| "የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ዳይሬክተሮች... |
|
|
| Sunday, 13 January 2008 | |
|
"የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ዳይሬክተሮች ከሃላፊነታቸው የተነሱት ባቀረቡት መልቀቂያ መሰረት ነው" የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ዳይሬክተሮች ከሀላፊነታቸው የተነሱት ራሳቸው ባቀረቡት መልቀቂያ መሰረት መሆኑን የባንኩ ፕሬዚዳንት ዋና አማካሪና የቦርዱ ዋና ጸሀፊ አቶ አፈወርቅ ገ/ፃዲቅ ለሪፖርተር ጋዜጣ ገለጹ፡፡ ረቡዕ ጥር 1 ቀን 2000 ዓ.ም በወጣው ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ..የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ሶስት ዳይሬክተሮች ከስራ ታገዱ.. በሚል ርዕስ የወጣው ዜናም እንዲስተካከል ሀላፊው ጠይቀዋል፡፡ አቶ አፈወርቅ እንደገለጹት የዶመስቲክ ባንኪንግ ዲፓርትመንት ዳይሬክተር አቶ ከፍያለው ዘገየ፣ የፋይናንስ ዳይሬክተሩ አቶ ገብረ ሚካኤል ታምራት እና የሰው ሀይልና የማዕከላዊ ሰርቪስ ዳይሬክተር አቶ ገብረ እግዚአብሄር ወልዱ ከሀላፊነታቸው የተነሱት ታህሳስ 25 ቀን 2000 ዓ.ም ባቀረቡት መልቀቂያ መሰረት ነው፡፡ ቦርዱም በሀላፊዎቹ ላይ የእገዳ እርምጃ አለመውሰዱን አቶ አፈወርቅ አረጋግጠዋል፡፡ በሌላ በኩል ትናንት በወጣው የእንግሊዝኛው ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ሶስት የአንበሳ ኢንተርናሽናል የቦርድ ዳይሬክተሮች ባቀረቡት መልቀቂያ መሰረት ከሀላፊነታቸው እንደተነሱ ተደርጎ የተዘገበው ስህተት በመሆኑ ..ሶስት የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ዳይሬክተሮች.. ተብሎ እንዲስተካከል ከይቅርታ ጋር እንጠይቃለን፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |