| ጥበብ ከጎረቤት የሚዋሱት ዕቃ አይደለም |
|
| Sunday, 13 January 2008 | |
|
በረቡዕ ሪፖርተር ጋዜጣ ኪንና ባህል ገጽ ከቴዎድሮስ ሞሲሳ ጋር የተደረገው ቃለምልልስ አንብቤዋለሁ፡፡
አርቲስቱ ከጠበቃነት ሙያው ጐን ለጐን የተለያዩ ዘፈኖችን አሰምቶናል፡፡ በኮራ አፍሪካ ላይም በእጩነት ቀርቦ ቢያንስ ኢትዮጵያን ወክሏል፡፡ በቃለ ምልልሱ ላይ ራሴን ብቻ ሳይሆን የአድማጩንም ስሜት ለመዝፈን ሞክሬያለሁ ማለቱን አልወደድኩለትም፡፡ በዙሪያው ያሉ አድማጮቹን መሠረት አድርጎ ለመሥራት መሞከሩ አይከፋም፡፡ ነገር ግን ጥበብ ከስሜት የሚመነጭ እንጂ ከጐረቤት የሚዋሱት ዕቃ ባለመሆኑ የራሱን እምነትና ዕውቀት እንዳያሳጣው፡፡ (ምሥራቅ ተሾመ፣ ከ22 ማዞሪያ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |