| በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ... |
|
|
| Thursday, 10 January 2008 | |
|
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዲዛይንና ሥነ ጥበብ ት/ቤት ተማሪዎች ትምህርት አቆሙ ሁሉንም ችግር በሰላም ፈትተነዋል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዲዛይንና ሥነ-ጥበብ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ከአስተዳደራዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ላለፉት ሁለት ቀናቶች ትምህርታቸውን አቆሙ፡፡ ትምህርት ቤቱ የተፈጠረውን ችግር በመነጋገር ስለፈታነው ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን ዛሬ ይጀምራሉ ብሏል፡፡ ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን ለማቆም ምክንያት የሆናቸው፣ ላለፉት አራት ወራት በትምህርት ቤቱ በኩል ተገዝቶ ይቀርብላቸው የነበረው የትምህርት መማሪያ ቁሳቁስ ሳይገዛላቸው የፈተና መፈተኛ ጊዜ ሰሌዳ በመውጣቱ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በፈተናው ወቅት የምናቀርበው ነገር ሳይኖር (ዲስፕሌይ) የፈተና ፕሮግራም በመውጣቱ፣ አግባብ አይደለም በሚል ፈተና እንደማንፈተንና የሚመለከተው አካል እንዲያውቅልን ትምህርታችንን ለማቆም ተገደናል ያሉት ተማሪዎቹ፣ አስተማሪዎች የሚሰሩትን ሥራ አዘዋቸው ቢሄዱም በማቴሪያል እጥረት ምክንያት ባለመስራታቸው የመማር ማስተማር ሂደቱ መስተጓጐሉን ተናግረዋል፡፡ ተማሪዎቹ ከአንደኛ ዓመት እስከ አራተኛ ዓመት መሆናቸውን ገልፀው፣ ትምህርታቸውን ከማቆማቸው በፊት በፅሑፍና በአካል በመገኘት ለትምህርት ቤቱ ኃላፊዎች ያለባቸውን ችግር ቢያቀርቡም መፍትሄ ማግኘት አለመቻላቸውንና በመጨረሻም ትምህርት የማቆም አድማ ለማድረግ መወሰናቸውን አብራርተዋል፡፡ ተማሪዎቹ ትናንትናና ከትናንት በስቲያ (ታህሳስ 21 እና 22 ቀን 2000 ዓ.ም) ያደረጉት የትምህርት ማቆም አድማ እንዳይቀጥልና የተማሪዎች ተወካዮችና ከከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር መመካከራቸውንና በዛሬው ዕለት የሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ ተገዝቶላቸው ትምህርታቸውን እንዲጀምሩ የሚል ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ትምህርት ቤቱ ለሪፖርተር ጋዜጣ ገልፀዋል፡፡ የማቴሪያሉ መግዢያ በሣይንስ ፋኩልቲ በኩል ስለሚተላለፍ ጊዜ ይወስዳል፡፡ ካለፈው ዓመት ተማሪዎች በተራረፈው ስሩ በማለት በአስተዳደሩ በደል ደርሶብናል ያሉት ተማሪዎቹ የበላይ ኃላፊዎች ሁኔታውን እንዳልሰሙና ከዚህ በኋላ አስፈላጊውን ክትትል እንደሚያደርጉ ቃል የገቡላቸው በመሆኑ፣ በዛሬው ዕለት ትምህርት የሚጀምሩ መሆኑን (ከተገዛላቸው) ተናግረዋል፡፡ ሁሉንም ነገር በሰላም ፈትተነዋል፡፡ በእርግጥ ተማሪዎቹ የማቴሪያል ችግር ስለነበረባቸው ይኸንን እርምጃ ሊወስዱ ችለዋል፡፡ ሌላ ችግር ግን የለብንም በማለት የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር አቶ ሙዜ አወል የተማሪዎቹ ጥያቄ አግባብ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ ዋናው ለችግሩ መንስኤ የሆነው ዩኒቨርሲቲው አዲስ የአገዛዝ ሲስተም በመዘርጋቱና ሲስተሙን ለተለያዩ የሙያ ትምህርት ቤቶች ለማዳረስ ጊዜ በመውሰዱ ችግሩ ሊከሰት መቻሉን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡ ወሬው ወደ ውጭና ወደ ሚዲያ ሲወጣ ይገናል እንጂ ጉዳዩ ቀላል ነው፡፡ ማቴሪያሉ ዛሬ (22/4/2000) ይገዛል፡፡ ትምህርትም ነገ ይጀመራል (ዛሬ..፡፡ ከዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንትና ከተማሪዎቹ ተወካዮች ጋር ተወያይተን ችግሩን ፈትተነዋል ብለዋል፡፡ በታምሩ ጽጌ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |