Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Thursday
Aug 28th
Home arrow Sections arrow ለችግሩ እልባት ሊፈለግለት ይገባል
ለችግሩ እልባት ሊፈለግለት ይገባል Print E-mail
Sunday, 13 January 2008
ሪፖርተር ጋዜጣ ታህሳስ 30 ቀን 2000 ፖለቲካ ገጽ "በብሔር ፖለቲካ የሚታመሱት ዩኒቨርሲቲዎቻችን"  በሚል ርዕስ የቀረበው ጽሑፍ ተማሪዎች ብሔርን መሠረት ያደረገ የቡድን ድብደባና አምባ ጉዋሮ እንደባህል አድርገው የያዙት መሆኑን አሳይቷል፡፡ ይህ ዓይነቱን ችግር ለመቅጨት ጉዳዩ የሚመለከታቸው መንግሥታዊ አካላት ተገቢውን እርምጃ ሊወስዱ ይገባል፡፡

በቡድን እየተደራጁ የሚያካሂዱት ድብደባና አምባጉዋሮ መንስኤው ምንም ይሁን ምን ውጤቱ አደገኛ መሆኑን መታወቅ ይኖርበታል፡፡ ይህ አደገኛ አዝማሚያ ያለውና ወቅት እየጠበቀ የሚከሰተው የተማሪዎች የእርስ በርስ ግጭት ዘላቂ መፍትሄ ሲሰጠው አልታየም፡፡

ስለሆነም መንግሥት፣ የከፍተኛ ተቋም ተማሪዎች ገዢውና ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ሕብረተሰቡና የሃይማኖት አባቶች በጉዳዩ ላይ ተወያይተው ችግሩን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ የሚያስችል ስትራቴጂ በማውጣት እልባት ሊያበጁለት ይገባል፡፡

(ሣምሶን አየለ፣ ከአዲስ አበባ)

 
< Prev   Next >