Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Aug 29th
Home arrow Sections arrow የአዲስ አበባ መልክዐ ምድር በደረቅ...
የአዲስ አበባ መልክዐ ምድር በደረቅ... Print E-mail
Sunday, 18 May 2008
የአዲስ አበባ መልክዐ ምድር በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ላይ ተጽዕኖ አሳደረ

የአዲስ አበባ መልክአ ምድራዊና አቀማመጥ አመቺ አለመሆን፣ የሕዝቡ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ሁኔታዎች ዝቅተኛ መሆን፣ በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩን አንድ ጥናት ይፋ አደረገ፡፡

ሶካንዲክ ኮንሰልታንስ ፒ.ኤል.ሲ በተባለው ኩባንያ የተካሄደው ይኸው ጥናት እንዳመለከተው ደረቅ ቆሻሻን ለመሰብሰብ የሚያስችል የመንገድና የሰዓት አጠቃቀም በሚገባ አለመቀረጽና በማጠራቀሚያ ገንዳዎች ውስጥ በሥነ ሥርዓት ባለማስቀመጥ በቆሻሻ አወጋገድ እንቅስቃሴ ላይ እንቅፋት ፈጥሯል፡፡

በየገንዳዎቹ በአግባቡ ባለመከማቸቱ የተነሳ በየቦታው ለመጣል ምክንያት መሆኑን ጥናቱ ጠቁሞ በአወጋገዱ ሥራ ቅልጥፍና በቂ ዕርዳታ አለማግኘት፣ የማጓጓዣ ተሽከርካሪዎች ጥገና ያለመኖር፣ የሕዝቡ ግንዛቤ ማነስ፣ በአወጋገድ ሥራ ላይ ማበረታቻዎች አለመኖርና ቆሻሻን መልሶ በጥቅም ላይ ለማዋል የሚካሄደው እንቅስቃሴ ደካማ መሆን ለችግሩ መባባስ አስተዋጽኦ ማድረጉን አስረድቷል፡፡

ከዚህ አኳያ አግባብ ያለው የደረቅ ቆሻሻ ማኔጅመንትን ሥራ ላይ በማዋል አዲስ አበባን ጽዱ ለማድረግ በሚካሄደው እንቅስቃሴ ላይ መንግሥትን ጨምሮ ነዋሪዎች፣ ኢንቨስተሮች፣ ሲቪክ ማኅበረሰብና ዕርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ንቁ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አሳስቧል፡፡

በከተማዋ ከሚሰበሰበው ደረቅ ቆሻሻ መካከል እስከ 65 በመቶ ያህሉ መንግሥት በሚያቀርባቸው ተሽከርካሪዎች ወደሚከማችበት ቦታ እንደሚጓጓዝ፣ ከ35 እስከ 40 በመቶ ያህሉ ደግሞ በየቦታው እንደሚጣልና ይህም ለአካባቢ ብክለት መንስኤ እንደሆነ ከጥናቱ ለመረዳት ተችሏል፡፡

ከዚህም ሌላ 70 ከመቶ ያህሉ ደረቅ ቆሻሻ ኮምፖዝድ ሆኖ ለባዮጋዝ አገልግሎት እንደሚውል፣ 15 ከመቶ ያህሉ ደግሞ በተለያየ መንገድ እንደገና ጥቅም ላይ ሊውል እንደሚችል ይህ አይነቱም ሁኔታ ለተሻለና ለምቹ አካባቢ እውን መሆን አስተዋጽኦ እንደሚያደርግና የሥራ ዕድልም እንደሚፈጥር ጥናቱ አመልክቷል፡፡

በ500 ሚሊዮን ብር ሆስፒታል ሊገነባ ነው


ሜድኮ ባዮ ሜዲካል ኮሌጅ በ500 ሚሊዮን ብር ወጪ የቴሌ ሜዲሰን አገልግሎት ያለው አንድ ጠቅላላ ሆስፒታል እንደሚያቋቁም ዶክተር መኮንን ሐጎስ የኮሌጁ ፕሬዚዳንት አስታወቁ፡፡

ሆስፒታሉ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የማገገሚያና የድንገተኛ ሕክምና አገልግሎት እንደሚሰጥም አስረድተዋል፡፡

የሆስፒታሉን ሕንፃ ኮሌጁ በ50 ሚሊዮን ብር ወጪ የማስገንባት ሥራ ይጀምርና የቀረውን ከኩባንያዎችና ከግለሰቦች ጋር ለማሰራት ማቀዱን ፕሬዚዳንቱ አስታውቀዋል፡፡
 
< Prev   Next >