Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow የኤሌክትሪክ ኩባንያዎችን የሚደግፍ...
የኤሌክትሪክ ኩባንያዎችን የሚደግፍ... Print E-mail
Wednesday, 07 May 2008
የኤሌክትሪክ ኩባንያዎችን የሚደግፍ ፕሮጀክት ሥራ ላይ ሊውል ነው

በጋዜጣው ሪፖርተር

የአለም ባንክ አካል የሆነው ኢንተርናሽናል ፋይናንስ ኮርፖሬሽን ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ አገራት በአሌክትሪክ አቅርቦት ኢንቨስትመንት የሚሰማሩ ኩባንያዎችን የሚደግፍ አዲስ ፕሮጀክት ማዘጋጀቱ ታወቀ፡፡

በአፍሪካ የመብራት እጦትን በመቅረፍና አንድ አራተኛ በሚሆነው የአፍሪካ ህዝብ ዘመናዊ ኤሌክትሪክ በማቅረብ አለም አቀፍ ዘመቻ የተጀመረ ሲሆን የዘመቻው አንድ አካል የሆነው የመጀመሪያ ጉባኤ ትናንት ጋና ውስጥ መጀመሩን ባንኩ አስታውቋል፡፡

በዚህ አክራ ጉባኤ አለም አቀፍ የኤሌክትሪክ ኢንዱስትሪ፣ መንግስታት፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ ለጋሽ ድርጅቶች ወኪሎች የተሳተፉበት ሲሆን የጉባኤው አዘጋጆች ከመደበኛው የኤሌክትሪክ አቀራረብ ውጪ አዲስ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ ኃይል ለአፍሪካ በሚቀርብበት ሁኔታ ላይ ይወያያሉ፡፡

ይኸው ጉባኤ ባለፈው መስከረም ወር 'Lighting Africa' የተባለ ዘመቻ ቀጣይ ሲሆን ፕሮግራሙን የሚያስተባብረው አለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ነው፡፡ ይህ ኮርፖሬሽን የአለም ባንክ አካል ሆኖ የግሉን ዘርፍ ለመደገፍ ይንቀሳቀሳል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ኢንቨስተሮች በዘርፉ ለመሰማራት ፍላጎታቸውን እንዲያሳዩ ኢንተርናሽናል ፋይናንስ ኮርፖሬሽን በዕቅዱ ኩባንያዎች የራሳቸውን የቢዝነስ ዕቅድና የፋይናንስ ትብብር እንዲያደርጉ አስቧል፡፡

ኤሌክትሪክ ለኢኮኖሚና ለማኅበራዊ ዕድገት ያለው አስተዋጽኦ የላቀ መሆኑን የሚጠቁመው የባንኩ ሪፖርት የኤሌክትሪክ አቅርቦት መቋረጥ ለኢንዱስትሪ ክስረት የሚያጋጥም በመሆኑ አማራጭ መንገዶችን ማመቻቸት የግድ መሆኑ ታምኖበታል፡፡

'Lighting Africa' የተባለው ዘመቻ በዕቅዱ መሠረት እ.ኤ.አ በ2036 250 ሚሊዮን የአፍሪካ ህዝብ ከመደበኛ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ውጪ ዘመናዊ፣ ርካሽና ጎጂ ከሆነና በነዳጅ ከሚሰራ ኃይል ውጪ የሆነ አቅርቦት እንዲኖረው ለማድረግ ነው፡፡

በአፍሪካ ርካሽና በቀላሉ የሚገኝ ከብክለት ነፃ የሆነ ሃይል በአማራጭነት ማቅረብ በጣም አስፈላጊ መሆኑን የገለፁት፣ በዓለም ባንክ የኢነርጂ ሴክተር ስፔሻሊስት የሆኑት አኒል ከብኒል "መደበኛውን የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ማስፋፊያ እንደ መፍትሄ መጠበቅ ትክክለኛው አማራጭ አይደለም፡፡ የሃይል አቅርቦት ጉዳይ ግንዛቤ ያስገኘበት ጊዜ ላይ ነን" ብለዋል፡፡

የአፍሪካ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ የወቅቱን ቴክኖሎጂ ያልተከተለና በሙስና የተተበተበ በመሆኑ የአፍሪካን የኤሌክትሪክ ችግር ሊፈታ አይችልም፡፡ ይህንን ዕድል ያገኙት 26 ከመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው፡፡ አንዳንዴም በአንዳንድ አገሮችም መጠኑ ቀንሶ የዘርፉ ተጠቃሚ የሆኑት ከ5 በመቶ በታች ናቸው፡፡

ከኢነርጂ አቅርቦት ደካማ የሆነችው አፍሪካ በአመት በነዳጅ ዘይት በሚሰራ የሃይል አቅርቦት 40 ቢሊዮን ዶላር ታወጣለች፡፡ በአለም ባንክ አገላለጽ ይህን ያህል ወጪ የወጣበት ዘርፍ አቅሙ ደካማ፣ ጥረቱ አነስተኛና በካይ ነው ይላል፡፡

በነዳጅ ሃይል ከሚሰሩ መገልገያዎች መካከል ዋነኛው በኬሮሲን የሚሰሩ ማብሰያዎች የቤተሰቡን ወጪ ከ10 እስከ 30 በመቶ ይወስዳሉ፡፡  

የአለም ባንክ በአፍሪካ ለማስፋፋት የፈለገው አማራጭ ሃይል ብርሃን የሚያመነጨው (light emitting lodes) እና የፍሎረሰንት አምፖሎችን ነው፡፡ ሁለቱም ቴክኖሎጂዎች የሚጠቀሙት ሃይል ከሌሎች (አምፖሎች) አንፃር ሲታይ አነስተኛና በዋጋም ተመጣጣኝ ናቸው፡፡

ለዚህም ደግሞ የግሉ ዘርፍ ትልቅ ሚና ሊጫወት ይችላል ብሏል እንደ የኢንተርናሽናል ፋይናንስ ኮርፖሬሽን አለም ባንክ ተወካይ ገለፃ፡፡ በጋናው ጉባኤ የዓለም ባንክና ኮርፖሬሽኑ በአዲስ መልክ በሚፈበረኩ ሃይል ቆጣቢ መገልገያዎች ዲዛይን እና ፈጠራ ሽልማት ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በጉባኤው ላይ ለሙከራ ተብሎ ፓይለት ፕሮጀክቶች በጋና እና በኬንያ የተዘጋጀ ሲሆን በኢትዮጵያ፣ በታንዛኒያ እና በዛምቢያ ተጨማሪ ጥናቶች መካሄዱን ኮርፖሬሽኑ ገልጿል፡፡

ለኮርፖሬሽኑ አላማ ግብ መምታት ከአለም ባንኩ በተጨማሪ የተባበሩት መንግስታት ዲቭሎፕመንት ፕሮግራም፣ ኢንቫይሮመንት ፋሲሊቲ፣ በጃፓን እና በብሪታኒያ መንግሥት የተቋቋመው (Public private infrastructure Advisory Facility) አብረው እየሰሩ ናቸው፡፡
 
< Prev   Next >