Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 06th
Home arrow Sections arrow የተጭበረበረ የክትባት ማስረጃ ይሸጣል
የተጭበረበረ የክትባት ማስረጃ ይሸጣል Print E-mail
Sunday, 11 May 2008
በአሰግድ ተፈራ

ለውጪ አገር ጉዞ ክትባት የሚወስዱ የዓለም አቀፍ የክትባት ማዕከል ደብተር በግለሰቦች እየታተመ እስከ 200 ብር ይሸጣል፡፡ የማዕከሉ ኃላፊ ሲስተር መሰለች ከተማ ችግሩ የቆየና ሊቆም ያልቻለ መሆኑን ይገልፃሉ፡፡

“በመላው ዓለም የፀና የክትባት ምስክር” የሚባለው የክትባት ደብተር ኢሚግሬሽን፣ ማዕከሉ ፊት ለፊት፣ በተለያዩ ሱቆች ውስጥና ቦሌ ሚካኤል አካባቢ እስከ 250 ብር ድረስ ይሸጣሉ፡፡

ሲስተር መሰለች ደብተሩ ፎርጅድ እየታተመ ግለሰቦች ሲነግዱበት የቆየ፣ የተለያየ ርምጃ ቢወሰድም ሊቆም ያልቻለ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በማዕከሉ ፊት ለፊት ይህንኑ የሚሰሩ ወደ ማዕከሉ ለክትባት የሚመጡትን በመያዝ ወረፋ አለ፣ በቀን የሚስተናገደው 50 ሰው ብቻ ነው፣ ተመዝግበው የቆዩ አሉ በማለት በማታለል ለአገልግሎቱ 42 ብር ብቻ የሚከፈልበትን ደብተር ከ80 ብር ጀምሮ እስከ 250 ብር መሸጡ የተለመደ ነው፡፡

የማዕከሉ ኃላፊ “በማጭበርበር የተያዙ ወዲያው ተለቅቀው ወደ ቀድሞ ማጭበርበር ስራቸው ይመለሳሉ፡፡ በእኛ በኩል አገልግሎት ከመስጠት ውጪ የምናደርገው ነገር የለም” ብለዋል፡፡

በቦሌ የአየር ማረፊያ ቁጥጥር ሲጀመር ፎርጅድ የክትባት ማረጋገጫ የያዙ ተጓዦች መገኘታቸውን የገለፁት ሲስተር መሰለች በአሁኑ ሰዓት የኳራንቲ ቁጥጥር ስለሚደረግ በየቀኑ ፎርጅድ ደብተር የገዙ ወደ ማዕከሉ ለአቤቱታ እንደሚመጡ ተናግረዋል፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ ኃላፊዎችን ለማነጋገር ማዕከሉ አካባቢ ስንደርስ “የክትባት ማረጋገጫ ደብተር ትፈልጋላችሁ ሰማንያ ብር ክፈሉ፡፡ እነሱ (ማዕከሉ) የዛሬ አገልግሎቱን ጨርሷል” በማለት አንዱ አጠገባችን ተጠግቶ ጠይቆናል፡፡ “ማህተም አለው፡፡ ከውስጥ በሀምሳ ብር እንገዛዋለን፡፡ ስማችሁን ጽፋችሁ መሄድ ብቻ ነው” አለን፡፡ ለሲስተር መሰለች ይህንን ስንገልፅላቸው “ከማዕከሉ የሚወጣ ደብተር የለም፡፡ ፎርጅድ እያሳተሙ ነው፡፡ ማዕከላችን ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ ሥራ ይሰራል” በማለት ሕገወጦቹን ህብረተሰቡ እንዲቃወም ጠይቀዋል፡፡ 
,/font.
 
< Prev   Next >