Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 20th
Home arrow Sections arrow የተባበሩት መንግሥታት ለበርማ እርዳታ ሰጠ
የተባበሩት መንግሥታት ለበርማ እርዳታ ሰጠ Print E-mail
Sunday, 11 May 2008
በኒክሎን ናርጂስ አውሎ ነፋስ ቤት አልባ ለሆኑ የበርማ ነዋሪዎች የተባበሩት መንግሥታት ዕርዳታ ሰጠ ሲል ቢቢሲ ዘገበ፡፡

 

የተባበሩት መንግሥታት በረራ በመከልከሉ እርዳታው ዘግይቷል፡፡ እስካሁን በአደጋው 22"980 ሰዎች ሲሞቱ ቁጥራቸው ወደ 100"000 ያሻቅባል ተብሎ ይገመታል፡፡

ተፈናቃዮች የመጠለያ ችግር ገጥሟቸዋል፡፡ አካባቢው በበርካታ አስከሬኖች በመሸፈኑ ምክንያት በተፈጠረው ብክለት አስከፊ የጤና ችግር እያደረሰ ነው፡፡ ሲል የቢቢሲው ዘጋቢ ፖል ዳናር ከደቡብ በርማ ዘግቧል፡፡

የተፈጥሮ አደጋ ከደረሰ በኋላ መንገዶች በእርዳታ ሰጪ ሀይሎች ሲሞላ ማየት የተለመደ ቢሆንም እዚህ ይህ አይታይም፡፡ በዋና ከተማዋ ራንጉል አልፎ አልፎ እርዳታ ሲሰጥ የሚታይ ቢሆንም በቂ አይደለም፡፡ በቂ የነዳጅ ክምችት የለም ብሏል ዘጋቢው፡፡

ሐሙስ የመጀመሪያዋ ከጣሊያን የመጣቸው የእርዳታ አውሮፕላን ሃይል ሰጪ ብስኩትና መድሀኒት ይዛ ራንጉግ ያረፈች ሲሆን በተመሣሣይ እርዳታ የሚያደርሱ ሦስት በረራዎች ከተባበሩት መንግሥታት ይጠበቃሉ፡፡ እርዳታው ለተጎጂው ሕዝብ በአግባቡ መድረስ ይኖርበታል ሲሉ የአለም አቀፉ ምግብ ፕሮግራም ድርጅት የወረዳው ዳይሬክተር አንቶኒ ባንቡኒ ተናግረዋል፡፡

""""""///"""""


ቡሩንዲ በተከፈተው ተኩስ ሃምሣ ሰዎች ተገደሉ

በዋና ከተማዋ ቡጁምብራ 50 አማጽያን መገደላቸውን የቡሩንዲ ሰራዊት ሲገልፅ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ቤታቸውን ጥለው መሰደዳቸውን የቢቢሲ ዘገባ አስታወቀ፡፡
 
የመንግሥት ወታደሮች ባደረጉት አፀፌታዊ ተኩስ ሁለት ወታደሮች መሞታቸውን ቃል አቀባዩ ኮሌኔል አዶልፍ ማኒራኪዛ አስታውቀዋል፡፡ ባለፈው ወር ከተከሰተው ጦርነት ቀጥሎ ይህ ከባዱ እንደሆነ ዘገባው ያመለክታል፡፡

የአማጽያኑ ቃል አቀባይ እንደተናገረው ተከታታይ ስምምነቶችን ለመፈራረም በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ቡጁምብራ ይሄዳሉ አያይዘውም የወታደሮቻቸውን ቁጥር እንደማይገለፁና የሞቱትና የተያዙት ወታደሮች ብሩንዲያውያን መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ካለው ኤፍ.ኤን.ኤል አማጺ ቡድን በስተቀር ሁሉም የሰላም ስምምነት ፈርመዋል፡፡ ቡድኑ በ2006 የሰላም ስምምነት ቢያደርግም በተግባር ግን አልታየም ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ታንዛኒያ የሚገኘው የቡድኑ መሪ እንደተናገረው የአማፂው ቡድን ህጋዊ አካል ሆኖ ሥልጣን መጋራት ይፈልጋል፡፡ ነገር ግን ይህ ሕገ መንግሥታዊ ለውጥ እንደሚያስከትልና ለምክር ቤቱም አስቸጋሪ እንደሆነ ዘገባው ያመለክታል፡፡

ታንዛኒያ ከሁለት ሳምንታት በፊት አማፅያኑ መሪ ቡሩንዲ በመሄድ ስምምነቱን እንዲፈርም የ10 ቀን ገደብ መስጠቷ የሚታወስ ነው፡፡

"""""""///""""""


የሊባኖስ ታጣቂዎች የሰላም ጥሪ አቀረቡ

በቤሩት አማፅያንና ተቃዋሚዎች ከፈጠሩት ሁከት ጋር በተያያዘ ፖለቲካዊ ቀውሱ የሚቀጥል ከሆነ እርምጃ እንደሚወስዱ የሊባኖስ ወታደሮች ማስጠንቀቃቸውን ቢቢሲ ዘገበ፡፡

ተቃውሞው ከተደረገበት ሁለተኛ ቀን ጀምሮ መንገዶች በተቃዋሚ ደጋፊዎች የተዘጋ ሲሆን በዋና ከተማዋ እንቅስቃሴ ቆሟል፤ አለም አቀፍ የአየር መንገዱን ጨምሮ ሱቆች፣ ትምህርት ቤቶችና ቢሮዎች ተዘግተዋል፡፡

ከወታደሮቹ ቁጥጥር በላይ በሱኒና ሺኣ መካከል ረቡዕ ከተከፈተው ተኩስ በኋላ ውጥረቱ ተባብሷል፡፡ በሂዝቦላ እና በሌሎች ደጋፊዎች የሚመራው ሺኣ የምዕራቡን መንግሥታት የሚቃወም ሲሆን የሱኒና ዱሩዝ አንጃ ግን በተቃራኒው ይደግፋል፡፡

በቀጣይ ቀናቶች የቤይሩት ሕዝብ በተቃጠሉ ጎማዎችና በፍርስራሽ የተዘጉ መንገዶችን ሲያስተካክሉ ታይቷል፡፡ ወታደሮችም በከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች በተለይም ቤይሩትን በሚያቋርጡ ሰሜናዊ የሺኣ ክልሎች በብዛት ተስተውለዋል፡፡

"በሊባኖስ የተፈጠረው ሁኔታ በቀጣይም በዚች ከተማ የሚሆነውን የሚያሳይ ነው፡፡ ይህም የአረቡ አለምና የመካከለኛው ምሥራቅ መከፋፈል ውጤት ነው" ሲል የዮርዳኖሱ አል-ዳክተር ጋዜጣ አስፍሯል፡፡

""""///""""

 
< Prev   Next >