Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 06th
Home arrow Sections arrow ድላችን
ድላችን Print E-mail
Sunday, 11 May 2008
Imageበሔኖክ ያሬድ

ኢትዮጵያ ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘይጥዕም እመዓር
"ኢትዮጵያ ከማር ለሚጣፍጥ ለስምሽ አጠራር ሰላምታ ይገባል፡፡
ባምላክ እጅ ለተሠራ ለራስ ጸጉርሽም ሰላምታ ይገባል፡፡
ምሳሌ የሌለሽ መቅደስ ኢትዮጵያ ጠላት ኢጣሊያ ስላረከሰሽና መሠዊያሽን ስላጠፋ ፈንታ ከእንግዲህ ወዲህ ተቀ    ደሽ ኃይልንም ገንዘብ አድርጊ፡፡"
 
ሚያዚያ 27 ቀን 1933 ዓ.ም ኢትዮጵያ የተቀዳጀችውን ድል ምክንያት በማድረግ በዚያን ወቅት ብርሃኑ ድንቄ ዘእንጦጦ ራጉኤል፣ በመልክእ አደራረስ ስልት ለኢትዮጵያ የተቀኙላት ነው፡፡ ዘንድሮ አዲስ አበባ በዓሉን ከሺሕ ዓመቱ ጋር አስተባብራ በታላቅ ሰልፍና አጀብ በሚያዚያ 27 አደባባይ ርእሰ ብሔር ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ በተገኙበት አክብራለች፡፡

የአምስቱን ዘመን የፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ ለመቀልበስና ነፃነትን ለማረጋገጥ ከጦራዊ ተጋድሎ በተጓዳኝ ዲፕሎማሲያዊ ትግሉ እልህ አስጨራሽ ነበር፡፡ በጄኔቭ የዓለም መንግሥታት ማኅበር (ሊግ ኦፍ ኔሽንስ) ብዙ ምልልስ ነበር፡፡

ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ በ1931 ዓ.ም በካርቱም ሳሉ "የኢትዮጵያ ጉዳይ በጄኔቭ ላይ ቀርቦ ነገ ተነገ ወዲያ እየተባለ በመዘግየቱ" እያዘኑ የዘረፉት መወድስ በ፣አማርኛ ሰዋሰው፣ መጽሐፍ የተጻፈው ቀጥሎ የተመለከተው ነው፡፡ ምሥጢሩ እሺ ነገ ወደ ጄኔቭ ሄዳ ኦራይትንና ቱሞሮን፣ አፍተር ቱሞሮን ወለደች ማለት ነው፡፡ (ኦራይ" እሺ፣ ቱሞ" ነገ፣ አፍተር ቱሞ" ተነገ ወዲያ፡፡)

ምንተ ንግበር የዐመፅ ልጆች
ለእመ ዐረፍት ይእቲ፣ ቃለ አፉነ ወስላታ
ወተድባበ ብሩር ልብነ ስታጫውተን ጨዋታ
ንግበር ማዕፆሃ ቃለ ጽድቅ ወቃለ ሐሰት ወአኮ ባሕቲታ
ወዲያና ወዲህም ሳትንገላታ
በየበራችን ለትቁም የዝግባ ሣንቃ ይሉንታ
በጄኔቭሂ አመ ተፀንሰ ዘኢትዮጵያ አለኝታ
የቱሞሮ እናት እሺ ነገ ለብሂለ ኦራይት ወለደታ
ወእሺ ነገ እኅትነ እምድኅረ ወለደት መንታ
ሕማማ ኢትዜከር ወአፍተር ቱሞሮ ተቀበለታ፡፡

ፋሺሽት ኢጣሊያ አዲስ አበባን በያዘበት ሚያዝያ 27 ቀን (1928ዓ.ም) በሕዝቡና በአርበኞች ተጋድሎ የድሉን ቀን ሚያዝያ 27 ቀን (1933 ዓ.ም) አበሰረ፡፡ 67ኛ ዓመቱንም ባለፈው ሰኞ ዘከረ፡፡

በሺሕ ዓመቱ ምልዐትና፣ በሦስተኛው ሺሕ ዋዜማ በመላ ኢትዮጵያ በተለይም በአዲስ አበባ "ሚያዝያ 27 አደባባይ" የተደረገው አከባበር የአርበኞች የሰልፍ ትርዒት፣ የስካውት ሰልፍና የአርበኞች ት/ቤት ተማሪዎች ትርዒት፣ ከዳር አዲስ አበባ የመጡ የፈረሰኛ ሰልፈኛን ያካተተ ነበር፡፡

የአገሪቱ ርእሰ ብሔር ከመገኘታቸው ሌላ የኮር ዲፕሎማቶች፣ ወታደራዊ አታሼዎች ከነሙሉ ማዕርጋቸውና ወታደራዊ ልብሳቸውን አድርገው ተገኝተዋል፡፡ የአገሪቱ የጦር አዛዦች ከማዕርጋቸውና ክብራቸው ጋር ተገኝተው ቢሆን ኖሮ ምንኛ ባደመቁት ነበር፡፡ የአገሪቱ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ የበዓሉ ማሳያ የሆኑትን ሽለላ፣ ቀረርቶ፣ ፉከራ ቢያቀርቡ ኖሮ ምንኛ ባገነኑት ነበር፡፡
 
የድል ቀን በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን (1923-1967) በያመቱ ሲከበር በተለያየ ስያሜ፣ "የነፃነት በዓል"፣ "ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በድል አድራጊነት አዲስ አበባ የገቡበት ቀን" እየተባለ ሲከበር ኖሯል፡፡

ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ ሥልጣኑን ሲጨብጥ በዓሉን ወደ መጋቢት 28 ቀን ለውጦ እስከ 1987 ዓ.ም እየተከበረ ቆይቷል፡፡ ከኅብረተሰቡና ከአርበኞች በቀረበው ጥያቄና የታሪክ ምሁራን በሰጡት ሙያዊ አስተያየት መሠረት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ በ1988 ዓ.ም በዓሉ እንደቀድሞው ወደ ሚያዚያ 27 እንዲመለስ መወሰኑ ይታወቃል፡፡

በአጀንዳዎች፣ በቀን መቁጠሪያዎችና በመገናኛ ብዙኀን ሚያዚያ 27ን የአርበኞች መታሰቢያ፣ የነፃነት በዓል፣ የድል ቀን እየተባለ በተለያዩ መጠርያዎች ሲስተናገድ ይታያል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ፣የሕዝብ በዓላትንና የእረፍት ቀንን ለመወሰን ' በወጣው አዋጅ መሰረት የበዓሉ መጠርያ "የድል ቀን" ነው፡፡

ኢትዮጵያ እምነ እስመ ለዕሩቃን ክዳን
እናታችን ኢትዮጵያ ሆይ ለታረዙ ልብስ ነሽና
በባንዲራሽ ጥላ ሰብስቢ ልጆችሽን
በክንፎቹዋ እንድታቅፍ ዶሮ ጫጩቶቹዋን፡፡
   ኢትዮጵያ ጀግኖችሽ በሞት ቢቀነሱ
   ከጠላት ሲዋጉ ክብርን ሊመልሱ
   ሴቶችም ታጠቁ መለዮ ለበሱ
   ለነፃነትሽ ደማቸውን ሊያፈሱ
    እንዝርትንም ጥለው ጋሻ ጦር አነሱ፡፡
 
< Prev   Next >