| ሕብረት ኢንሹራንስ ብሔራዊ ባንክን ከሶ አሸነፈ |
|
| Sunday, 13 January 2008 | |
|
ሕብረት ኢንሹራንስ አክስዮን ማህበር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቁጥር ኤስቢቢ/39/2006 ያወጣውን መመሪያ በመቃወም በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በመሠረተወ ክስ ጥር 2 ቀን 2000 ዓ.ም በዋለው ችሎት አሸናፊ ሆነ፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በቁጥር ኤስቢቢ/39/2006 ባወጣው መመሪያ አንቀፅ 5.1.4 እና 5.1.5 ማናቸውም የባንክ ዳይሬክተር ሆና መስራት ላይ ያለ በሌሎች የገንዘብ ተቋሞች ውስጥ በዳይሬክተርነት እንዳይሰራ (እንዳይመረጥ..፣ ማንኛውም የባንክ ዳይሬክተር በተመረጠበት የባንክ ዳይሬክተርነት መደብ ከስድስት ተከታታይ ዓመታት በላይ እንዳያገለግል፣ መመረጥ የሚችለው ከስድስት ዓመታት የቆይታ ጊዜ በኋላ እንደሚሆን የደነገገውን መመሪያ በመቃወም፣ ሕብረት ኢንሹራንስ ሐምሌ 19 ቀን 1999 ዓ.ም በመሰረተው ክስ አሸናፊ ሆኗል፡፡ ፍርድ ቤቱ (ፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 6ተኛ ፍ/ብሔር ችሎት) ጥር 2 ቀን 2000 በዋለው ችሎት፣ የባንኩ መመሪያ አንቀጾች ከኢትዮጵያ ንግድ ሕግ (1952 ዓ.ም) አንቀፅ 347 (1)፣ 350 (3) እና 350 (4) ጋር መሰረት አድርጎ ከወጣው ከባንኩ መመስረቻ ጽሁፍ ጋር ፍጹም የሚጋጩ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ እንዲያወጣባቸው ከተሰጠው ስልጣን ክልል ውጭ በመሆናቸው፣ ሕግን የጣሱና ያለ ሕጋዊ ስልጣን በሕግ በተሰጡ በመሠረታዊ የባለ አክስዮኖች የመምረጥ፣ የመመረጥና ኢንቨስትመንታቸውን የማስተዳደር መብቶች ላይ ገደብ የሚጥሉ ናቸው፡፡ በመሆኑም ተፈፃሚነት ሊኖራቸው አይችልም በማለት ፍርድ ቤቱ መወሰኑን ሕብረት ኢንሹራንስ የወከላቸው ጠበቆች አቶ እሥራኤል ተክሌና አቶ ተፈራ ደምስ ለሪፖርተር ጋዜጣ ገልፀዋል፡፡ በታምሩ ጽጌ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |