Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 06th
Home arrow Sections arrow ኢትዮጵያ ከሁለት ቢሊዮን...
ኢትዮጵያ ከሁለት ቢሊዮን... Print E-mail
Sunday, 11 May 2008
ኢትዮጵያ ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ የልማት ድጋፍ ልታገኝ ነው

የእንግሊዝ የልማት መምሪያ ኢትዮጵያ ለምታካሂደው የድህነት ቅነሳ ኘሮግራም የሚውል የሁለት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር የልማት ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡

 

የእንግሊዝ አምባሳደር በኢትዮጵያ ሚስተር ኖርማን ሊንግ እንዳስታወቁት፣ እንግሊዝ ለኢትዮጵያ የምታደርገው ድጋፍ በአፍሪካ ከምታደርገው የልማት ድጋፍ ከፍተኛው መሆኑንና እስካሁን ሲደረግ ከነበረው የ180 ሚሊዮን ብር ብልጫ እንዳለው ገልፀዋል፡፡

(ኢዜአ)

*                               *                             *

አዲስ የቡና የንግድ መለያ ምልክት ይፋ ሆነ


ኢትዮጵያ በጣዕምና መዓዛቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ ዝነኛ ላደረጓት የቡና ምርቶቿ "ኢትዮጵያን ፋይን ኮፊ" የሚል ስያሜ የተሰጠው አዲስ የንግድ መለያ ምልክት (ብራንድ) አሜሪካ ውስጥ ይፋ ማድረጓን የአእምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

አዲሱ አርማ ይፋ የተደረገው በሚኒኦፖሊስ እየተካሄደ ባለው 2ዐኛው የአሜሪካ ልዩ ቡና ማህበር ጉባዔ ላይ ሲሆን፣ ከቡና ፍሬ ጋር ተመሳሳይነት ባለውና በእንግሊዝኛ ቋንቋ "ኢ" የፊደል ቅርፅና በዙሪያው የብርሃን ጮራ የሚመስሉ የመስመር ጨረሮች የተፈነጣጠቁበት፣ የኢትዮጵያ ምርጥ ቡና መለያ ምርቶች ምልክት (አርማ) "ኢትዮጵያን ፋይን ኮፊ" የሚል ፅሁፍ ያካተተ መሆኑን ጽሕፈት ቤቱ ጠቁሟል፡፡

(ዋኢማ)

*                               *                             *

የቆዳና ሌጦ ማምረቻ ፋብሪካ በ100 ሚሊዮን ብር ሊገነባ ነው


ኢትዮጵያ ለውጭ ገበያ የጠናቀቀ የቆዳና ሌጦ ምርት የምታቀርብበት ፋብሪካ በ100 ሚሊዮን ብር ለመገንባት ዝግጅት በመደረግ ላይ መሆኑን ክሪስታል የቆዳ ፋብሪካ አስታወቀ፡፡

አገሪቱ በውጭ ምንዛሪ የምታገኘውን ገቢ ለማሳደግ የሚያስችለውን ፋብሪካ ለመገንባት በኢጣሊያና በኢትዮጵያ ባለሀብቶች ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን፣ ወደ ውጪ የሚላከውን በከፊል የለፋ የቆዳና ሌጣ የሚያስገኘውን ጥቅም ከፍ ለማድረግ እንደሚያስችልና ወደ አውሮፓ ገበያ ለማስገባት እንደሚረዳ፣ ሙሉ በሙሉ ሥራ ሲጀምር 470 ሠራተኞች የሚኖሩት አዲሱ ፋብሪካ ግንባታው ከሁለት ወር በኋላ ይጀመራል፡፡

    (አዲስ ዘመን ሚያዚያ 29 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም".

*                               *                             *

የቡና ማበጠሪያ ማሽኖቹ ለብልሽት እየተዳረጉ ነው

በምዕራብ ወለጋ ዞን የመንግሥት ንብረት የሆኑ 16 የደረቅ ቡና ማበጠሪያ ማሽኖች ያለ ሥራ በመቆማቸው ለብልሽት እየተዳረጉ መሆኑን ነዋሪዎች ገለፁ፡፡

ማሽኖቹ ያሉ አገልግሎት በመቆማቸውና አስፈላጊው ጥበቃ ስለማይደረግላቸው እየወላለቁ መሆኑን፣ ከፍተኛ የቡና ምርት ባለበት ወቅት የማሽኖቹ ያለ ሥራ መቆም በቀን እስከ 15ዐ ኩንታል ደረቅ ቡና የማበጠር አቅም ቢኖራቸውም ተግባራዊ ማድረግ አልተቻለም በማለት የሚመለከተው አካል ትኩረት እንዲሰጣቸው ነዋሪዎቹ አመልክተዋል፡፡

(ኢዜአ"

*                               *                             *

ሀገር አቀፍ ፈተናዎች ከግንቦት 26 እስከ ሰኔ 4 ይሰጣሉ


የ2ዐዐዐ ዓ.ም. የትምህርት ዘመን ሀገር አቀፍ ፈተናዎች ከግንቦት 26 እስከ ሰኔ 4 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. እንደሚሰጡ አጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማረጋገጫና የፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

ፈተናዎቹ በ768 ጣቢያዎች፣ በአንድ ሺ 236 አስፈታኝ ት/ቤቶች፣ 961 ሺ 641 የአስረኛ፣ 91 ሺ 660 የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እንደሚወሰዱ ገልጿል፡፡

(አዲስ ዘመን ግንቦት 1 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም".

 
< Prev   Next >