Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Aug 29th
Home arrow Sections arrow ጤፍ 800፣ ሽምብራ በጨረታ 620 ብር ደረሰ
ጤፍ 800፣ ሽምብራ በጨረታ 620 ብር ደረሰ Print E-mail
Sunday, 11 May 2008
በአሰግድ ተፈራ

መንግሥት ህገወጥ ነጋዴዎች ለመቆጣጠር ግብረ ሃይል ቢያቋቁምም የእህልና የተለያዩ የምግብ ሸቀጣች ዋጋ እያሻቀበ መሆኑ ተጠቆመ፡፡ የአዲስ አበባ እህል ነጋዴዎች ማህበር እየታየ ያለውን የዋጋ ንረት ደላሎች የሚፈጥሩት ማዕበል ብሎታል፡፡
ከተለያዩ አቅጣጫዎች ጤፍ ወደ ገበያ መግባቱ አለመቀነሱን የእህል ደላሎች ገልፀዋል፡፡ ዋጋው ግን ማሻቀቡን ተናግረዋል፡፡ በመሳለሚያ የእህል በረንዳ በመገኘት ለማረጋገጥም ችለናል፡፡

የአድአ ማኛ ጤፍ እስከ ትናንት በስቲያ ድረስ አንደኛ ደረጃ የሚባለው በኩንታል 8ዐዐ ብር ነበር፡፡ የብቸኛ ነጭ (መለስተኛ) ጤፍ 760 ብር ሲሆን በጥቅሉ የጤፍ ዋጋ ከ700 እስከ 800 ብር እንደነበር ተዛውረን ተመልክተናል፡፡ የአዲስ አበባ የእህል ነጋዴዎች ማህበርም አረጋግጧል፡፡

ወ/ሮ አበራሽ ይገዙ የተባሉ ሸማች እንጀራ ስለሚሸጡ በየቀኑ የጤፍ ገበያን እንደሚከታተሉ ይገልፃሉ፡፡ እሳቸው እንደሚሉት፣ የዋጋ ንረትን ተከትሎ መንግሥት ግብረ ኃይል ሲያቋቁም 500 ብር ገብቶ የበረው የብቸና ጤፍ በአሁኑ ወቅት 760 ብር መድረሱ አስደንጋጭ ነው፡፡

የእህል ደላላ መሆናቸውን የሚገልፁት አቶ ይማም እንድሪስ ግብረ ሃይሉ ከተቋቋመ በኋላ ወፍጮ ቤቶች እንደቀድሞ እህል አያከማቹም፡፡ ጤፍ ከየአቅጣጫው ይገባል፡፡ በረንዳ ከተራገፈ በኋላ ሸማች ሳይገዛው የት እንደሚሄድ ግልፅ ሊሆንላቸው እንዳልቻለ ይገልፃሉ፡፡

የአዲስ አበባ እህል ነጋዴዎች ማህበር ዋና ፀሐፊ አቶ ነጋሽ ደበሌ እየታየ ያለውን የዋጋ ጭማሪ “ማዕበል” ብለውታል፡፡ የመኪና ላይ ደላሎች ሆን ብለው የሚፈጥሩት የገበያ ግርግር በመሆኑ ቁጥጥር ሊደረግበት እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡
“እየታየ ያለው የእህል የዋጋ ንረት ከጀርባው ሌላ ተልዕኮ አለው፡፡ በአሁኑ ወቅት የእህል እጥረት ያለ አይመስለኝም” ብለዋል፡፡ አያይዘውም ችግሩና ችግር ፈጣሪዎቹ ሊጠኑ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ሽምብራ ወደ ሩቅ ምስራቅና መካከለኛ ምስራቅ አገሮች እንደሚላክ ያመለከቱት አቶ ነጋሽ በወር ጊዜ ውስጥ የሽምብራ ዋጋ ከመቶ ብር በላይ ጭማሪ እንዳሳየም ገልፀዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት 620 ብር መሸጡን፣ በየዕለቱም በህገ ወጥ ጨረታ ዋጋው ማሻቀቡንም አስረድተዋል፡፡

ለኬክ ምግብነት በከፍተኛ ደረጃ እየተፈለገ ያለውን ሽምብራ ከጠዋቱ 2 ሰዓት በኋላ በብዛት ማግኘት አይታሰብም፡፡ በሸመታ ላይ የነበሩ አስተያየት ሰጪ “ሽምብራ ቢያንስ ሽሮና ቆሎ ሆኖ ቢበላ ሌላ አማራጭ ነውና ከዓለም የምግብ እጥረት አንፃር ሌሎች አገሮች በእህል ምርቶች ላይ የወሰዱት የጥንቃቄ ርምጃ ሊወሰድ ይገባል” ብለዋል፡፡
 
< Prev   Next >