በአድዋ ሆስፒታል የሚታየውን የሕፃናት መኝታ ክፍል ጥበት ለማቃለል የ7ዐዐ ሺ ብር እርዳታ መለገሱን ገልጿል፡፡

(ኢዜአ)
 
< Prev   Next >