| እገዛና ድጋፍ ያስፈልጋል |
|
|
| Thursday, 15 May 2008 | |
|
ዲያስፖራውን በአገር የልማት እንቅስቃሴ ላይ ለማሳተፍ መንግሥት ሁሉን አቀፍ ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ በአገሪቱ የሚካሄዱትን ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ እንቅስቃሴዎች የደረሱበት ደረጃና ያጋጠማቸውን ችግር የሚያንፀባርቁ መረጃዎችን ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡
ለዚህም በተለያዩ አገሮች የሚገኙ ኤምባሲዎችን (አምባሳደሮቻችን) ከፍተኛ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል፡፡ ዲያስፖራውን በሀገሩ ጉዳይ የሚመክርበት የውይይትና የመቀራረቢያ መድረኮችን ማዘጋጀት፣ የሚፈልጋቸውን መረጃዎች ወዲያውኑ የሚያገኝበትን መንገድ ማመቻቸት፣ ጉዳዩ ቶሎ እልባት እንዲያገኝ መንቀሳቀስ ወዘተ ይኖርባቸዋል፡፡ ግንቦት 3 ቀን 2000 በወጣው ሪፖርተር ጋዜጣ ..ዲያስፖራው ባለፉት ዘጠኝ ወራት.. በሚል ርዕስ የቀረበው ጽሑፍ ይህንኑ ጉዳይ በመጠኑ ዳስሷል፡፡ ከጽሁፉ ለመረዳት እንደተቻለው ..በዘጠኝ ወራት 34 ውይይቶች በተለያዩ አገሮች ተካሂደዋል.. ይህ አበረታች ቢሆንም አሁንም ገና ብዙ መሥራት ይጠበቃል፡፡ የዲያስፖራውን የልማት አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችል የዲያስፖራ ፖሊሲ ለማዘጋጀት የተጀመረው ጥናት ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል፡፡ ጥናቱም ትኩረት ማድረግ ያለበት በዲያስፖራው ዘርፍ ከፍተኛ ልምድና ተሞክሮ ባላቸው አገሮች ላይ ቢሆን መልካም ነው፡፡ በርካታ ሀገሮች ከዲያስፖራው በሚያገኙት ጥቅም ደህና የገቢ ምንጭ መፍጠራቸው ይታወቃል፡፡ በዚህ ዘርፍ ተጠቃሚ ከሆኑት አገሮች መካከል ሕንድን በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ ከጥናቱ ጐን ለጐን ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት እገዛና ድጋፍ ይጠበቃል፡፡ (በቀለ ገላው፣ ከቂርቆስ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |