Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow ሕዝቡ የልማት ጥሙን ካረኩለት ይተባበራል
ሕዝቡ የልማት ጥሙን ካረኩለት ይተባበራል Print E-mail
Wednesday, 07 May 2008
አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን የአፍሪካ መዲና ናት፡፡ የበርካታ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች መናኸሪያ ናት፡፡ ይሁን እንጂ በልማትና በተወሳሰቡ ችግሮች የተዘፈቀች ናት፡፡ ከመሬት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ሙስና የሚፈጸምባት ሆናለች፡፡ ድህነት በጣም ተንሰራፍቶባታል፡፡ በዚህ ሁኔታ ላይ የምትገኘውን አዲስ አበባን በከንቲባነት ለማስተዳደር ብልህነትን፣ አርቆ አስተዋይነትን፣ ቆራጥነትን፣ ከሙስና መጽዳትን፣ ብቃት ያለው አመራር ሰጪነትን ያስፈልጋል፡፡ ከተማን የማስተዳደር ልምድ ያካበተ ሰው ሊሆን ይገባል፡፡  

በሪፖርተር ጋዜጣ ሚያዚያ 26 ቀን 2000 እትም ፖለቲካ ገጽ "ኩማ ወደ ማዘጋጃ ቤቱ እያቀኑ ነው" በሚል ርዕስ ጽሑፍ ወጥቷል፡፡ አቶ ኩማ ብዙ ሥራና ኃላፊነት እንደሚጠብቃቸው ከወዲሁ መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከሁሉ አስቀድሞ ግን ቢሯቸውን ለጋዜጠኞች ክፍት ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ በዚህ በኩል ከንቲባ ብርሃነ ደሬሳን በጥሩ አብነት መጥቀስ ይቻላል፡፡

ከዚህም ሌላ በሕዝቡ መሃል እየተገኙ ችግሩንና ብሶቱን ሊረዱለትና መፍትሄም ሊፈልጉለት ይገባል፡፡ በውዝፍነት የሚጠብቋቸውን ጉዳዮች በአፋጣኝ የመፍታትና ከሕዝብ ጋር የመቀላቀል ችሎታ ማዳበር አላባቸው፡፡ በተዛባ መልኩ የተከናወነው የሠራተኛ ቅነሳ በአስተዳደሩ ከፍተኛ የሆነ የባለሙያ እጥረት እንደፈጠረ እየታየ ነው፡፡ ለእነዚሀ ችግሮች መፍትሄ መስጠት የአቶ ኩማ ሥራ ይሆናል፡፡

ሕዝቡ የሚፈልገው ልማት ነው፡፡ መልካም አስተዳደር ነው፡፡ አድሎአዊነት የሌለበት ፍትሃዊ ውሣኔ ነው፡፡ ይህን ካሟሉለት ሕዝቡ ይደግፋቸዋል፤ ይተባበራቸዋል፡፡
 
(ፈለቀ ኃይሉ፣ ከአየር ጤና)
 
< Prev   Next >