Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 20th
Home arrow Sections arrow ዴሞክራሲያዊ ኪዳን ማዕከላይ...
ዴሞክራሲያዊ ኪዳን ማዕከላይ... Print E-mail
Sunday, 11 May 2008
ዴሞክራሲያዊ ኪዳን ማዕከላይ ኮሚቴና ሥራ አስፈፃሚ አዋቀረ

በየማነ ናግሽ

ባለፈው ሰኞ የተጀመረው የኤርትራ ዴሞክራሲያዊ ኪዳን ጉባኤ ማዕከላይ ኮሚቴና የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በማወቃቀር አጠናቀቀ፡፡

የ13 ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥላ ፓርቲ የሆነው የኤርትራ ዴሞክራሲያዊ ኪዳን ለአንድ ሣምንት የቆየው ባለፈው ሰኞ የተጀመረው ጉባኤ ዛሬ እንደሚጠናቀቅ ታውቋል፡፡ ጉባኤው በተሳካ ሁኔታ መካሄዱና ያወዛግባሉ የተባሉ ነጥቦችም ያለምንም ልዩነት ሁሉም ፓርቲዎች ተስማምተው ቻርተሩንና ህገደንቡን ማፅደቁን የጉባኤው አመቻች ኮሚቴ ሊቀመንበር አቶ መንግሥተአብ አስመሮም ለሪፖርተር ጋዜጣ ገልፀዋል፡፡

እንደ አቶ መንግሥተአብ ገለፃ፣ የጥምር ድርጅቱ (ኪዳን) ማዕከላይ ኮሚቴና ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ተቋቁመዋል፡፡ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ 13 አባላት ያካተተ ሲሆን ከእያንዳንዱ ድርጅት አንድ ሰው መወከሉን አቶ መንግሥተአብ ጠቁመዋል፡፡ እንዲሁም የእናት ድርጅቱ ማዕከላይ ኮሚቴ 26 አባላት ያሉት ሲሆን ከእያንዳንዱ ድርጅት ሁለት ሁለት አባላት ተመርጠው ተዋቅሯል፡፡

ጉባኤኛው አቶ አብደላ መሐመድን የማዕከላይ ኮሚቴ ሊቀመንበር አድርጎ የመረጠ ሲሆን፣ አቶ ተወልደ ገብረሥላሴ የሥራ አስፈፃሚ ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡

አቶ መንግስተአብ የስደት መንግሥት ማቋቋምን አስመልክቶ “እስከ አሁን አልተነሳም፣ ለወደፊቱ ሊነሳ” እንደሚቻልና የኢሳያስ መንግሥት ለማስወገድ የትጥቅ ትግል ጨምሮ በሁሉም ዓይነት የትግል ስልቶች ለመጠቀም ስምምነት ላይ መደረሱን ገልፀዋል፡፡

 
< Prev   Next >