| ከባለሥልጣኑ ሥራ የተረከቡ የቻይና... |
|
| Friday, 11 January 2008 | |
|
ከባለሥልጣኑ ሥራ የተረከቡ የቻይና ኩባንያዎች ቁጥር ዘጠኝ ደረሰ በአገሪቱ ውስጥ የሚካሄደውን የመንገድ ሥራ ግንባታዎች ለማከናወን ከዚህ ቀደም ጨረታ አሸንፈው ስራ ከጀመሩት የቻይና ኩባንያዎች ሌላ የቻይና የመገናኛና የግንባታ ኩባንያ /ሲ.ሲ.ሲ.ሲ/ የተባለ አዲስ ኩባንያ የ645 ሚሊዮን ብር የመንገድ ሥራ በመረከብ ዘጠነኛው የቻይና ኩባንያ ሆነ፡፡ የመንገድ ግንባታውና የዲዛይን ሥራ የቻይና የመገናኛና የግንባታ ኩባንያ የተረከበው ከአላማጣ - መሆኒ - ሄዋኔን ያለውን የ114 ኪ.ሜ. መንገድ ሥራ ነው፡፡ ኩባንያ ቀደም ብሎ 8 የሚሆኑ የቻይና ኩባንያዎች ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ የሚሆን የመንገድ ሥራዎችን መረከባቸው ታውቋል፡፡ ኩባንያው ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ጋር ባለፈው ሣምንት ውል የተፈራረመ ሲሆን ይህንን ውል ከሌሎች የመንገድ ሥራ ውሎች የሚለየው አሸናፊው ኩባንያ የመንገድ ግንባታውን ብቻ ሣይሆን የዲዛይን ሥራውንም ደርቦ እንደሚሠራ መደረጉ ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የኢንፎርሜሽንና የህዝብ ግንኙነት አገልግሎት ኃላፊ አቶ ሳምሶን ወንድሙ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለፁት የመንገድ ግንባታና የዲዛይን ሥራ በጣምራ እንዲሠራ ማድረጉ አዲስ አሠራር ሲሆን ጊዜን ለመቆጠብና ሥራውን በአግባቡ ለማሠራት ጠቀሜታ አለው፡፡ በአዲሱ የቻይና ኩባንያ የሚሰራው መንገድ ከዚህ በፊት በጠጠር መንገድ ደረጃ የነበረ ሲሆን መንገዱ በአፋርና በትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኝ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡ በኮንትራት ውሉ መሠረት የመንገዱ ግንባታ በሦስት ዓመት ውስጥ የሚጠናቀቅ ሲሆን የግንባታ ወጪውንም የኢትዮጵያ መንግሥት የሚሸፍን ይሆናል፡፡ በመንገድ ልማት ኘሮግራም ከታቀዱትና በዚህ መሥመር ከሚገኙት ኘሮጀክቶች ውስጥ ከአዲስ አበባ ጣምራ በርና ከኮምቦልቻ ወልድያ ያሉት መንገዶች ግንባታ ይገኛሉ፡፡ በዳዊት ታዬ |
| < Prev |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |