| የደቡብ ክልል ምክትል ኘሬዚዳንት... |
|
|
| Sunday, 11 May 2008 | |
|
የደቡብ ክልል ምክትል ኘሬዚዳንት በግምገማ ከኃላፊነታቸው ተነሱ
በጋዜጣው ሪፖርተር የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ምክትል ኘሬዚዳንትና የአቅም ግንባታ ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ ፀጋዬ ማሞ “በስነ ምግባር ችግር” ተገምግመው ከኃላፊነታቸው ተነሱ፡፡ አቶ ፀጋዬ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉ ሲሆን ከሥነ ምግባር ችግር ጋር በተያያዘ ሰሞኑን በተደረገ ግምገማ የቀረበባቸውን ድክመት መቀበላቸውን የክልሉ ምንጮች አስረድተዋል፡፡ በዚህም ሳቢያ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ተወስኗል፡፡ አቶ ፀጋዬ የደኢህዴን እና የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ነበሩ፡፡ በተያያዘም ሰሞኑን በተካሄደው የደኢህዴን ግምገማ ላይ የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ ለብአዴን ተፅዕኖ የፓርቲውን አባላት አጋልጠዋል፤ በሚል መገምገማቸውን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ፓርቲው በሌሎች ተጨማሪ ሦስት የክልሉ የሥራ ኃላፊዎች ላይ ተመሳሳይ እርምጃ የወሰደ መሆኑም ታውቋል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |