| ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ነገ ከነጋዴው... |
|
|
| Sunday, 11 May 2008 | |
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ነገ ከነጋዴው ኅብረተሰብ ጋር ይወያያሉበታምሩ ጽጌ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የንግዱን ኅብረተሰብ ነገ ግንቦት 4 ቀን 2000 ዓ.ም በጽሕፈት ቤታቸው የጉባኤ አዳራሽ ያወያያሉ፡፡ ከኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትሩና ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት የንግዱ ማህበረሰብን እንዲያወያዩ የቀረበላቸውን ጥያቄ ተቀብለው በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በኩል እንዳረጋገጡላቸውና ውይይቱም ነገ እንደሚካሄድ የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው አየነው ለሪፖርተር ጋዜጣ ገልፀዋል፡፡ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የተመሠረተበትን አንደኛ ዓመትና፣ በአገራችን የንግድ ምክር ቤት የሥራ ሂደት የተመሠረተበትን 60ኛ ዓመት እያከበረ ባለበት ወቅት የመንግሥት አካላት የንግዱን ማህበረሰብ ለማወያየት ፍቃደኛ መሆናቸው እንዳስደሰታቸው ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡ መንግሥትና ኅብረተሰቡ ከንግዱ ማኅበረሰብ ምን ይጠብቃል? የንግዱ ማህበረሰብ ምን እየሠራና ምንስ ይቀሩታል? ምን እንዲያደርግስ ይጠበቅበታል? መንግሥት ለንግዱ ማኅበረሰብ ምን ማድረግ አለበት? የሚሉትና ሌሎችንም ጥያቄዎች በማንሳት ሰፊ ውይይት እንደሚደረግ አቶ ጌታቸው ገልፀዋል፡፡ በትናንትናው ዕለት (ግንቦት 2 ቀን 2000) 306 አባላት ያሉት የምክር ቤቱ ጠቅላላ ጉባኤ እንደተካሄደ የገለፁት ፕሬዚዳንቱ በጉባኤው ላይ የተገኙት አባላት፣ ተጋባዢ እንግዶች፣ ከተለያየ የዘርፍ ማኅበራት የተወከለ አባላትና ሌሎች ተጋባዦች እንደሚገኙና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይም ውይይት እንደሚካሄድ አብራርተዋል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |