Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 06th
Home arrow Sections arrow የተሳሳተ ጸሎት
የተሳሳተ ጸሎት Print E-mail
Sunday, 11 May 2008
Imageአዲስ የፖለቲካ ባህል አዳብረን ካልተጓዝን በስተቀር አሁን የያዝነው አሉታዊ ፖለቲካ ለምንመኘው ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሐዊና ልማታዊ ሥርዓት በእጅጉ እንቅፋት ይሆንብናል፡፡ እየሆነብንም ነው፡፡
ራሳችንን አጠናክረንና በልጠን ተወዳዳሪያችን የምናሸንፍበት፣ እጅ ለእጅ ተያይዘን የምናድግበት ፀሎትና ምኞት ሳይሆን ተወዳዳሪዬንና ተፎካካሪዬን አድክምልኝ ብለን የምንፀልይና በዚያኛው ድክመት የበላይነት የምንይዝበት ፀሎት ላይ ነው ያለነው፡፡ እኔን አጠናክረኝ ሳይሆን እሱን አድክምልኝ ብለን የምንፀልይና እሱን ካደከምክልኝ “የወርቅ ጃንጥላ” እሰጥሃለሁ እያልን የምንሳል ሆነናል፡፡ ይህ በሽታ በመንግሥትና በተቃዋሚዎች ብቻ የሚታይ ሳይሆን በባለሃብቶችና በሲቪል ማኅበረሰቡም ዘንድ ያለ አደገኛና አሉታዊ “ፀሎት” ነው፡፡

የተቃዋሚዎች ፀሎት ምንድን ነው? ኢሕአዴግ ይጠናከር፣ እኛ ተቃዋሚዎችም እንጠንክር፣ ጠንካራ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ይኑሩ፣ የተሟሟቀ ፉክክር ውስጥ ገብተን በአሸናፊነት እንድንወጣ አድርገን የሚል “ፀሎት” ከአብዛኛው ተቃዋሚ ፓርቲ አይደመጥም፡፡

አገር ሲወረር፣ ድርቅ ሲመጣ፣ መብራት ይጠፋል ሲባል፣ እርዳታ አይሰጥም ሲባል፣ የአገርና የሕዝብ ወገን ሆኖ ተጨንቆና ተጠብቦ መፍትሔ ከማፈላለግ ይልቅ ይኼኔ ነው የስልጣን መገኛ እያሉ መፍለቅለቅ ይስተዋላል፡፡ የሚደመጠው “ፀሎት” በድርቁም፣ በኤርትራውም፣ በሶማሊያውም፣ በዋጋ ንረቱም፣ በፍንዳታውም አድርገህ ኢሕአዴግን አዳክምልኝ ነው፡፡ ይህን ካደረግክልኝ የሕዝቡ ችግሮች ተባብሰው በኢሕአዴግ ላይ አመፅ ካስነሳህልኝ “የወርቅ ጃንጥላ እሰጥሃለሁ” ብሎ ስለት የሚገባ ተቃዋሚ ነው ያለው፡፡

ኢሕአዴግ ራሱስ ምን ያህል ነው ተቃዋሚዎች እንዲጠናከሩ የሚፈልገው? በኢሕአዴግ በኩልም ተመሳሳይ ፀሎት አለ፡፡ ጠንካራ ተቃዋሚ ተፈጥሮ የተሟሟቀ ፉክክር ከማየት ይልቅ “ለቁልቢ የሚሰጠው የወርቅ ጃንጥላ ስለት” ተቃዋሚዎችን እርስ በእርሳቸው እንዲባሉና እንዲጣሉ አድርግልኝ፣ በእድሜም በበሽታም ጨርስልኝ፣ በስርቆት ተጣልተው መሳቂያ እንዲሆኑ አድርግልኝ፣ በታትንልኝ፣ አናክስልኝ፣ እንደወጡ አስቀርልኝ፣ የልማት መርሃ ግብሬ ላይ እንዳተኩር የተቃዋሚ አጀንዳ አጥፋልኝ፣ ዝጋልኝ የሚል ነው፡፡ እኔን ካጠናከርከኝ የወርቅ ጃንጥላ እሰጥሃለሁ ሳይሆን እነሱን ካዳከምክልኝና ከበታተንክልኝ የወርቅ ጃንጥላ እሰጥሃሁ የሚል ሆኗል፡፡

በቢዝነስ ዓለም ያለውን ፉክክር ስናይም የተሳሳተ ፀሎት ይፀለያል፡፡ የእሱም፣ የእሷም ሥራቸውና ኢንቨስትመንታቸው ሲሳካ የእኔም ይሳካል፤ ይጠናከራል ብሎ የሚፀልይና የሚያምን ከመሆን ይልቅ፣ የዚያኛው ቢዝነስ መክሰሩ፣ የባንክ ብድር መከልከሉን፣ በሙስና መታሰሩን አሳየኝ ብሎ “የሚፀልይና” ይህን ካሳየኸኝ “የወርቅ ጃንጥላ አስገባለሁ” ብሎ የሚሳል ነው፡፡ ክፋት፣ ምቀኝነትና አሉባልታ የበዛበት ፀሎት ነው፡፡

አዳዲስ ሃሳብና ራዕይ እንዲያመጣ የሚጠበቀው ፕሬስ ራሱ ፕሬስ የሚያድገው ሲደጋገፍና ሲተባበር ሁሉም ሲጠናከር መሆኑን አምኖ ለሁሉም ጥንካሬ ከመፀለይ ይልቅ ያኛውን ጋዜጣና መፅሄት፣ ያኛውን ኤፍ.ኤም፣ ያኛውን ፕሮግራም ካዳከምክልኝ “የወርቅ ጃንጥላ” ብሎ የተሳሳተ ፀሎት ሲያሰማ የሚውል ነው፡፡ አሉታዊ የሆነ  ፀሎት” ክፋት” ምቀኝነት”

በስፖርትም ሁሉም ቡድኖች ሲጠናከሩ እያንዳንዱ ቡድንና አገር ተጠቃሚ እንደሚሆን አምኖ አዎታዊ ፀሎት ከማስተጋባት ይልቅ ያኛውን ቡድን አዳክምልኝ አሰልጣኙን አጥፋልኝ፣ በታትንልኝ የሚል የተሳሳተ ፀሎት ሲያስተጋባ የሚውል ነው፡፡

አብዛኛው ፕሬስ፣ መንግሥት ጠንካራ ሆኖ፣ ተሻሽሎ፣ በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲታይ አይፈልግም፡፡ የታሰሩ ጋዜጠኞች ተፈቱ ሲባል ጎሽ ከማለት ይልቅና መንግሥት አዎንታዊ እርምጃና አዋጅ እንዲያወጣ ከመገፋፋት ይልቅ፣ መንግሥት የሚወገዝበት አጀንዳ ልናጣ ነው ብሎ ሲጨነቅና ሲጠበብ ይታያል፡፡ በአሜሪካ ተወገዘ፣ በአውሮፓ ተረገመ ሲባል እልል የሚል አለ፡፡ አምላኬ ሆይ መንግሥት ስህተቱንና ድክመቱን አንዳያርም አድርግልኝ እያለ የሚፀልይና ይህ ከተሳካ “የወርቅ ጃንጥላ” ለቁልቢ የሚሳል ነው፡፡

መንግሥትም፣ ፕሬስ ራሱ ድክመቱን ካረመ፣ ለማንነቱ ከቆመ፣ ከተደራጀ፣ አቅሙ በፋይናንስም በሙያም በስነ ምግባርም ካጠናከረ ለአገርም ለሕዝብም ይጠቅማል፤ እኔንም ያርመኛል ብሎ አይደሰትም፡፡

ሚዲያ ከተጠናከረ ጣጣ ሊመጣ ይችላል ብሎ በመስጋት፣ የፕሬስ ዘርፉ ለኢንቨስትመንት እንዳይጋብዝ፣ ፈቃድ ማግኘቱና መንቀሳቀሱ አዳጋችም ተስፋ አስቆራጭም እንዲሆን፣ መረጃ ማግኘት እልህ አስጨራሽ እንዲሆን፣ ቅጣቱም ከባድና አሳፋሪ ሆኖ እንዲፀድቅ፣ ጋዜጠኛው ራሱ ከመቀራረብ ይልቅ እንዲራራቅ ወዘተ. የሚመኝና “የሚፀልይ” ለዚህም ሰባት “የወርቅ ጃንጥላ” ለቁልቢ የሚሳል ነው፡፡

እየተሰማና እየተስተዋለ ያለው ፀሎት የአጠናክረኝ ፀሎት ሳይሆን የአዳክምልኝ ነው፡፡

ሁላችንም ከዚህ አሉታዊ የተዳከመ ምኞትና ፀሎት መራቅ አለብን፡፡ መለወጥ አለብን፣ መነሻችንም መድረሻችንም አካሄዳችንም የአገርንና የሕዝብን ጥቅምና ክብር ልማትና ብልፅግና ሰላምና መረጋጋት የሚያስቀድም ሊሆን ይገባል፡፡

ጠንካራ ገዢ ፓርቲ ካለ አገርና ሕዝብ ይጠቀማል፣ ጠንካራ ተቃዋሚ ፓርቲ ካለ አገርና ሕዝብ ይጠቀማል፡፡ ጠንካራ ፕሬስ በየቦታው ከተፈጠረ አገርና ሕዝብ ይጠቀማል፡፡ ጠንካራ ባለሀብትና ጠንካራ የቢዝነስ ሰው ካለ አገርና ሕዝብ ይጠቀማል፡፡

የትግላችን አቅጣጫ ራሳችንን ብቁና ጠንካራ አድርገን ለፉክክር የምናቀርብበት እንጂ ተፎካካሪ ባለመኖሩ ወይም በመዳከሙ ምክንያት የእሱ መቀነስ ለእኛ መጀመር ሆኖ በምናገኘው የበላይነት መሆን የለበትም፡፡

አስተሳሰባችን፣ ዓላማችን ሁሉም እንዲጠናከር መሆን አለበት፡፡ ፀሎታችን አዎንታ መሆን አለበት፡፡ የአዎንታና የመጠናከር፣ አገርን የማጠናከርና የመጥቀም ፀሎት ይሁን፡፡ ይህ ፀሎታችን ከተሳካ “የወርቅ ጃንጥላ”“
 
< Prev   Next >