Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Aug 08th
Home arrow Sections arrow የያሁና ጉግል ሽርክና እስካሁን አልተረጋገጠም
የያሁና ጉግል ሽርክና እስካሁን አልተረጋገጠም Print E-mail
Thursday, 15 May 2008
በቅርቡ ያሁና ጉግል ኢንተርኔት ላይ የሚወጡ ማስታወቂያዎችን ለመጋራት ተስማምተናል የሚል መረጃ ለቀው እንደነበር ይታወሳል፡፡

 

ከ16 የአሜሪካ የሲቪል ራይትና ገጠር ተኮር የቅሰቀሳ ተቋማት የተውጣጡ በአሜሪካ የሚገኙ ተቆጣጣሪዎች ጉግልና ያሁ ለሽርክና የተዋዋሉት ነገር መኖሩን ምርመራ በማድረግ አስካሁን ድረስ የተፈረመ ስምምነት እንደሌለ አረጋግጠዋል፡፡

በሁለቱ ተቋማት መካከል በግልፅ ስምምነት ባይፈረምም ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት፣ ለወደፊቱ በማስታወቂያና ሰርች አግሪመንት ላይ የሚኖራቸውን ብቃት ተገማግመዋል፡፡ ለወደፊት ሁለቱም ፍትሃዊ ባልሆነ መልኩ የንግድ ውድድር እንደማይፈፅሙ በመተማመን በሽርክና ለመስራት አቅደዋል፡፡

ባለፈው ሐሙስ የጉግል ባለአክሲዮኖች ባካሄዱት ስብሰባ ላይ የተቋሙ ሊቀመንበር ኤሪክ ከኬሚ፣ “ከያሁ ጋር ስምምነት ብናደርግ ስምምነቱን የምንቀርፀው ሰፊ ውይይት በሚፈልገው ፍትሃዊ ያልሆነ የንግድ ውድድርን ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ ይሆናል” ብለዋል፡፡

በአሜሪካ 16 የሲቪል ራይትና ገጠር ተኮር የቅስቀሳ ተቋማት ተውጣጥተው የተመሰረተው መርማሪዎች፣ የፍትህ ክፍል ስምምነቱ ጉግልን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ይከራከራል፡፡ ይኸው ቡድን እንደሚለው በታቀደው መልኩ ከተፈፀመ ጉግል 90 በመቶ በሚሆነው የኦንላይን ማስታወቂያ ገበያ ተጠቃሚ እንዲሆንና መረጃዎችን ፍለጋ በኢንተርኔት በሚጠቀሙት ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖዎች ከፍ እንዲያደርግ ይረዳዋል፡፡

የምግብ መመረዝን የሚያረክስ መድሃኒት

በአለም ላይ በጣም የሚፈራውን የምግብ ብክለት ለመከላከል ውጤታማ የሆነ ማርከሻ መድሃኒት ለመፍጠር እየተቃረቡ መሆኑን ሳይንቲስቶች አስታወቁ፡፡ ሳይንቲስቶቹ እንደሚሉት አንድ ግራም የተመረዘ የተበከለን ምግብ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሊገድል ይችላል፡፡

በየዓመቱ በርካታ ሰዎች በተመረዘ ምግቦች ምክንያት ለህመም ይጋለጣሉ፡፡ በጣም አደገኛ ደረጃ የደረሰን፣ በምግብ ብክለት ምክንያት የሚከሰትንና ለሞት የሚዳርግን ህመም ለማክሸፍ የሚረዳ አዲስ መድሃኒት ለመስራትም የአሜሪካ ሳይንቲስቶች ቡድን ጥረቱን ቀጥሏል፡፡

ክለዝትሪድየም በቱሊናም ባክቴሪየም በተሰኘው ባክቴሪያ የሚከሰተው የምግብ መመረዝ በሰው ልጅ ነርቭ ሴል በሚገኝ ፕሮቲን ላይ በመጣበቅ ነርቭ ሴሎች እርስ በርስና ከጡንቻዎች ጋር የሚገናኙበትን ኬሚካል እንዳይመነጭ ያግዳል፡፡ ይህም የሰውየውን የመተንፈሻ ጡንቻዎች ፓራላይዝ በማድረግ መታፈን ይፈጥርበታል፡፡

የሳይንቲስቶች ቡድን የሰራው ማርከሻ መድሃኒትም ፕሮቲን ሲሆን በምግብ መመረዙ ምክንያት እንዳይፈጠር የሚሆነውን ኬሚካል እንዲፈጠር በማገዝ በሰውየው ላይ የከፋ አደጋ እንዳይደርስ ይከላከላል፡፡

በብሩክሔቨን ናሽናል ላብራቶሪ የተፈጠረው ይኸው ፕሮቲን በተለይ አደገኛ በሆኑ የምግብ መመረዝ ምክንያቶች የሆኑና ምንም ህክምና የሌላቸው ሰባት የምግብ ብክለቶች የመከላከል ብቃት አለው፡፡

አዲሱ የምግብ መመረዝ ምክንያት የሚከሰትን አደገኛ የጤና ችግር ለመከላከል የሚረዳው ፕሮቲን በአሁኑ ወቅት ካሉት ከ10 እስከ 15 እጥፋ እንደሚሻል ሳይንቲስቶች ገልፀዋል፡፡

የተመረዘ ምግብ ባዩሉጂካል መሳሪያም ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ1990 እና በ1995 የጃፓን አሸባሪ ቡድን እንዲሁም በ1991 በነበረው የባህረ ሰላጤ ጦርነት ኢራቅ በሺዎች የሚቆጠር ሊትር የተመረዘ ምግብ አዘጋጅተው እንደነበር ይታወቃል፡፡

የተመረዘ ምግብ በሰዎች ላይ የሚያደርሰውን ገዳይነት ለማቆምም የሚደረገውን ጥናት ለመደገፍ የአሜሪካ መንግሥት በሚቀጥለው የፈረንጆች አመት 9 ቢሊዮን ዶላር እንደሚመደብ አስታውቋል፡፡

ሳይንቲስቶችና ፖለቲከኞች እየተሟገቱ ነው

የሰውን ልጅ ፅንስ ለተለያዩ ሳይንሳዊ ጥናቶች መጠቀመን በተመለከተ ሳይንቲስቶችና ፖለቲከኞች ሙግት ላይ እንደሆኑ ቢቢሲ ዘገበ፡፡

የሰውን ፅንሰ መጠቀምን የሚመለከተውን የእንግሊዝ ሕግ እንዲቀይር የሚጠይቅ ማመልከቻ የፓርላማ አባላት አቅርበዋል፡፡ ሕጉ የሰው ልጅን ፅንስ በመጠቀም ለዲኤንኤ እና የእንስሳት ሴል ለመስራት እንዲቻል ይፈቅዳል፡፡ በተለያዩ የካቶሊክ እምነት ተከታይ የሆኑ የፓርላማ አባላትና ሚኒስትሮች ሕጉን ይቃወማሉ፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ሳይንቲስቶች የሰዎችን መካንነት ለማዳንና በዘር የሚተላለፍ በሺታዎችን ለማዳን የሚያገለግሉ መድሃኒቶችን ለመስራት የሰው ልጅ ፅንስ በዋናነት ያገለግላል፡፡ በመሆኑም ሕጉ ትክክል ነው ይላሉ፡፡

ሕጉ ይቀጥል ወይም ይነስ በሚለው ጉዳይ ላይ የፓርላማ አባላት በቀጣይ ክርክር እንደሚያደርጉ የሚጠበቅ ሲሆን በክርክሩ የሚነሱ ነጥቦችንም ቢቢሲ በዘገባው ጠቅሷል፡፡

በክርክሩ ከሚነሱት የመጀመሪያው ነጥብ ከሰው ዲ ኤንኤ እና ትናንሽ የእንስሳትን አንድ አካል በመጠቀም ለሳይንሳዊ ጥናት የሚጠቀሙበትን የድቅል ፅንስ አመልክቷል፡፡ ሳይንቲስቶች ይህ ፅንስ የዘር ጉድለትን በተመለከተ ለሚደረግ ጥናት ጠቋሚ ይሄንን ስራ አንዳንዶች “ሞራልን የሚነካና በሰው ልጅ ተፈጥሮ ላይ የሚያላግጥ” ይሉታል፡፡    

ሁለተኛው የክርክር ነጥብ ደግሞ በማደግ ላይ ያለና ፅንስ የአጥነት መቅኒ ወይም እትብትን በመጠቀም በዘር የሚተላለፍ አደገኛ በሽታዎችን ለማከም የሚቻልበት ሳይንስ ነው፡፡ የሃሳቡ ደጋፊዎች መድሃኒት የሌሎች በዘር የሚተላለፉ በሽታዎችን ለማዳን ተስፋ የሚሰጥ ነው ሲሉ ተቃዋሚዎች ደግሞ ለዚህ አላማ ብቻ ልጆች እንዲፈጠሩ ወደ ማድረግ ወይም የተረገዘው ሴት ነው ወይስ ወንድ እያሉ ለሳይንሳዊ ጠቀሜታው ስንል ወደ መምረጥ እንዲያመራ ያደርጋል የሚል ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡

ከላይ የተጠቀሱትና ሌሎችም መከራከሪያ ሃሳቦች ላይ የእንግሊዝ ፓርላማ አባላት ከተከራከሩ በኋላ ሕጎቹ ደግሞ ስራ ላይ ይውላሉ ወይም ይሰረዛሉ፡፡

በጨረር ተክልንና እንሰሳትን መግደል ተቻለ

የማይፈለጉ ተክሎችንና እንስሳትን ለይቶ በጨረር መግደል የሚቻልበትን ዘዴ መፍጠራቸውን የአሜሪካ ሳይንቲስቶች አስታወቁ፡፡ በታንከር የተሞላ ውሃ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ እንስሳትንና ተክሎችን በመጨመር የተደረገው ሙከራም ውጤታማ እንደሆነ ነው ሳይንቲስቶቹ የገለፁት፡፡

በአለም ላይ እቃ ከአህጉር አህጉር የሚዘዋወርበት በመቶ በመርከብ ነው፡፡ የመርከቡ ካርጎ ሙሉ በሙሉ በዕቃ ከሞላ በሚደረገው የውሃ ላይ ጉዞም በየዓመት 5 ቢሊዮን ቶን ያህል ውሃ ከቦታ ቦታ ከመርከብ ጋር ይዘዋወራል ከአንድ ቦታ በመርከብ ጉዞው ምክንያት ተጠልፎ ወደ ሌላ ቦታ ከሚሄደው ዋሃ ጋርም አብረው የሚወጡ እንሰሳትና ተክሎች ከቦታ ቦታ ይዘዋወራሉ፡፡ ብዙዎችም ጉዞውን መቋቋም ስለማይችሉ መንገድ ላይ ይሞታሉ አንዳንዶቹ ግን የተሻለ መራቢያ ስፍራ በማግኘት ይራባሉ፡፡

ከመርከቡ ጉዞ ጋር ወደ ሌላ ቦታ ተወስደው በመራባታቸው አደገኛ ሁኔታን የሚፈጥሩ እንስሳትና ተክሎች እንዳሉ በጥናት መረጋገጡን የዘገበው ቢቢሲ ለዚሁ አደገኛ ሁኔታ መፍትሔ ለመስጠት ነው ከመርከቦች ጋር በገባ ውሃ የሚሄዱ እንስሳትን አዕዋፋት መካከል የማይፈለገውን በጨረር ለመግደል የሚያስችል ዘዴ መፈጠሩን ያትታል፡፡

ለምሳሌ ጂሊዴሽ የተሰኘው የአሳ አይነት ከመርከብ ጋር ወደ ጥቁር መጓጓዝ በአካባቢው ላሉ ሌላ የአሳ አይነቶች መጥፋት ምክንያት መሆኑን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል፡፡

 
< Prev   Next >