| የነዳጅ ዋጋ በማሻቀብ ላይ ነው |
|
|
| Sunday, 11 May 2008 | |
|
በጋዜጣው ሪፖርተር
በናይጄሪያ ባለው አለመረጋጋትና ከዶላር ዋጋ መውደቅ ጋር ተያይዞ የነዳጅ ዋጋ በማሻቀብ ላይ ነው፡፡ ባለፈው ዓርብ የአንድ በርሜል ድፈድፍ ነዳጅ ዋጋ ጧት ላይ ከነበረው 125 ዶላር 125.98 ዶላር ደርሷል፡፡ የነዳጅ ዋጋ ባለፈው ሳምንት በየዕለቱ እየጨመረ የመጣ ሲሆን ጭማሪው በናይጄሪያ ያለው አለመረጋጋት በቀጣይ በሚኖረው አቅርቦት ላይ ለውጥ ይፈጥራል በሚል ስጋትና ከዶላር ዋጋ መውረድ ጋር ተያይዞ እንደሆነ ባለሙያዎች እየተናገሩ መሆኑን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡ እንደ ዘገባው የነዳጅ ዋጋ ከ2008 መጀመሪያ ጀምሮ የ25 በመቶ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከነበረው 62 ዶላር በእጥፍ ማደጉም ተመልክቷል፡፡ የቻይናና የሕንድ የነዳጅ ፍላጎት እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ ዋጋ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ መሆኑንም ዘገባዎች ያስረዳሉ፡፡ ባለፈው ሀሙስ የፔትሮሌየም ላኪ አገሮች (ኦፔክ) ባለው ፍላጎት መሠረት አቅርቦት በመጨመር ዋጋው እንደሚረጋጋ መግለጫ ቢሠጥም በመጨመር ላይ መሆኑ ተገል"ል፡፡ የኦፔክ ዋና ሴክሬታሪ አብደላ ሳለም ኤል በዲር ባለፈው ሀሙስ የድፍድፍ ነዳጅ እጥረት እንደሌለ የተናገሩ ሲሆን አሜሪካ እየጨመረ የመጣውን የነዳጅ ፍላጎት ለማሟላት ተጨማሪ ማምረት እንደምትችልና በነዳጅ ገበያ የአቅርቦት ችግር እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ 13ቱ የኦፔክ አባል አገራት 40 በመቶ የሚሆነውን የዓለማችንን ነዳጅ የሚያመርቱ ሲሆን አሁን ባለው አቅርቦት በቀን 32 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ለገበያ ያቀርባሉ፡፡ ዋና ሴክሬታሪው ኤል ባዲር እንደተናገሩት፣ የነዳጅ ገበያ በገንዘብ ገበያ ለውጦችና በቀጣይ በሚኖር ገንዘብ ጭማሪ ተለዋዋጭ ነው፡፡ የአሜሪካ ዶላር ዋጋ መቀነስ ባለሐብቶች ካላቸው የነዳጅ ምርት በተለይ ከድፍድፉ ነዳጅ ለወደፊት የተሻለ ገቢ እንዲያገኙ ስለሚረዳቸው የነዳጅ ዋጋ እንዲጨምር ምክንያት መሆኑንም የተናገሩ ሲሆን ሌሎች አምራች አገሮችም የነዳጅ ዋጋ በየጊዜው መጨመር በማሳየቱ አምራች አገሮች የበለጠ ተጠቃሚ ለመሆን ያላቸውን ነዳጅ በመያዛቸው የመጣ እንደሆነም ይገለፃል፡፡ በነዳጅ ላኪ አገራቱ ያለው የነዳጅ አቅርቦት ባለፉት ጊዜያት ከነበረው በአማካኝ በአምስት እጥፍ ያደገ ሲሆን በአሜሪካ በነዳጅ ማውጣት ሥራ ላይ የተሠማሩ ባለሐብቶች የነዳጅ አቅርቦትን ባለፈው ሳምንት በ6 እጥፍ ያሳደጉ ሲሆን አቅርቦቱ ካለው ፍላጎት አንፃር በቂ መሆኑንም ኦፔክ አስታውቋል፡፡ አንዳንድ ነጋዴዎች እንዳሉት የነዳጅ ዘይት አምራች ሃገራት ምርታቸውን ላለመጨመር መወሰንን የመሳሰሉ የጫናዎች መደራረብ ዋጋውን እንዲንር ተጨማሪ ምክንያት ነው፡፡ በናይጀሪያና የአፍሪካ ታላላቅ ድፍድፍ ነዳጅ አምራች ሃገራት እየተካሄደ ያለው አመፅ የነዳጅ ዋጋ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል፡፡ ተንታኞች እንደሚሉት "በናይጀሪያ አማፅያን የሃገሪቱን የነዳጅ ሃብት ድርሻ ይኑረን በሚል እያካሄዱት ያለው ጥቃት በሃገሪቱ የሚመረተው ነዳጅ መጠን እንዳይጨምር ምክንያት ሆኗል፡፡ በተጨማሪም በኢራቅ ያለው የሰላም እጦትም ለዋጋ መዋዠቁ ምክንያት ነው" |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |