Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Monday
Oct 13th
Home arrow Sections arrow ብሔራዊ ባንክ በአምስት የአዋሽ ባንክ...
ብሔራዊ ባንክ በአምስት የአዋሽ ባንክ... E-mail
Friday, 11 January 2008

ብሔራዊ ባንክ በአምስት የአዋሽ ባንክ ዳይሬክተሮች ላይ ማጣራት ሊያደርግ ነው

ለሠባቱ ዳይሬክተሮች እውቅና ሠጠ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ጠቅላላ ጉባዔ ከተመረጡት 12 የቦርድ አባላት ውስጥ የሠባቱን በማፅደቅ ሥራ እንዲጀምሩ አስታወቃቸው የቦርድ አባላት ላይ ማጣራት ሊያደርግ መሆኑ ተገለፀ፡፡

ከባንኩ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ከሁለት ሣምንት በፊት በተደረገው አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ ምርጫ የተመረጡትን 12 የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ብሔራዊ ባንክ እንዲያፀድቅ በተጠየቀው መሠረት በአዲሱ ምርጫ ከተካተቱትና የቀድሞ ቦርድ አባላት የነበሩትን አምስት ሠዎች ጉዳይ እንዲጣራ በማመልከት ቀሪዎቹ ሠባት ተመራጭ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ግን በአስቸኳይ ሥራ እንዲጀምሩ ባለፈው ትእዛዝ ሠጥቷል፡፡

በብሔራዊ ባንክ ማጣራት እስኪደረግባቸው የቦርድ አባልነታቸው ያልፀደቀላቸው የቀድሞዎቹ የቦርድ አባላትና በአዲሱ ምርጫ ተካተው የበሩት አቶ ሃምቢሣ ወቅወያ፣ አቶ ከበደ ቦረና፣ አቶ ሃምሣሉ ብዙነህ አቶ እምሩ አመንቴ ናቸው፡፡ አቶ ወንድሙ ዓመቴ የተባሉት ተመራጭ ደግሞ ከቀድሞ ቦርድ ጋር በተያያዘ ሣይሆን በሌላ ምክንያት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነታቸው እንዳይፀድቅ መደረጉን ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡

ከብሔራዊ ባንክ የተላለፈውን አስቸኳይ ደብዳቤ ተከትሎም ብሔራዊ ባንክ የቦርድ ተመራጭነታቸውን ያፀደቀላቸው ሠባት ተመራጮችም የቦርድ ሠብሣቢያቸውንና ምክትል ሠብሳበያቸውን ለመምረጥ እንደሚችሉ በማሳወቅ ባደረጉት ሥብሠባ አቶ በቀለ ነዲን ሠብሳቢ አድርጐ በመምረጥ ቦርዱ ሥራ መጀመሩን አስታውቋል፡፡

አቶ በቀለ ነዲ በአቶ ሃምቢሣ ወቅወያ ይመራ በነበረው ቦርድ ውስጥ ምክትል ሠብሳቢ ሆነው ሲያገለግሉ የነበረ ሲሆን ባፈለው ዓመት ተደርጐ በነበረ ምርጫ ሰበብ ምርጫው ተጭበርብሯል ብለው ባለአክስዮኖች ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት የባንኩ ኦዲተር የጠቅላላ ጉባዔ ሲጠራ እነ አቶ ሃምቢሣ ኦዲተሩን በፍርድ ቤት ሲከሱ አቶ በቀለ በዚህ ውሳኔ ውስጥ ሣይገቡ መቅረታቸው ይታወሳል፡፡ በወቅቱ ለሪፖርተር ጋዜጣ በላኩት መልዕክት ኦዲተሩን በፍርድ ቤት ለመክሰስ ተደርገው ስብሰባ ላይ አለመኖራቸውንና ጉዳዩንም እንደማይወቁ መግለፃቸው ይታወሳል፡፡

ከሁለት ሣምንት በፊት በተደረገው አዲስ ምርጫ ተመርጠው አሁን ጉዳያቸው እስኪጣራ እንዲቆዩ የተደረጉት አምስቱ የቦርድ አባላት ጉዳይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ውሣኔ እስኪሰጥበት ድረስ ሰባቱ የቦርድ አባላት ሥራቸውን እንደሚሠሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ብሔራዊ ባንክ ጉዳያቸወ እስኪጣራ በሚል በቦርድ ውስጥ እንዳይካተቱ ስላደረጋቸው ግለሰቦች ምን ምን ለማጣራት እንዳቀዱ ባይገለፅም ማጣራቱን ካደረገ በኋላ በቦርድ አባልነታቸው እንዲቀጥሉ ሊያደርግ የሚችል ወይም በቦርድ ውስጥ እንዳይካተቱ የሚያደርግ ውሳኔ እንደሚያስተላልፍ ይጠበቃል፡፡

ብሔራዊ ባንክ ማጣራት ሒደት እነአቶ ሃምቢሣ በቦርዱ ውስጥ እንዳይካተቱ የሚያደርግ ውሣኔ ካልወሰነ በቅርቡ በተደረገው ምርጫ በተጠባባቂነት የተያዙት ተመራጮች ቦርድ ውስጥ እንዲገቡ የሚደረግ መሆኑም ታውቋል፡፡

ብሔራዊ ባንክ ሥራቸውን ባስቸኳይ እንዲጀምሩ ማረጋገጫ የሰጣቸው ሰባቱ የቦርድ አባላት አቶ ለይኩን ብርሃኑ፣ አቶ በቀለ ነዲ፣ አቶ ነጋሳ ቱምሣ፣ አቶ ወሌ ጉርሙ፣ አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ፣ አቶ ተረፈ መንገሻና አቶ ምትኩ አሹ መሆናቸውንም ለማወቅ ተችሏል፡፡

የአገሪቱ ባንኮችን በበላይነት የማቆጣጠረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሲሆን ባንኮቹ በህገ ደንባቸው መሠረት በባለአክሲዮኖች የዳይሬክተሮች ቦርድ አባሎቻቸውን በመምረጥ የተመሠረጡትን ለብሔራዊ ባንክ በማቅረብ ማፅደቅ የሚኖርባቸው ሲሆን ይህንን ካላደረጉ በህግ የሚጠየቁ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ባለፈው ዓመት በተደረገውና አወዛጋቢ በነበረው ምርጫደ ተመርጠው የነበሩት የእነ አቶ ሃምቢሣ ቦርድ ብሔራዊ ባንክ እውቅና ሳይሰጥ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡

በዳዊት ታዬ

 
< Prev   Next >