| የምርት መጨመሩ ከፍላጎት ጋር... |
|
|
| Friday, 11 January 2008 | |
|
የምርት መጨመሩ ከፍላጎት ጋር ተመጣጣኝ ባለመሆኑ የዋጋ መቀነስ አልታየም አበራ ደሬሳ የአገሪቱ ጠቅላላ ምርት ቢጨምርም አምራች ያልሆነው ሕዝብ ቁጥር ማደግ፣ የፍላጐት መጨመርና የሕገ ወጥ ነጋዴዎች መበራከት ዋጋው እንዳይቀንስ እንቅፋት መሆኑ ተጠቆመ፡፡ የግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር አበራ ደሬሳ እንደተናገሩት፣ የግብርና ምርቶች መጨመር በተለይ በሰብል ወቅት ከፍተኛ የዋጋ መቀነስ ሊፈጥር ቢችልም የምርት መጨመሩ ከፍላጐት ጋር ተመጣጣኝ ባለመሆኑ የዋጋ መቀነስ አልታየም፡፡ የምርት መጨመር የገበሬውን ገቢ እንዲጨምር በማድረጉ ምርቱን መያዝ መጀመሩ፣ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ የሠራተኞች ፍላጐት እንዲያድግ ማድረጉ፣ የሕዝብ ቁጥሩ ከምርት እድገት ጋር አለመጣጣሙና የግብይት ሰንሰለቱ አለመጠናከሩ የዋጋ ለውጥ እንዳይኖር ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የምርት እድገቱን ከሕዝብ ቁጥር ጋር እንዲጣጣም ለማድረግ በሥነ ህዝብ ፖሊሲና ስትራቴጂ መደገፍ ምርትና ምርታማነትን መጨመር አስፈላጊ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ በምርት መሰብሰቢያ ወቅት የግብር፣ የማዳበሪያ፣ የምርጥ ዘር እዳ፣ የልጆች ትምህርት ቤት ለመክፈል ምርቱን ወደ ገበያ ስለሚያወጣ ዋጋ ይቀንስ እንደነበር ጠቅሰው የአርሶ አደሩ የገቢ ሁኔታ በገበያ እህሎች በመጠናከሩ በምርት ወቅት እንደነበረው የዋጋ መውረድ የሚጠበቀውን ያህል መሆን እንዳልቻለ ተናግረዋል፡፡ ሆኖም በአሁኑ የምርት ወቅት በከፍተኛ ደረጃ ምርት እንደሚጨምር የባለሙያዎች ግምት በመኖሩ ገበያው እንደሚረጋጋ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡ ምርታማነት ለመጨመር አዳዲስና ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂዎች መጠቀም የሥራ ባህልን ማሻሻል አስፈላጊ መሆኑን፣ በግብርና ምርምር የተደገፉ የልማት ሥራዎችን ለመተግበር ሰፊ ሥራ መሠራት እንዳለበት ዶ/ር አበራ አሳስበዋል፡፡ አሁን ወደ ሥራ እየገቡ ያሉት የግብርና ባለሙያዎች /ዲኤ/ ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ በምርታማነቱ ላይ ትልቅ ለውጥ ለመፍጠር እንደሚያስችልም አመልክተዋል፡፡ የምርምር፣ የሥርጭት፣ የገበሬና ሸማች /ተጠቃሚ/ ግንኙነትን በየደረጃው ማጠናከር የየዕለቱን የአየር ሁኔታ የመረጃ ልውውጥ ማሳደግ የአመጋገብ ባህልን መለወጥ አስፈላጊ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ ለገበያው አለመረጋጋት ያለአግባብ ምርት የሚያከማቹ ነጋዴዎች መኖር፣ የገበያ ሰብሎች ዋጋ መጨመር፣ የግንባታ ሥራዎች መስፋፋት፣ የአገልግሎት ዕቃዎች ዋጋ መጨመርን በምክንያትነት ጠቅሰዋል፡፡ በሕገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ የሚደረገው ቁጥጥር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለፁት ዶ/ር አበራ ወደ ውጭ እንዳይላኩ ጊዜያዊ እገዳ የተደረገባቸው የግብርና ምርቶች ዋጋ ለማረጋጋት በሚደረገው ጥረት እንደሚቀጥልም ተናግረዋል፡፡ አርሶ አደሩ በገበያ ምርት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሥራቱ የአርሶ አደሩን የገቢ አቅም የወጪ ንግድን ከማሳደግ አንፃር የሚኖረውን ሚና አብራርተው ..ገበያ ተኮር የሆኑ ምርቶችን ማምረት ለቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ለመሠረተ ግንባታ ትልቅ አስተዋፅኦ አለው፡፡ ለአገር ውስጥና የምግብ ሰብሎችን ብቻ ማምረት ለውጥ አያመጣም.. ብለዋል፡፡ የእንስሳት ምርት እንደ ሰብል ጥሩ ውጤት እንደሌለው፤ ያለውን ሰፊ ሀብት ለማልማት የተሰጠው ቦታ አናሳ መሆንና የእንስሳት በሽታ ማነቆ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ ለእንስሳት መኖና የገበያ ሥርዓት የተዘረጋ ባለመሆኑ ወደ ወጪ ለመላክ የገበያ ችግር መኖሩን፣ ይህም ችግር ለማስተካከል ኘሮጀክት ተቀርፆ እየተሠራበት መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ በአምራችና በሸማቹ መካከል ያሉ ነጋዴዎች ያለውን የመረጃ ችግር በመጠቀም ያለአግባብ ዋጋ የሚወስኑበት ሁኔታን ለመቀነስና የግብይት ሥርዓቱን ለማስተካከል የምርት ገበያ ድርጅት በባለሥልጣን ደረጃ መቋቋሙንና ከአምራቹ ጥራቱን የጠበቀ ምርት በሕጋዊ መልክ በመቀበል ለሸማቹ እንዲደርስ የማድረግ ኃላፊነት እንዳለበት ገልፀዋል፡፡ የመሬቱን ምርታማነት በመጨመር በኩል አገልግሎት ላይ ያልዋሉ መሬቶችን በመጠቀም በተለይ በኮትቻ አፈር ላይ ውኃን በማንጠፍጠፍ ምርትን እስከ ሦስት እጅ ማሳደግ እንደሚቻል፤ በኮምጣጤና አሲዳማ አፈር ሰብልን የማቃጠል ባህሪይን በመቀነስ በሁለት እጅ ምርትን ማሳደግ እንደሚቻልም አብራርተዋል፡፡ በግብርናው ዘርፍ የተሠማሩ የግል ባለሃብቶችን በማበረታታት ዙሪያ እየተሠራ መሆኑን፤ በግል ባለሃብቶች የተያዙ ኘሮጀክቶች በ2ዐዐ6 ከነበረበት 8ዐዐ ወደ 1..1ዐዐ፣ ቋሚ የሥራ እድል በመፍጠር ረገድ በ2ዐዐ5 ከነበረበት 60..000 ወደ 155 ሺህ ማደጉንም አስረድተዋል፡፡ በቤዛዊት ሥዩም |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |