Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow በነጋዴዎች በሸማቾችና በመንግሥት...
በነጋዴዎች በሸማቾችና በመንግሥት... Print E-mail
Wednesday, 07 May 2008
በነጋዴዎች በሸማቾችና በመንግሥት መካከል የጋራ መግባባት እንዲፈጠር ተጠየቀ

በቤዛዊት ሥዩም

የኢትዮጵያ የሰላም፣ የልማትና የዴሞክራሲ ሕዝባዊ የምክክር መድረክ ባለፈው ሐሙስ ሚያዚያ 23 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በሂልተን ሆቴል በኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበትና የኑሮ ውድነት ዘላቂ የመፍትሄ ሃሳቦች በሚል ባካሄደው ውይይት ላይ እንደተገለፀው የኑሮ ውድነት በህብረተሰቡ ላይ እየፈጠረ ያለውን ጫና ለመቀነስ በነጋዴዎች፣ በሸማቾችና በመንግሥት መካከል የጋራ መግባባት መፍጠር ያስፈልጋል፡፡

በውይይቱ በርካታ ማህበራትና ባለሙያዎች በዋጋ ንረቱ ላይ የመከሩ ሲሆን የዋጋ ንረቱ አነስተኛ አቅም ያላቸውን የሕብረተሰብ ክፍሎች እየጎዳ በመሆኑ ለውጥ የሚያመጣ እርምጃ መውሰድ እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል፡፡

የአዲስ አበባ ፎረም ተወካይ አነስተኛ አቅም ባላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች ላይ የዋጋ ንረት ያደረሰውን ተፅእኖ አስመልክቶ እንደገለፁት አነስተኛ አቅም ያላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች ክፉኛ እየተጎዱ ነው፡፡ አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል በሚጠቀምበት በስንዴ፣ በጤፍ፣ በቆሎ እና በማሽላ ላይ ያለው ከፍተኛ የዋጋ ንረት ፈታኝ ሆኖባቸዋል፡፡

የግብርና ኢኮኖሚው አድጓል ቢባልም ጐልቶ የመጣው ግሽበት ከግብርናው እድገት ጋር እንደማይጣጣም ገልፀዋል፡፡ "የዋጋ ንረቱን ለመቆጣጠር በተወሰኑ የምግብ ምርቶች ላይ በዱቄት ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስና የተርን ኦቨር ታክስ ቢነሳም በከተማ ግብርናና በከብት ማደለብ ለተሰማሩት የሕብረተሰብ ክፍሎች በተረፈ ምርቶቹ ላይ ባለመነሳቱ እየተጎዱ ስለሆነ መንግሥት ሊያየው ይገባል" ብለዋል፡፡ በስንዴ ስርጭት ላይ ችግር እንዳለ የገለፁት ተወካይ በእርሻ ሰብል ላይ ያለው ውጣ ውረድ እንዲታይም ጠይቀዋል፡፡

የዋጋ ንረቱን ለማርገብ በሚል የተጨማሪ እሴት ታክስና የተርን ኦቨር ታክስ ከተነሳላቸው የምግብ እህሎች አንዱ በሆነው ስንዴ መጀመሪያ አካባቢ በኩንታል እስከ 8ዐ ብር የሚደርስ የዋጋ ቅናሽ የነበረው ቢሆንም አሁን ከበፊቱ በበለጠ ዋጋ ጨምሯል፡፡

የኢትዮጵያ ዱቄት አምራች ማህበር ተወካይ እንዳሉት ከስንዴ እጥረት ጋር በተያያዘ የስንዴ ዋጋ በመጨመሩ አንዳንድ ፋብሪካዎች ወደ መዘጋት በመሄድ ላይ ናቸው፡፡ የስንዴ ምርት እጥረት በመኖሩና ያለውም በኩንታል በ475 ብር በመድረሱ ለችግር መጋለጣቸውን ጠቁመዋል፡፡ የስንዴው ጥራት አነስተኛ በመሆኑ  አንድ ኩንታል ዱቄት ለማምረት ከ130 እስከ 140 ኪ.ግ ስንዴ እንደሚያስፈልግና የሠራተኛ የኤሌክትሪክና ሌሎች ወጪዎች ተደምረው አቅርቡ በሚባለው ዋጋ ማቅረብ አዳጋች እንደሆነባቸው ተናግረዋል፡፡

የማህበሩ አባላት የስንዴ ግብአት ባለመኖሩ በከፍተኛ ዋጋ ገዝተው በትክክለኛ ዋጋ ለመሸጥ በሚያደርጉት ጥረት ዋጋውን ጠብቃችሁ በ520 ሽጡ እየተባሉ መገደዳቸውንና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በውይይት መድረኩ የነበሩት ተሳታፊ በበኩላቸው በምግብ እህሎች ላይ ታክስ ተነስቶ በአንዳንድ ነጋዴዎች የሚደረግ አላግባብ የዋጋ ጭማሪን ለመከታተል የሚያስችል የዋጋ ቁጥጥርን የሚፈቅድ ደንብና ሕግ በንግድ ሕጋችን ላይ ቢኖርም በትክክል ተግባራዊ እየሆነ አይደለም፡፡ ከውጪ የሚገባ እቃ ሲመጣ ጥራቱ በደረጃ መዳቢ እንደማይታይና አስመጪዎችም ምርቱ የተገዛበት ዋጋ የትራንስፖርት ልዩ ወጪያቸውን በግልፅ በማስቀመጥ ማከፋፈል ያለበትን ዋጋ እንደማያሳውቁ ገልፀዋል፡፡ የሚመለከታቸው አካላት ዋጋ የመለካት ሂደት ተግባራዊ እንዲያደርጉም=ጠይቀዋል፡፡ የውጭ ምንዛሬ ሲፈቀድ አስፈላጊ በተለይ ከምግብ ምርቶች ጋር=ተያያዥና ወቅታዊ ለሆኑ ጉዳዮች እንዲውል=ጠይቀዋል፡፡

የአዲስ አበባ እህልና ወፍጮ ባለንብረቶች ማህበር ተወካይ በበኩላቸው አገራችን የግብርና አመራረት ዘይቤ ምርታማ አለመሆኑንና በሄክታር ያለውን ምርታማነትና የምግብ ይዘት በማየት በተሻለ=ቴክኖሎጂ ማምረት እንደሚገባ ገልፀው የአመራረትና የአመጋገብ ባህላችን ሥር=ነቀል ለውጥ ያስፈልገዋል ብለዋል፡፡

ምርቶቹን ለማሳደግ የምንጠቀመው ቴክኖሎጂ ማሳደግና=ከሌሎች አገሮች አንፃር በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ የተሻለ የምርት አቅርቦት=ያላቸውን ቴክኖሎጂዎች መጠቀም ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የምግብ ምርቶች ላይ=የሚደረጉት ቁጥጥሮችና የሚወሰዱ=እርምጃዎች ችግሩን እያባባሱ እንደሆነ ገልፀው ጅምላ ሻጮች=ላይ ቁጥጥር እንደሌለና ቁጥጥሩ በቸርቻሪዎች ላይ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በመሳለሚያ የእህል መሸጫ አንድ ኩንታል እህል መሸጫ ዋጋ ላይ ቁጥጥር እንደሌለ ሆኖም በቸርቻሪዎች ላይ ተቆጣጣሪዎች ጫና እያሳደሩባቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ብዙ ወፍጮ ቤቶች ባለቤቶች በተወሰነላቸው ዋጋ ካልሸጠ ንግዳችሁ ይዘጋል እየተባሉ ሲሆን ባለንብረቶች በበኩላቸው ቁጥጥሩ ከመሠረቱ እንዲሆን ደረሰኝ እንዲዘጋጅ ጠይቀዋል፡፡ ቁጥጥሩም ንግድና ኢንዱስትሪን ብቻ ሳይሆን ነጋዴዎችንና የንግድና የዘርፍ ማህበራትን ያካተተ እንዲሆን ጠይቀዋል፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ከጥራትና ደረጃዎች መዳቢዎች ባሥልጣን ጋር በመተባበር ርካሽ ምርቶችን እገዳና በዋጋ ንረቱ አኳያ ለምግብነት የሚውሉ ምርቶች ላይ የተሠማሩ ፋብሪካዎች ቅድሚያ ትኩረትና ማበረታቻ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ወጣቶች ፎረም ተወካይ በግብርና ስርዓቱ ምርታማነት ዙሪያ ትኩረት አለመሰጠቱ ገልፆ ካለንበት የአገራችን ነባራዊ ሁኔታ አንፃር የግብርና ክፍለ ኢኮኖሚ ወደ ተሻለ ደረጃ እየተሸጋገረ መዋቅራዊ ለውጥ እየታየ ቢሆንም በፍላጎት ግፊት እንደተዋጡ ገልጿል፡፡ ግብርናው ባደገበት መጠን በበለጠ ፍላጎት ማደጉና በዓለም አቀፍ ደረጃ የዋጋ ግሽበት መኖሩ በኢትዮጵያ ላይ ተፅእኖ ፈጥሯል፡፡ ታክስ ከተነሳ በኋላ በትክክል ተግባራዊ ባለመሆኑ ችግሩን ማባባሱ፤ ታክስ መነሳቱ ለነጋዴው የተሻለ እድል እንደፈጠረ ጠቁሞ ቁጥጥር በሚያደርጉ አካላት ድክመት እንዳለና ተግባራዊነቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እንዲከታተለው ጠይቋል፡፡ ሕብረተሰቡን የሚያሳትፍ የቁጥጥር ስርዓት መዘርጋት ተገቢ መሆኑንና ወቅቱን የጠበቀ+የግንዛቤ መድረክ እንዲመቻች አሳስበዋል፡፡

ከአዲስ አበባ ዳቦ ቤቶች ማህበር የተወከሉት የኮሚቴ አባል+እንደተናገሩት የተርን ኦቨርና የተጨማሪ እሴት ታከስ በመነሳቱ በዱቄት ዋጋ ምክንያት ጨምሮ+የበረው የዳቦ ዋጋ ቀንሷል፡፡ ታክስ ከመነሳቱ በፊት ስንዴ በኩንታል ብር+535 የነበረ ሲሆን ታክሱ ቢቀነስም በአሁኑ ሰዓት ከ78ዐ+ብር ያላነሰ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የዚህ ዓመት ምርት+በተሰበሰበበት በጥቂት ወራት ከፍተኛ የስንዴ እጥረት መኖሩን ጠቁመው የእጥረቱን ትክክለኛ ምክንያቱን ማወቅ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡ በአርሶ አደሩ የተያዘ ምርት ካለም ወደ ገበያ እንዲያወጣ ማበረታቻ መስጠትና በምርት ዙሪያ ሠፊ ቁጥጥር ማድረግ ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የዱቄት ዋጋ በመጨመሩ የተዘጉ ዳቦ ቤቶች መኖራቸውን ገልፀው በዚህ ሁኔታ የሌሎች ዳቦ ቤቶች መቀጠል አጠራጣሪ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ አሁን በተቀመጠው ዋጋ አንድ ዳቦ አምርቶ ለማቅረብ ካለው ወጪ አንፃር ስንዴ 8ዐዐ ብር በመግዛት 5ዐ ግራም ዳቦ በ2ዐ ሳንቲም በመሸጥ በ5ዐዐ ብር ማጣራት ፈታኝ እንደሆነባቸው ገልፀዋል፡፡
 
< Prev   Next >